top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


ጉንፋን ብለው አትዘናጉ! ሳንባ ምች ቢሆንስ?
የሳንባ ምች (Pneumonia) እንደ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ሊጀምር ይችላል። ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ወደ ሳንባ ሲደርስ ሳል፣ ትኩሳት፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል። በኢትዮጵያም የሳንባ ምች ብዙዎችን ለሞት የዳረገ በሽታ ነው። ሳንባ ምች እንዴት እንደሚይዝ፣ ከተለመደ ጉንፋን እንዴት ሊለይ እንደሚችል፣ እራስዎን እንዴት መከላከልና ምልክቶቹ ሲጀምሩ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 184 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


“ይሰማኛል! ግን ቃላቱ አይለዩልኝም?” — በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ የመስማት ችግር ምልክቶች
ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት የሚከሰት ወይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ ብቻ የሚገደብ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። የመስማት ችሎታ ማጣት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው ቀስ በቀስ ነው። በዚህ ጠቃሚ የጤና መመሪያ ውስጥ፣ “ድምፅ እየሰሙ ቃላትን ለመለየት መቸገርን” ጨምሮ በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የቀደሙ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን፣ ዋና ዋና መንስኤዎቻቸውን እና የሕክምና መፍትሔዎችን በዝርዝር እንመረምራለን።
Zebeaman Tibebu
Aug 57 min read


"ማንኮራፋት" የሰላማዊ እንቅልፍ መግለጫ ወይስ የጤና ጠንቅ?
"ማንኮራፋት የጥሩ እንቅልፍ ምልክት ነው" የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ህይወትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥለው ይጠንቀቁ! በምሽት የሚሰማው ይህ ድምፅ የልብ፣ የጭንቅላት ደም መፍሰስ (ስትሮክ) እና ከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤ የሆነው የ«ስሊፕ አፕኒያ» (Sleep Apnea) ስውር ምልክት ሊሆን ስለሚችልበት አስገራሚ እውነታ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 303 min read


የትራኮማ የዓይን በሽታ በኢትዮጵያ:- መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች
በኢትዮጵያ ከ61 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ይህ ጽሑፍ በቀላሉ መከላከል እየተቻለ ብርሃንን በዝምታ ስለሚሰርቀው የትራኮማ የዓይን በሽታ መንስኤዎች፣ ደረጃዎች እና ፍቱን ስለሆነው የዓለም ጤና ድርጅት የ"ሴፍ" (SAFE) መከላከያ ስልት ዝርዝር መረጃዎችን በሚስብ መልክ ያቀርባል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Jul 194 min read


ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን? ከማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ጀርባ ያለው እውነት
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ‘አዛውንት የሚመስል ህጻን በጥቁር ጺም ተወለደ’ የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ታይተዋል። የህክምና ሳይንስ ግን ‘ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን?’ ለሚለው ጥያቄ ከምናስበው በላይ አስደናቂ ምላሽ አለው። ከእድሜያቸው በላይ ያረጁ የሚመስሉ ህጻናትን ገጽታ የሚፈጥሩ ብርቅዬ የጤና እክሎች ምንድን ናቸው? ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 33 min read


የማሕበራዊ ሚዲያ አብዝቶ መጠቀም ጭንቅላት ላይ ያለው ተጽእኖ
ስልክዎን አብርተው ማለቂያ የሌለውን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ወደ ታች እየሳቡ ለሰዓታት መጥፋት የዕለት ተዕለት ልማድዎ ሆኗል? ይህ ዝም ብሎ የተፈጠረ ስንፍና ሳይሆን፣ የዲጂታል ዓለም አእምሯችንን አወቃቀርና የዶፓሚን (Dopamine) ሆርሞን ፍሰትን እንዴት እንደቀየረው የሚያሳይ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። ይህ ጽሑፍ ማህበራዊ ሚዲያ በትኩረት፣ በእንቅልፍ እና በስነ-ልቦናችን ላይ የሚያመጣውን ጫና (በተለይም በወጣቶች ላይ) በክሊኒካዊ መረጃዎች አስደግፎ ያብራራል። አእምሯችን ላይ የሚከሰተውን የኒውሮ ፕላስቲሲቲ (Neuroplasticity) ለውጥ እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል እና የስልክ አጠቃቀማችንን ሚዛናዊ ለማድረግ የሚረዱ ቀላል የሕክምና ሳይንስ መፍትሔዎችን ዝርዝር ይዟል። ሙሉውን አንብበው የአእምሮዎን ጤና እና ትኩረት ይመልሱ!
Zebeaman Tibebu
May 184 min read


ቤተሰብዎን ከአየር ብክለት እንዴት ይጠብቃሉ?
የአየር ብክለት በኢትዮጵያ ለሞት እና ለአካል ጉዳት ሁለተኛው ዋና መንስኤ መሆኑን ያውቃሉ? ይህ ጽሁፍ በአዲስ አበባ የሚታየውን ከፍተኛ የአየር ብክለት መጠን፣ ከተሽከርካሪ ጭስ እና ከቤት ውስጥ ቃጠሎ የሚመጡ የጤና ስጋቶችን በዝርዝር ያብራራል። ጤናማ የመተንፈሻ አካል እንዲኖርዎት በቤት ውስጥ ሊወስዷቸው የሚገቡ ቀላል እርምጃዎች፣ የትራፊክ ሰዓት ጥንቃቄዎች እና በሳይንሳዊ ማስረጃ የተደገፉ የመከላከያ መንገዶችን እዚህ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 244 min read


ልጅዎን ያመመው ቀላል ሕመም ነው ወይስ ሌላ?
በብዙ የኢትዮጵያ ቤቶች የሕፃናት ትኩሳትና ሳል የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን አንድ ቀላል ሕመም ወደ አደገኛ ደረጃ መሸጋገሩን እንዴት እናውቃለን? ይህ ጽሁፍ ባህላዊ እውቀትን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር በማቀናጀት ወላጆች የሕመምን መባስ እንዴት እንደሚያውቁ ይጠቁማል። የሳምባ ምችን የሚጠቁሙ አተነፋፈሶች፣ የወባ ስጋት እና የዚንክን አስፈላጊነት ጨምሮ የልጅዎን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ ወሳኝ ነጥቦችን ዝርዝር ይዞ ቀርቧል። ያንብቡት!
Zebeaman Tibebu
Apr 165 min read


ፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና : ጥሩ ወይስ መጥፎ
የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ከውበት ማሻሻያ ባለፈ የአካል ጉዳቶችን ለመጠገንና የተጎዱ ክፍሎችን ለመመለስ የሚረዳ የሕክምና ዘርፍ ነው። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የዘርፉን ታሪክ፣ ስነ-ልቦናዊ ፋይዳ፣ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት የሚከናወኑ እንደ ብራዚሊያን በት ሊፍት፣ የጡትቀዶ ጥገና ያሉትን ይነሳሉ። እስከ 2026 ያሉ መረጃዎች በአሃዝ ተደግፈው በዝርዝር ያገኛሉ።
Zebeaman Tibebu
Apr 25 min read


ለልጅ ስልክ መስጠት ኦቲዝም ያመጣ ይሆን?
የልጅዎ የንግግር መዘግየት ወይም የአይን ለአይን ግንኙነት መቀነስ ከስልክ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ይሆን? በአዲስ አበባ ቤቶች ውስጥ እየተለመደ የመጣው የ'ዲጂታል ኦቲዝም' ስጋት እና በመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት ውስጥ የሰው ልጅ ግንኙነት ያለው ወሳኝ ሚና ምን እንደሆነ ይረዱ። ቴክኖሎጂን ከልጅዎ እድገት ጋር እንዴት ማመጣጠን እንደሚችሉ የሚረዱ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Mar 304 min read


በህጻንነት ራሰ በራ ሊያደርግ የሚችለው ቆሮቆር በሽታ
በኢትዮጵያ ከአምስት ተማሪዎች አንዱ በራስ ቅል ፈንገስ (Tinea Capitis) ይያዛል። ይህ "እንደ ፎሮፎር" የሚጀምር ኢንፌክሽን በጊዜ ካልታከመ ለቋሚ ራሰ-በራነትና ለሥነ-ልቦና ጫና ይዳርጋል። ስለ በሽታው መተላለፊያ መንገዶችና ትክክለኛ ሕክምና እዚህ ያንብቡ
Zebeaman Tibebu
Feb 223 min read


ታዋቂዋ አርቲስት ለምን ንቅለ ተከላ አስፈለጋት?
ለመሆኑ ስመ ገናናዋ አርቲስት ሴሌና ጎሜዝ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለምን አስፈለጋት? ለአመታት ከ ስራዋ ያስተጓጎላት ከባድ በሽታ ምንድነው? ምልክቶቹስ ምንድናችው? ህክምናውስ ምን ይመስላል? ስለዚህ ሰውነት ራሱን ስለሚያጠቃበት በሽታ በጥልቀት ለመረዳት ፤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Dec 6, 20253 min read


❤️ የልብ ቧንቧ በሽታ ለምን ያጋጥማል?
የልብ ቧንቧ በሽታ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ኢንፌክሽንን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ፤ መከላከል እየተቻለ ብዙዎችን ለከፋ ደረጃ ይዳርጋል። ግን ለምን? ምን ማድረግ ይቻላል? የልብ ቧንቧ ችግሮች መንስኤዎችስ ምንድንናቸው? እርስዎስ እንደ ግለሰብ ምን ማድረግ ይችላሉ? ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ግንዛቤዎን ለማሻሻል ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Nov 2, 20254 min read


ሰሞነኛው ጉንፋን ለምን መጣ?
ሰሞኑን በመዲናችን በአዲስ አበባ ጉንፋን እየተስፋፋ ይገኛል። ይህ ወቅታዊ ጉንፋን ባይሆንስ? ምናልባት ከባድ ቢሆንስ? ለመሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ? ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ለዚህ ሁሉ ምላሽ ይዟል። ስለዚህ ጉንፋን መስፋፋት፣ መነሻ ምክንያቶች፣ አሳሳቢ ምልክቶች፣ መከላከያ ተግባራት፣ ማድረግ ያለብዎ ድርጊቶችና መቆጠብ ስላለብዎ ነገሮች መረጃን አስደግፎ ይዘረዝራል። ሙሉ ጽሁፉን ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Oct 26, 20255 min read


ካንሰር በኢትዮጵያ ፡ ለመሆኑ ዝግጁ ነን?
ካንሰር ድሮ የሀብታም ሀገሮች ችግር ተብሎ ቢታሰብም፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ ብዙዎችን እየቀጠፈ ያለ አንገብጋቢ የጤና ችግር ነው። በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ80,000 በላይ ሰዎች ካንሰር ይታመማሉ፣ ከ50,000 በላይ ህይወታቸውን ያጣሉ። ለመሆኑ ኝ ቆም ብለው ለምን ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? እንዴትስ መከላከል እንደሚቻል ያውቃሉ? እንግዲያውስ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Oct 22, 20255 min read


እንጥል መቆረጥ ወይስ?
የቶንሲል ህመም ህጻናትን አብዝቶ የሚያጠቃ ሲሆን ለመዳን በባህላዊ መንገድ እንጥል የሚያስቆርጡ ብዙዎች ናቸው። ይህም ብዙ ህፃናትን ለአደጋ ያጋልጣል። አሳዛኙ እውነታ እንጥል መቆረጥ ከቶንሲል አይከላከልም። ለምን? እንዴት የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ስለ ቶንሲል በሽታ እና ህክምናው በጥልቅ ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Oct 3, 20254 min read


ትምባሆና የኤሌክትሪክ ሲጋራ ያላቸው የጤና እክል
ከአለም አንጻር ያነሰ ቢሆንም፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሲጋራ ያጨሳሉ። በ10 ሚሊየን የሚቆጠሩ በእጅ አዙር ያጨሳሉ፤ በየአመቱ ቢያንስ 1.3 ሚሊየን ሰዎች በእጅ አዙር በማጨሳቸው ይሞታሉ። አዲስ የመጣው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ደግሞ ይህንን ጥፋት ይጨምራል። ስለ ትምባሆና ኤሌክትሪክ ሲጋራ ጤና እክሎች፣ ስርጭት፣ ሱስ እና ህክምና መፍትሄዎች ለማወቅ ይህን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 13, 20255 min read


የስኳር በሽታ አስከፊ ዳፋ የሆነው ዲኬኤ
ክትትል ያልተደረገለት ስኳርን ተከትሎ የሚመጣ ሆድ ህመም ለህይወት አስጊ ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ? ይህ ህመም ዲያቤቲክ ኬቶ አሲዶሲስ ይባላል። ከሆድ ህመም ባሻገር ፤ ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት፣ ውህ አብዝቶ መጠጣት እንዲሁም ማቅለሽለሽ ምልክቶቹ ሊሆኑ ይችላሉ። በሰለጠኑ ሀገራት እምብዛም ቢሆንም ፤ በኢትዮጵያ ይህ ህመም እስከ 46 ፐርሰንት እንደሚያጋጥም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስለዚህ ህመም ፣ ምልክቶቹ ፣ መንስኤዎቹ እና መከላከያ መንገዶቹ በይበልጥ ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 10, 20254 min read


❗ሾተላይ
ሾተላይ በባል እና ሚስት ደም አለመጣጣም ላይ ተመስርቶ በእርግዝና ወቅት፤ ጽንስን የሚያጠፋ ነው። ሾተላይ መከላከያ መድሐኒት ቢኖረውም ፤ በግንዛቤ ጉድለት የተነሳ፤ አሁንም እናቶች እየተጠቁ ይገኛሉ። ስለ ሾተላይ በሽታ የተሟላ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 31, 20253 min read
bottom of page
