top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


ግማሽ አንጎሏን አጥታ ማስተር የያዘችው ሴት ታሪክ
ግማሽ አንጎሏ ተወግዶ እንዴት መኖር ቻለች? የክሪስቲና ሳንታውዝ አስደናቂ የሕይወት ታሪክ የሰው አንጎል የመላመድ አቅምን (Neuroplasticity) እና ከባድ የአንጎል በሽታ በኋላ የማገገም አቅምን ያሳያል። በ8 ዓመቷ ከRasmussen’s encephalitis ጋር ከባድ የሚጥል በሽታ ያጋጠማት ክሪስቲና፤ የአንጎሏ ግማሽ ከተወገደ በኋላ እንዴት ወደ ትምህርት፣ ሥራ እና ሙሉ ሕይወት መመለስ ቻለች?
Zebeaman Tibebu
Oct 14 min read


ሲቀመጡ ወይም ሲቆሙ ወገብዎን ያምዎታል? ለምን?
ለረዥም ሰዓት በቢሮ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ወይም ቆመው ሲሠሩ ወገብዎ ያምዎታል? ብዙዎቻችን ይህንን ከዕድሜ መግፋት ጋር ብናያይዘውም፤ እውነታው ግን የተለየ ነው። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከ90% በላይ ለሚሆነው ተራ የወገብ ሕመም ሳይንሳዊ መንስኤዎችን፣ የወገብ ሕመምን የሚከላከሉበትን ቀለል ያሉ መፍትሔዎች በጥልቀት እንፈትሻለን።
Zebeaman Tibebu
Sep 144 min read


MRI ወይስ CT Scan? የትኛው የተሻለ ነው?
CT ወይስ MRI? የቱ ነው የሚሻል? ብዙዎች MRI ከCT “የላቀ” ምርመራ እንደሆነ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ CT ፈጣን ስለሆነ ይመርጡታል። እውነታው ግን ...... የሁለቱን ሳይንሳዊ ልዩነት፣ የትኛው መሣሪያ ለየትኛው በሽታ ቀዳሚ ምርጫ እንደሆነ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
Sep 94 min read


ስለ ጭንቅላት ዕጢ ማወቅ ያለብዎ!
የአንጎል ዕጢ (Brain Tumor) ምንድን ነው? ምልክቶቹስ እንዴት ይታወቃሉ? ብዙዎች “ካንሰር አይደለም” ማለት “ምንም አደጋ የለውም” የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ይህ ጽሑፍ አዲስ የራስ ምታት፣ የእይታ መለወጥና መንቀጥቀጥን ጨምሮ 8 ዋና ዋና የአንጎል ዕጢ ምልክቶችን ያብራራል። በተጨማሪም በሽታው በደም ምርመራ የማይታወቅበትን ምክንያት፣ የ-MRI እና የባዮፕሲ ጥቅምን እንዲሁም ያሉ የሕክምና አማራጮችን ይዘረዝራል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 284 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


ኮሌስትሮል፦ ወዳጅ ወይስ ጠላት? መንስኤዎቹ፣ ምልክቶቹ፣ እና መፍትሔው
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ለዓመታት ሊቆይ ይችላል። ራስዎን ጤነኛ እየተሰማዎትም ቢሆን ኮሌስትሮልዎ ከፍ ሊል ይችላል። ምልክቶችን ከመጠበቅ ይልቅ ምርመራ ማድረግ ለምን አስፈላጊ ነው? ይህንን እና ስለኮሌስትሮል የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 105 min read


ውሻ ነክሶዎታል? ማወቅ ያለብዎት እውነታዎች!
የውሻ ንክሻን በፍጹም "ቀላል ቁስል" ብለው አይለፉ! የሬቢስ (Rabies) ቫይረስ ምልክት ከመታየቱ በፊት ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ ግን ለሞት ይዳርጋል። ከንክሻ በኋላ ባሉ የመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች መወሰድ ስላለባቸው ወሳኝ እርምጃዎች እና ህይወትን የሚያድኑ የህክምና መንገዶችን ይወቁ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 35 min read


ለሳምንታት የቆየው የዳንስ ወረርሽኝ ፡ ከ 500 አመት በኋላ ያልተፈታ ሚስጥር
ሰዎች እግራቸው እየደማ፤ በልብ ድካምና በረሃብ እስኪወድቁ ድረስ ለሳምንታት እንዲደንሱ ያደረጋቸው ምስጢራዊ ኃይል ምንድን ነው? የተመረዘ ዳቦ፣ የነርቭ በሽታ ወይስ የጋራ የአእምሮ መዛባት? በ16ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓን ያናወጠውና እስከ ዛሬ ድረስ ፍቺ ያልተገኘለት የስትራስቡርግ የዳንስ ወረርሽኝ የሳይንስ ሊቃውንትንና የታሪክ ተመራማሪዎችን ለዘመናት ሲያከራክር የኖረ ትልቅ እውነት ነው። ለሕክምና እንቆቅልሽ የሆነውን የዚህን አስገራሚ ክስተት ለማወቅ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 166 min read


የመመረዝ አደጋ በኢትዮጵያ፦ የሚያጋጥሙ መርዞች እና መፍትሔዎቻቸው
በኢትዮጵያ በብዛት የሚከሰቱ ድንገተኛ የመመረዝ አደጋዎችን፣ መንስኤዎቻቸውን እና ሕይወት አድን የሆኑ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ መንገዶችን ይረዱ። ሰከንዶች በሚወስኑበት በዚህ የሕክምና ቀውስ ውስጥ ምን ማድረግ እና ምን ማስወገድ እንዳለብዎት ይወቁ። እራስዎን ያዘጋጁ።
Zebeaman Tibebu
Jul 96 min read


ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን? ከማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ጀርባ ያለው እውነት
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ‘አዛውንት የሚመስል ህጻን በጥቁር ጺም ተወለደ’ የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ታይተዋል። የህክምና ሳይንስ ግን ‘ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን?’ ለሚለው ጥያቄ ከምናስበው በላይ አስደናቂ ምላሽ አለው። ከእድሜያቸው በላይ ያረጁ የሚመስሉ ህጻናትን ገጽታ የሚፈጥሩ ብርቅዬ የጤና እክሎች ምንድን ናቸው? ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 33 min read


ቲማቲም አሜባን ይቀሰቅስ ይሆን? ስለ አሜባ በሽታ እና መከላከያ መንገዶች ይወቁ!
“ቲማቲም አትብላ!"" ሰላጣ ከበላህ አሜባህ ይነሳል።” ይህን ምክር ያልሰማ ኢትዮጵያዊ የለም። ነገር ግን አሜባ ለዓመታት ተኝቶ ኖሮ፤ ቲማቲም ስለበላን ብቻ በድንገት ሊነቃ ይችላልን? ይህንን አስተሳሰብ በሳይንሳዊ ማስረጃ የሚሞግተውን፣ ስለ አሜባ ጥልቅ ግንዛቤ የሚሰጠውን፣ ምልክቶቹንና፣ ትክክለኛውን የአሜባ ሕክምና የሚያሳየውን አዲሱን ጽሑፋችንን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 305 min read


አንዳንድ ሰዎች መኪና ውስጥ ለምን ይታመማሉ?
በአንድ መኪና ውስጥ እያደረጉት ባለው ጉዞ ላይ አንዱ ተሳፋሪ ምንም ሳይለው ሌላው ግን በከባድ ማቅለሽለሽ የሚሰቃየው ለምንድን ነው? የችግሩ ምስጢር ያለው ሆዳችን ውስጥ ሳይሆን በዓይናችን እና ጆሯችን ጋር ነው። ከዚህ ህመም በስተጀርባ ያለውን ሳይንስ ይረዱ። ቀጣዩን ጉዞዎንም ሙሉ በሙሉ ምቹ ለማድረግ የሚረዱ በተግባር የተፈተኑ የሕክምና መፍትሄዎችን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 255 min read


መጸዳጃ ቤት ውስጥ ማማጥ በጤናችን ላይ የሚያስከትለው ከባድ መዘዝ
ብዙዎቻችን ሽንት ቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓት የመቀመጥ እና የማማጥ ልማድ አለን። ነገር ግን ይህ ቀላል የሚመስል ልማድ ለኪንታሮት፣ ለራስ መሳት፣ ለዓይን ጉዳት ወይም ለድንገተኛ የልብ አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል ያውቃሉ? ማማጥ በሰውነታችን ላይ የሚያመጣውን ድብቅ የሕክምና አደጋ እና ችግሩን የምናስወግድባቸውን 7 ተግባራዊ መንገዶች ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 46 min read


ሳይንስ ያልፈታው እንቆቅልሽ፦ የአእምሮ ጤና እውነታዎች
ስለ "ጤና" ስናስብ ወደ አእምሯችን የሚመጣው የደም ግፊት፣ ስኳር ወይም የሰውነት ክብደት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች ከጀርባ ሆኖ በዝምታ የሚዘውረውን ዋና መሪ — አእምሯችንን — እንዘነጋዋለን። ይህ ጽሑፍ በዘመናዊ ሕክምና ውስጥ እጅግ ወሳኝ ወደሆነውና ብዙ የተሳሳተ ግንዛቤ ወደተወሰደበት የአእምሮ ጤና (Mental Health) እውነታ ይወስደዎታል። ሙሉውን ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
May 314 min read


ህመም ያለመሰማት በሽታ (CIP)፡ ፀጋ ወይስ ርግማን
ህመም አለመሰማት ልዩ ስጦታ ወይስ አሰቃቂ የህክምና ቅዠት? ተፈጥሯዊ የህመም ስሜት እጦት (CIP) የተባለውን እጅግ አልፎ አልፎ የሚታይ ከዘረመል ጋር ተይያዝነት ያለውን በሽታ እናነሳለን። ለምን ህመም ለሰው ልጅ ህልውና ወሳኝ የጥበቃ ዘዴ እንደሆነ በዚህ አስገራሚ የህክምና ጽሑፍ ውስጥ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
May 244 min read


የማሕበራዊ ሚዲያ አብዝቶ መጠቀም ጭንቅላት ላይ ያለው ተጽእኖ
ስልክዎን አብርተው ማለቂያ የሌለውን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ወደ ታች እየሳቡ ለሰዓታት መጥፋት የዕለት ተዕለት ልማድዎ ሆኗል? ይህ ዝም ብሎ የተፈጠረ ስንፍና ሳይሆን፣ የዲጂታል ዓለም አእምሯችንን አወቃቀርና የዶፓሚን (Dopamine) ሆርሞን ፍሰትን እንዴት እንደቀየረው የሚያሳይ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። ይህ ጽሑፍ ማህበራዊ ሚዲያ በትኩረት፣ በእንቅልፍ እና በስነ-ልቦናችን ላይ የሚያመጣውን ጫና (በተለይም በወጣቶች ላይ) በክሊኒካዊ መረጃዎች አስደግፎ ያብራራል። አእምሯችን ላይ የሚከሰተውን የኒውሮ ፕላስቲሲቲ (Neuroplasticity) ለውጥ እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል እና የስልክ አጠቃቀማችንን ሚዛናዊ ለማድረግ የሚረዱ ቀላል የሕክምና ሳይንስ መፍትሔዎችን ዝርዝር ይዟል። ሙሉውን አንብበው የአእምሮዎን ጤና እና ትኩረት ይመልሱ!
Zebeaman Tibebu
May 184 min read


ዳማከሴ ወይስ ጤና አዳም ፡ የቱ ይሻላል?
በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዳማከሴ እና ጤና አዳም እጅጉን ጥቅም ላይ የሚውሉ የቤት ውስጥ መድሀኒቶች ናቸው። ነገር ግን አንዱ ለመተንፈሻ አካላት፣ ሌላኛው ደግሞ ለምግብ መፈጨት ልዩ 'ባለሙያ' መሆናቸውን ያውቁ ኖሯል? ይህ ጽሑፍ የጥንቱን የኢትዮጵያ የዕፅዋት ጥበብ ከዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ ጋር በማጣመር የሁለቱን እፅዋት ድብቅ ኃይል፣ ጥቅምና አስፈላጊ ጥንቃቄዎች በዝርዝር ያብራራል። 'ተፈጥሯዊ' መሆኑ ብቻውን 'ደህንነቱ የተጠበቀ' እንደማያደርገው ተገንዝበው፤ እነዚህን ውድ እፅዋት እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚችሉ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
May 135 min read


ከ 8000 ኪሎ ሜትር ርቀት የተደረገው ቀዶ ጥገና
በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቆ የሚገኝ ሐኪም፣ ልክ በአንድ ክፍል ውስጥ እንዳለ ሆኖ ቀዶ ጥገና ሲያከናውን ማሰብ ይቻላል? ዛሬ ይህ ሳይንስ ልብ-ወለድ ሳይሆን እውነት ሆኗል! ርቀትን ድል የነሳው የቴሌ-ሰርጀሪ (Telesurgery) ቴክኖሎጂ፣ ከለንደን እስከ ጂብራልታር፣ ከሮም እስከ ቤጂንግ ድረስ የሕክምና ዓለምን ድንበር እየሰበረ ነው። ነገር ግን ይህ ታላቅ ተስፋ በጀርባው ምን ዓይነት የቴክኖሎጂ ስጋቶችንና የሞራል ጥያቄዎችን ደቅኗል? ሕይወት በዲጂታል መስመር ላይ ሲጓዝ የሚገጥሙትን አስገራሚ እውነታዎች በዚህ ጽሑፍ በጥልቀት ይፈትሹ።
Zebeaman Tibebu
May 74 min read


ስኳር ማቆም ከ ስኳር በሽታ ይታደጋልን?
ብዙዎቻችን ስኳርን ማቆም ብቻውን ከስኳር ህመም የሚጠብቀን ይመስለናል። ነገር ግን እውነታው ከዚያ የሰፋ ነው! ይህ ጽሁፍ ስለ ኢንሱሊን መቋቋም ሳይንሳዊ ሚስጥር፣ በታሸጉ ምግቦች ውስጥ ስለሚደበቁ ስኳሮች እና እንደ ነጭ ዳቦና ሩዝ ያሉ ምግቦች እንዴት ስኳር በሽታን እንደሚያባብሱ ያብራራል። በተጨማሪም የ'4-ግራም ህግን' በመጠቀም ጤናዎን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Apr 273 min read


ሙዚቃ እና ጤና
ሙዚቃ ዝም ብሎ መዝናኛ ነው ወይስ ባዮሎጂያዊ ፍላጎት? ከልብ ትርታ መረጋጋት ጀምሮ አእምሮን እስከ ማደስ ድረስ ፤ ሙዚቃ እንዴት እንደ ተፈጥሯዊ የህመም ማስታገሻና የበሽታ መከላከል አቅም ማጠናከሪያ እንደሚያገለግል ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 205 min read
bottom of page
