top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


የቀሲል 5 ጥቅሞች እና አስፈላጊ ጥንቃቄዎች
በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሴቶች የሚቀቡት ቀሲል ምንድነው? ቀሲል የውበት መጠበቂያ መሆኑ ተራ የዘልማድ ተረት ወይስ ሳይንስ የመሰከረለት እውነተኛ የቆዳ ፈውስ? የአለም አቀፍ የውበት ኢንደስትሪን ቀልብ እየሳበ ስላለው ስለዚህ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ማንም ያልነገረዎትን 5 አስገራሚ ጥቅሞች እና ሊያደርጉት የሚገቡ 4 ወሳኝ ጥንቃቄዎችን ይወቁ። ግንዛቤዎን ያስፉ።
Zebeaman Tibebu
16 hours ago4 min read


ለረዥም ሰዓት ሲቀመጡ ወይም ሲቆሙ ወገብዎን ያምዎታል? ለምን?
ለረዥም ሰዓት በቢሮ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ወይም ቆመው ሲሠሩ ወገብዎ ያምዎታል? ብዙዎቻችን ይህንን ከዕድሜ መግፋት ጋር ብናያይዘውም፤ እውነታው ግን የተለየ ነው። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከ90% በላይ ለሚሆነው ተራ የወገብ ሕመም ሳይንሳዊ መንስኤዎችን፣ የወገብ ሕመምን የሚከላከሉበትን ቀለል ያሉ መፍትሔዎች በጥልቀት እንፈትሻለን።
Zebeaman Tibebu
4 days ago4 min read


MRI ወይስ CT Scan? የትኛው የተሻለ ነው?
CT ወይስ MRI? የቱ ነው የሚሻል? ብዙዎች MRI ከCT “የላቀ” ምርመራ እንደሆነ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ CT ፈጣን ስለሆነ ይመርጡታል። እውነታው ግን ...... የሁለቱን ሳይንሳዊ ልዩነት፣ የትኛው መሣሪያ ለየትኛው በሽታ ቀዳሚ ምርጫ እንደሆነ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
Sep 94 min read


ሥራዬን እወደዋለሁ ግን መሄድ ሰልችቶኛል፦ ሥራ እና የአእምሮ ጤና
“ሥራዬን እወደዋለሁ… ግን ከእንግዲህ መሄድ አልፈልግም።” ይህ የሰነፍ ሰዎች ሰበብ ሳይሆን፣ በሀገራችን በብዙ የሥራ ዘርፎች ውስጥ በየቀኑ የሚሰማ የጤና እክል ምልክት ነው። በዚህ የሕክምና ጽሑፍ ውስጥ በሥራ ላይ ጭንቀት፣ በሥራ መቃጠል (Burnout) እና በድብርት (Depression) መካከል ያሉትን ወሳኝ ልዩነቶች፣ የዓለምና የሀገራችንን ተጨባጭ ቁጥሮች፣ እንዲሁም መፍትሔዎቹን እንፈትሻለን። ያንብቡ። አእምሮዎን መጠበቅ ሥራዎን መጥላት ሳይሆን ራስዎን መታደግ ነው።
Zebeaman Tibebu
Sep 45 min read


በቀን ስንት ስኳርና ጨው መመገብ አለብን?
በምግባችን ውስጥ ትክክለኛውና ጤናማው የስኳር እና የጨው መጠን ስንት ነው? “እኔማ በሻይ ላይ ስኳር አልጨምርም” ማለት ብቻውን በቂ ዋስትና አይሆንም። እንደ በርበሬ እና ሽሮ ያሉ ባህላዊ ምግቦች ውስጥ አስቀድሞ የሚጨመረውን ስውር ጨው ከግምት በማስገባት፤ በቀን ልንመገበው የሚገባንን ትክክለኛ መጠን ምን ያህል ነው። ለተሻለ ግንዛቤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 14 min read


ስለ ጭንቅላት ዕጢ ማወቅ ያለብዎ!
የአንጎል ዕጢ (Brain Tumor) ምንድን ነው? ምልክቶቹስ እንዴት ይታወቃሉ? ብዙዎች “ካንሰር አይደለም” ማለት “ምንም አደጋ የለውም” የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ይህ ጽሑፍ አዲስ የራስ ምታት፣ የእይታ መለወጥና መንቀጥቀጥን ጨምሮ 8 ዋና ዋና የአንጎል ዕጢ ምልክቶችን ያብራራል። በተጨማሪም በሽታው በደም ምርመራ የማይታወቅበትን ምክንያት፣ የ-MRI እና የባዮፕሲ ጥቅምን እንዲሁም ያሉ የሕክምና አማራጮችን ይዘረዝራል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 284 min read


የጾም ሳይንሳዊ ሚስጥር፡ ሳይንስ ዛሬ የደረሰበት የጤና መፍትሔ
አብዛኞቻችን ጾምን እንጾማለን። አባቶቻችን ከዘመናት በፊት በመንፈሳዊ ጥበብ የኖሩትን ይህንን የጾም በረከት፣ ዛሬ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎ በሳይንስ ተደግፎ መጥቷል። ይህ ዘመናዊ አጿጿም ("Intermittent Fasting") ምንድነው? ለጤናችንስ ያለውን እውነተኛ ፋይዳ ምን ይመስላል?
Zebeaman Tibebu
Aug 255 min read


እያንዳንዱ ወንድ ሊያውቀው የሚገባው የፕሮስቴት ካንሰር
“እያረጀሁ ስለሆነ ነው” በሚል ሰበብ የሽንት መለወጥን ቸላ አይበሉ!ብዙ ጊዜ የፕሮስቴት ካንሰር በትልቅ ምልክት አይጀምርም። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ፣ አንድ ተራ የሽንት መቆራረጥ እንዴት ከአስፈሪው ካንሰር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል የሚያሳይ እናሳያለን። ስለ ፕሮስቴት ምንነት፣ ስለ በሽታው ምልክቶች፣ ቀድሞ ስለመመርመሪያ ዕድሜ እና ስላሉት ዘመናዊ የሕክምና አማራጮች በዝርዝር ያንብቡ። ቀድሞ መለየት ሕይወትን ያድናል!
Zebeaman Tibebu
Aug 205 min read


ጉንፋን ብለው አትዘናጉ! ሳንባ ምች ቢሆንስ?
የሳንባ ምች (Pneumonia) እንደ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ሊጀምር ይችላል። ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ወደ ሳንባ ሲደርስ ሳል፣ ትኩሳት፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል። በኢትዮጵያም የሳንባ ምች ብዙዎችን ለሞት የዳረገ በሽታ ነው። ሳንባ ምች እንዴት እንደሚይዝ፣ ከተለመደ ጉንፋን እንዴት ሊለይ እንደሚችል፣ እራስዎን እንዴት መከላከልና ምልክቶቹ ሲጀምሩ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 184 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


ኮሌስትሮል፦ ወዳጅ ወይስ ጠላት? መንስኤዎቹ፣ ምልክቶቹ፣ እና መፍትሔው
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ለዓመታት ሊቆይ ይችላል። ራስዎን ጤነኛ እየተሰማዎትም ቢሆን ኮሌስትሮልዎ ከፍ ሊል ይችላል። ምልክቶችን ከመጠበቅ ይልቅ ምርመራ ማድረግ ለምን አስፈላጊ ነው? ይህንን እና ስለኮሌስትሮል የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 105 min read


“ይሰማኛል! ግን ቃላቱ አይለዩልኝም?” — በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ የመስማት ችግር ምልክቶች
ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት የሚከሰት ወይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ ብቻ የሚገደብ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። የመስማት ችሎታ ማጣት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው ቀስ በቀስ ነው። በዚህ ጠቃሚ የጤና መመሪያ ውስጥ፣ “ድምፅ እየሰሙ ቃላትን ለመለየት መቸገርን” ጨምሮ በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የቀደሙ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን፣ ዋና ዋና መንስኤዎቻቸውን እና የሕክምና መፍትሔዎችን በዝርዝር እንመረምራለን።
Zebeaman Tibebu
Aug 57 min read


ውሻ ነክሶዎታል? ማወቅ ያለብዎት እውነታዎች!
የውሻ ንክሻን በፍጹም "ቀላል ቁስል" ብለው አይለፉ! የሬቢስ (Rabies) ቫይረስ ምልክት ከመታየቱ በፊት ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ ግን ለሞት ይዳርጋል። ከንክሻ በኋላ ባሉ የመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች መወሰድ ስላለባቸው ወሳኝ እርምጃዎች እና ህይወትን የሚያድኑ የህክምና መንገዶችን ይወቁ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 35 min read


"ማንኮራፋት" የሰላማዊ እንቅልፍ መግለጫ ወይስ የጤና ጠንቅ?
"ማንኮራፋት የጥሩ እንቅልፍ ምልክት ነው" የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ህይወትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥለው ይጠንቀቁ! በምሽት የሚሰማው ይህ ድምፅ የልብ፣ የጭንቅላት ደም መፍሰስ (ስትሮክ) እና ከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤ የሆነው የ«ስሊፕ አፕኒያ» (Sleep Apnea) ስውር ምልክት ሊሆን ስለሚችልበት አስገራሚ እውነታ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 303 min read


አፍንጫዎ ሁልጊዜ ተደፍኖ ይሰማዎታል? ጉንፋን ሳይሆን የአፍንጫ እጢ ቢሆንስ?
አፍንጫዎ ለወራት ተደፍኖ ከቆየ፤ ሁልጊዜ ንፍጥ ካለዎት፤ ወይም ሽታ የመለየት አቅምዎ ቀስ በቀስ ከቀነሰ፤ ችግሩ ቀላል ጉንፋን ብቻ ላይሆን ይችላል። ናዛል ፖሊፕ (Nasal Polyp) በአፍንጫና በሳይነስ ውስጥ በሚኖር ሥር የሰደደ መቆጣት የሚፈጠር ካንሰር ያልሆነ እጢ ሲሆን፤ የመተንፈስ ችግር፣ የሽታ መቀነስ፣ የሳይነስ ኢንፌክሽን እና የእንቅልፍ መታወክን ሊያስከትል ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ስለናዛልፖሊፕ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ሕክምና እና መቼ ሐኪም ማየት እንደሚገባ በዝርዝር ቀርቧል። ለበለጠ ግንዛቤ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Jul 273 min read


በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ የጉበት ቫይረሶች
ሄፓታይተስ ኤ እና ኢ በበዛት በሕጻንነት ዘመን የሚታዩ፤ ጉበትን የሚያጠቁ ቫይረሶች ናቸው። እነኝህ ቫይረሶች በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ የጉበት ሥራን በፍጥነት በማሰናከል እስከ 25% የሞት አደጋ ያስከትላሉ። የበሽታውን ምልክቶቹ፣ መከላከያ መንገዶች፣ ምርመራዎች ፣ ህክምናውን እና መከላከያ መንገዶቹን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 225 min read


የትራኮማ የዓይን በሽታ በኢትዮጵያ:- መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች
በኢትዮጵያ ከ61 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ይህ ጽሑፍ በቀላሉ መከላከል እየተቻለ ብርሃንን በዝምታ ስለሚሰርቀው የትራኮማ የዓይን በሽታ መንስኤዎች፣ ደረጃዎች እና ፍቱን ስለሆነው የዓለም ጤና ድርጅት የ"ሴፍ" (SAFE) መከላከያ ስልት ዝርዝር መረጃዎችን በሚስብ መልክ ያቀርባል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Jul 194 min read


ለሳምንታት የቆየው የዳንስ ወረርሽኝ ፡ ከ 500 አመት በኋላ ያልተፈታ ሚስጥር
ሰዎች እግራቸው እየደማ፤ በልብ ድካምና በረሃብ እስኪወድቁ ድረስ ለሳምንታት እንዲደንሱ ያደረጋቸው ምስጢራዊ ኃይል ምንድን ነው? የተመረዘ ዳቦ፣ የነርቭ በሽታ ወይስ የጋራ የአእምሮ መዛባት? በ16ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓን ያናወጠውና እስከ ዛሬ ድረስ ፍቺ ያልተገኘለት የስትራስቡርግ የዳንስ ወረርሽኝ የሳይንስ ሊቃውንትንና የታሪክ ተመራማሪዎችን ለዘመናት ሲያከራክር የኖረ ትልቅ እውነት ነው። ለሕክምና እንቆቅልሽ የሆነውን የዚህን አስገራሚ ክስተት ለማወቅ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 166 min read


የመመረዝ አደጋ በኢትዮጵያ፦ የሚያጋጥሙ መርዞች እና መፍትሔዎቻቸው
በኢትዮጵያ በብዛት የሚከሰቱ ድንገተኛ የመመረዝ አደጋዎችን፣ መንስኤዎቻቸውን እና ሕይወት አድን የሆኑ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ መንገዶችን ይረዱ። ሰከንዶች በሚወስኑበት በዚህ የሕክምና ቀውስ ውስጥ ምን ማድረግ እና ምን ማስወገድ እንዳለብዎት ይወቁ። እራስዎን ያዘጋጁ።
Zebeaman Tibebu
Jul 96 min read


የዝሆኔ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይከሰታል? መከላከያ መንገዶቹስ
የዝሆኔ በሽታ (Elephantiasis) በአብዛኛው አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ብዙዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። በሀገራችንም ይህ በሽታ ከትንኝ ንክሻ እና ቀይ አፈር ላይ በባዶ እግር ከመሄድ ጋር ይያዛል። የበሽታውን ምልክቶች፣ የሕክምና አማራጮች እና ራስን የመከላከያ መንገዶችን ይወቁ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 65 min read
bottom of page
