top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ የጉበት ቫይረሶች
ሄፓታይተስ ኤ እና ኢ በበዛት በሕጻንነት ዘመን የሚታዩ፤ ጉበትን የሚያጠቁ ቫይረሶች ናቸው። እነኝህ ቫይረሶች በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ የጉበት ሥራን በፍጥነት በማሰናከል እስከ 25% የሞት አደጋ ያስከትላሉ። የበሽታውን ምልክቶቹ፣ መከላከያ መንገዶች፣ ምርመራዎች ፣ ህክምናውን እና መከላከያ መንገዶቹን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 225 min read


የትራኮማ የዓይን በሽታ በኢትዮጵያ:- መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች
በኢትዮጵያ ከ61 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ይህ ጽሑፍ በቀላሉ መከላከል እየተቻለ ብርሃንን በዝምታ ስለሚሰርቀው የትራኮማ የዓይን በሽታ መንስኤዎች፣ ደረጃዎች እና ፍቱን ስለሆነው የዓለም ጤና ድርጅት የ"ሴፍ" (SAFE) መከላከያ ስልት ዝርዝር መረጃዎችን በሚስብ መልክ ያቀርባል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Jul 194 min read


ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን? ከማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ጀርባ ያለው እውነት
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ‘አዛውንት የሚመስል ህጻን በጥቁር ጺም ተወለደ’ የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ታይተዋል። የህክምና ሳይንስ ግን ‘ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን?’ ለሚለው ጥያቄ ከምናስበው በላይ አስደናቂ ምላሽ አለው። ከእድሜያቸው በላይ ያረጁ የሚመስሉ ህጻናትን ገጽታ የሚፈጥሩ ብርቅዬ የጤና እክሎች ምንድን ናቸው? ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 33 min read


የፌስቱላ ስውር ስቃይ እና ተስፋው
የወሊድ ፊስቱላ የአካል ስቃይ ብቻ ሳይሆን የእናቶችን ክብርና ማኅበራዊ ሕይወት የሚያናጋ የዝምታ ሸክም ነው።በሽታው በተራዘመ ምጥ፣ በሕፃናት ጋብቻ እና በአገልግሎት እጦት የሚከሰት ከባድ የእናቶች ጤና ችግር ነው። ይህ ጽሑፍ የበሽታውን ምንነት፣ መንስኤዎቹን፣ ምልክቶቹን፣ የሚያስከትላቸውን ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የመከላከልና የሕክምና አማራጮችን በቀላሉ ያብራራል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jun 154 min read


ስለ ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ ማወቅ ያለብሽ?
ድንገት ኮንዶም ተቀደደ? ወይም መከላከያሽን ረሳሽ? ያልታሰበ እርግዝና ከመፈጠሩ በፊት መከላከል ይቻላል። በዚህ ጽሁፍ "ፖስት ፒል" ወይም ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እርግዝና ከመፈጠሩ በፊት እንዴት እንደሚከላከል፣ አይነቶቹን እና የተሳሳቱ አመለካከቶችን ከሳይንሳዊ እውነታ ጋር አዛምዶ ያነሳል። ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Mar 223 min read


ልቧ ከሷ ቀድሞ ዝሎ ነበር! የራሂማ ታሪክ
በኢትዮጵያ ብዙዎች በለጋ እድሜያቸው የልጅነት ደስታን በሚነጥቃቸው የልብ ቧንቧ በሽታ ይጠቃሉ። ይህም ካልታከመ የጉሮሮ ህመም የሚነሳው ሲሆን ፤ በተለይም የሚትራል ቧንቧን (Mitral Valve) ይጎዳል። የዚህ ቧንቧ ችግር ሴቶችን በይበልጥ ያጠቃል።። እውነተኛ ታሪክን፣ ከሳይንስ ጋር አጣምሮ የያዘው ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ። የልብ ቧንቧ በሽታ መንስኤዎችን፣ ምልክቶችን እና የመከላከያ መንገዶችን በግልጽ ያቀርባል።
Zebeaman Tibebu
Mar 184 min read


ከባድ የወር አበባ ህመም ባይሆንስ?
በኢትዮጵያ ከባድ የወር አበባ ህመም ብዙውን ጊዜ እንደ ተፈጥሯዊ ሂደት ተቆጥሮ ችላ ይባላል። ነገር ግን ይህ ህመም 'ኢንዶሜትሪዮሲስ' የተባለና በመውለጃ ዕድሜ ላይ የሚገኙ 10% ሴቶችን የሚያጠቃ የጤና እክል ሊሆን ይችላል። በባህላዊ ጫና እና በግንዛቤ እጥረት ምክንያት የብዙዎችን ጤና እና የመውለድ ዕድል እየቀማ የሚገኘውን የዚህን ህመም ሳይንሳዊ መንስኤዎችና አስፈላጊ ምርመራዎች እና ህክምና ይውቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Mar 85 min read


ሰው ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ አለብዎት?
አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? ይህ የሰውን ሕይወት ለማዳን የሚረዱ ሳይንሳዊ እርምጃዎችን፣ የደረት መጫን (CPR) እርዳታዎችን እና እንደ ሚሪንዳ ማጠጣት ወይም ክብሪት ማሽተት ያሉ ባህላዊ ልምዶችን በዝርዝር ያብራራል። በመጀመሪያዎቹ አራት ወርቃማ ደቂቃዎች ውስጥ የአእምሮ ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ ወሳኝ ጥቆማዎችን ይሰጣል። የሚጥል በሽታ (Seizure) ሲያጋጥም የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ያስረዳል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Mar 44 min read


በእንቅርት ላይ...
ስለ እንቅርት በሽታ ያለዎት ግንዛቤ በቂ ነው ብለው ያስባሉ? ለምንድነው እንቅርት ከ ጨው ማነስ ጋር የሚያያዘው? ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ሴቶች እና ህጻናት ለዚህ በሽታ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው። ስለ እንቅርት በሽታ ምንነት፣ መንስኤዎች ፣ ስርጭት ፣ ተጋላጭነት፣ ምልክቶች ፣ መከላከያ መንገዶች እና ህክምናው ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Oct 31, 20253 min read


ሰሞነኛው ጉንፋን ለምን መጣ?
ሰሞኑን በመዲናችን በአዲስ አበባ ጉንፋን እየተስፋፋ ይገኛል። ይህ ወቅታዊ ጉንፋን ባይሆንስ? ምናልባት ከባድ ቢሆንስ? ለመሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ? ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ለዚህ ሁሉ ምላሽ ይዟል። ስለዚህ ጉንፋን መስፋፋት፣ መነሻ ምክንያቶች፣ አሳሳቢ ምልክቶች፣ መከላከያ ተግባራት፣ ማድረግ ያለብዎ ድርጊቶችና መቆጠብ ስላለብዎ ነገሮች መረጃን አስደግፎ ይዘረዝራል። ሙሉ ጽሁፉን ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Oct 26, 20255 min read


ካንሰር በኢትዮጵያ ፡ ለመሆኑ ዝግጁ ነን?
ካንሰር ድሮ የሀብታም ሀገሮች ችግር ተብሎ ቢታሰብም፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ ብዙዎችን እየቀጠፈ ያለ አንገብጋቢ የጤና ችግር ነው። በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ80,000 በላይ ሰዎች ካንሰር ይታመማሉ፣ ከ50,000 በላይ ህይወታቸውን ያጣሉ። ለመሆኑ ኝ ቆም ብለው ለምን ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? እንዴትስ መከላከል እንደሚቻል ያውቃሉ? እንግዲያውስ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Oct 22, 20255 min read


የሐሞት ጠጠር ምልክቶቹና ህክምናው
'ሀሞት' የሚለው ቃል አብዝተን በተለምዶ የምንጠቀመውም ሲሆን ፤ የሀሞት ጠጠር ግን ጤናን የሚያውክ በሽታ ነው። እነኝህ ከአሸዋ የሚስተካከሉ ጥቃቅን ድንጋዮች የሚያስከትሉት ህመም ፈጽሞ ቀላል አይደለም። ምግብ በተበላ ቁጥር እያገረሽ ጤና ይነሳል። ታድያ ግን ሁሉም የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ምልክት አያሳዩም። ስለ ሀሞት ጠጠር ምንነት፣ ምልክቶቹ፣ መንስኤዎቹ፣ ስርጭቱ፣ ህክምናው እና መከላከያ መንገድ ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 21, 20253 min read


🌱 አዲስ ዓመት ለጤንነትዎ አዲስ ጅማሬ
በአዲስ ዓመት ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መምረጥ ይኖርብዎታል። ምን አይነት ለውጥን ማምጣት እንዳለብዎ ለመረዳት ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 11, 20254 min read


🌸የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ ባይመጣስ?
መቼ ነው የወር አበባ ከመደበኛ ተለወጠ የምንለው? በአለም ዙሪያ ከ 4ት ሴቶች በትንሹ አንዷ በህይወት ዘመኗ ከመደበኛ የተለየ የወር አበባ ታያለች። የወር አበባ ለውጥ ከጀርባ ያለ በሽታን ሊሳይ ይችላል። ሆኖም ግን ብዙ ጊዘ በችልተኝነት የሚታይ ጉዳይ ነው። ታድያ ስለ ወር አበባ ምንነት ፣ መደበኛ ባህሪያት ፣ ከተለምዶ የሚያሳይቸው ለውጦች ፣ መንስኤዎቹ ፣ ምፍትሒዎቹ ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ።
Zebeaman Tibebu
Aug 21, 20253 min read


ትምባሆና የኤሌክትሪክ ሲጋራ ያላቸው የጤና እክል
ከአለም አንጻር ያነሰ ቢሆንም፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሲጋራ ያጨሳሉ። በ10 ሚሊየን የሚቆጠሩ በእጅ አዙር ያጨሳሉ፤ በየአመቱ ቢያንስ 1.3 ሚሊየን ሰዎች በእጅ አዙር በማጨሳቸው ይሞታሉ። አዲስ የመጣው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ደግሞ ይህንን ጥፋት ይጨምራል። ስለ ትምባሆና ኤሌክትሪክ ሲጋራ ጤና እክሎች፣ ስርጭት፣ ሱስ እና ህክምና መፍትሄዎች ለማወቅ ይህን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 13, 20255 min read


🎀 የጡት ካንሰር ምን? በምን? እንዴት? 🎀
የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ ሴቶችን ከሚያጠቁ ካንሰሮች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። የኢትዮጵያ ሴቶችም ከሌላው አለም ቀድመው በጡት ካንሰር እየታመሙ ፤ አርፍደው እየታከሙ ፤ በቶሎ እየሞቱ ይገኛሉ። ይህም በዋነኝነት ከግንዛቤ እጥረት ጋር ይገናኛል። ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ሰለ ጡት ካንሰ ምንነት ፣ አይነቶች፣ መንስኤዎች ፣ ምልክቶች ፣ መከላከያ መንገዶችና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ያብራራል። የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Aug 3, 20254 min read


❗ሾተላይ
ሾተላይ በባል እና ሚስት ደም አለመጣጣም ላይ ተመስርቶ በእርግዝና ወቅት፤ ጽንስን የሚያጠፋ ነው። ሾተላይ መከላከያ መድሐኒት ቢኖረውም ፤ በግንዛቤ ጉድለት የተነሳ፤ አሁንም እናቶች እየተጠቁ ይገኛሉ። ስለ ሾተላይ በሽታ የተሟላ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 31, 20253 min read


የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና መዘዙ
ባብዛኞቻችን ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሰምተናል። ከተለመዱ የባክቴሪያ ህመሞች መሀል ይጠቀሳል። መከላከል የሚቻል ህመም ሆኖ ሳለ በአለም ዙሪያ በየአመቱ 300 ሺ ሰው ያህል በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተነሳ ይሞታል። ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ ስለ ምልክቶቹ ፣ መከላከያ መንገዶቹ እና ተያያዥ መዘዞቹ ለማወቅ ይህን ትምሀርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 13, 20253 min read


የምሽት አይነስውርነት እና ቪታሚን ኤ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማሻሻል ብዙ ጥረቶች እያደረገች ቢሆንም ፤ የቪታሚን ኤ እጥረት አሁንም ተንሰራፍቶ ይገኛል። የምሽት አይነስውርነትም እንዲሁ። ስለ ቪታሚን ኤ እና ስለ ምሽት አይነስወርነትም በይበልጥ ለመረዳት ፤ መንስኤዎቹን፣ መከላከያ መንገዶቹን እና ነባራዊ ሁኔታውን በጥልቀት ለማወቅ ፤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 8, 20254 min read
bottom of page
