top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


ዳቦ ወይም ሌሎች የስንዴ ምግቦች ለምን አንዳንድ ሰዎችን ያሳምማሉ?
ዳቦ ወይም ሌሎች የስንዴ ምግቦችን ከበሉ በኋላ የሆድ መነፋት፣ ተቅማጥ ወይም የሆድ ቁርጠት ይሰማዎታል? ምክንያቱ ሴሊያክ በሽታ (Celiac Disease) ሊሆን ይችላል። ይህ በሽታ ግሉተን በሚባል ፕሮቲን ምክንያት የሚመጣና የትንሹን አንጀት የሚጎዳ ሲሆን፣ ከሆድ ሕመም በተጨማሪ የደም ማነስና አንዳንድ ንጥረ ነገሮች እጥረት ሊያስከትል ይችላል። ምልክቶቹን፣ የምርመራ ዘዴዎቹንና ሕክምናውን ይወቁ!
Zebeaman Tibebu
9 hours ago3 min read


ከማህጸን ውጭ ያለ እርግዝና (Ectopic Pregnancy)፦ መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
እርግዝና ሁልጊዜ በማህጸን ውስጥ ብቻ እንደማይፈጠር ያውቃሉ? አንዳንድ ጊዜ ጽንሱ ከማህጸን ውጭ፤ ብዙውን ጊዜም በወሊድ ቱቦ ውስጥ ሊያድግ ይችላል። ይህ Ectopic Pregnancy ይባላል። በጊዜ ካልታወቀ ለሕይወት አስጊ የሆነ ደም መፍሰስ ሊያስከትል ይችላል። ምልክቶቹን፣ መንስኤዎቹንና የሕክምና አማራጮቹን ለማወቅ ይህን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
3 days ago4 min read


ካንሰር የሚያመጣው ቫይረስ! ብዙዎች የማያውቁት የማህጸን ጫፍ ካንሰር እውነታ
የማህጸን ጫፍ ካንሰር ዋነኛ መንስኤ የሆነው HPV ቫይረስ ምንድነው? እንዴት ይተላለፋል? ሁሉም HPV ካንሰር ያመጣል? ስለ HPV ቫይረስ፣ ምልክቶቹ፣ የምርመራ ዘዴዎች፣ ክትባትና መከላከያ መንገዶች ከዚህ ይማሩ።
Zebeaman Tibebu
Nov 194 min read


የዓይን ግፊት (Glaucoma)፦ ምልክቶቹ፣ መንስኤዎቹ እና ሕክምናው
ዓይንዎ አያምዎትም? ምንም ምልክት የለዎትም፤ ሆኖም የዓይን ብርሃንዎ እየጠፋ ሊሆን ይችላል! ግላኮማ እንዴት እንደሚከሰት፣ ማንን እንደሚያጠቃ እና በጊዜ እንዴት መለየት እንደሚቻል ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Nov 35 min read


የልጅዎ ጭንቅላት ከመጠን በላይ እያደገ ነው? ችላ አይበሉት!
የልጅዎ ጭንቅላት በፍጥነት እያደገ ነው? ይህ ሃይድሮሴፋለስ (Hydrocephalus) የተባለ የአንጎል ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል። ምን እንደሆነ፣ ምልክቶቹንና መቼ የሕክምና እርዳታ መፈለግ እንዳለብዎ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Oct 223 min read


አንድ እግር ብቻ በድንገት ሲያብጥ ምን ማለት ነው?
አንድ እግርዎ ብቻ በድንገት አብጦ ቢያገኙት ምን ያደርጋሉ? ብዙዎች የሚሰሩት ትልቁ ስህተት እግርን ማሸት ሲሆን፤ ይህ ግን ለሕይወት አስጊ ወደሆነው የሳንባ ደም ስር መዘጋት (PE) ሊመራ ይችላል። ይህ በደም ሥሮች ውስጥ የደም መርጋት መፈጠሩን (Deep Vein Thrombosis - DVT) የሚያሳይ ምልክት ሊሆን ይችላል። የዚህን በሽታ ምልክቶች፣ መንስኤዎች እና ሕይወትዎን ለማዳን ፍጹም ማድረግ የሌለብዎትን 3 ወሳኝ ስህተቶች ከዚህ ጽሑፍ ያግኙ።
Zebeaman Tibebu
Oct 194 min read


ስለ ነስር ማወቅ ያለብን እውነታዎች፦ መንስኤው፣ ስህተቶች እና ህይወት አድን እርምጃዎች
ድንገት አንድ ሰው ከአፍንጫው ደም ቢፈስ ምን ያደርጋሉ? "ጭንቅላትህን ወደ ኋላ አዘንብል!" የሚለው የለመድነው ምክር ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የነስር እውነተኛ መንስኤዎችን፣ ማንም ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ 3 ሳይንሳዊ የመጀመሪያ እርዳታዎችን እና ወደ ሕክምና መቼ መሄድ እንዳለብዎ በዝርዝር ይማራሉ።
Zebeaman Tibebu
Oct 124 min read


የሽንት ቀለም ስለ ጤናችን ምን ይነግረናል?
በየቀኑ የምናየው የሽንታችን ቀለም ስለ ጤናችን ምን አይነት ሚስጥር ሊነግረን እንደሚችል ያውቃሉ? ከቀላል ቢጫ እስከ ቀይ እና ብርቱካናማ፣ እያንዳንዱ የሽንት ቀለም የራሱ የሆነ የጀርባ ታሪክ አለው። የሽንትዎ ቀለም ስለ ጤናዎ የሚናገረውን ለመለየት እንደሚችሉ በዚህ ማራኪ ጽሑፍ ውስጥ ይወቁ!
Zebeaman Tibebu
Oct 85 min read


ግማሽ አንጎሏን አጥታ ማስተር የያዘችው ሴት ታሪክ
ግማሽ አንጎሏ ተወግዶ እንዴት መኖር ቻለች? የክሪስቲና ሳንታውዝ አስደናቂ የሕይወት ታሪክ የሰው አንጎል የመላመድ አቅምን (Neuroplasticity) እና ከባድ የአንጎል በሽታ በኋላ የማገገም አቅምን ያሳያል። በ8 ዓመቷ ከRasmussen’s encephalitis ጋር ከባድ የሚጥል በሽታ ያጋጠማት ክሪስቲና፤ የአንጎሏ ግማሽ ከተወገደ በኋላ እንዴት ወደ ትምህርት፣ ሥራ እና ሙሉ ሕይወት መመለስ ቻለች?
Zebeaman Tibebu
Oct 14 min read


🫁 ትንፋሽ ማጠር ሁሉ የሳንባ ችግር ነው?
ትንፋሽ ሲያጥርዎት ወዲያውኑ ሳንባዎን ይጠረጥራሉ? እውነቱ ግን ትንፋሽ ማጠር ሁልጊዜ የሳንባ ችግር አይደለም። ከልብ፣ ከደም፣ ከጭንቀት እና ከሌሎች ሁኔታዎችም ሊመጣ ይችላል። ስለ ትንፋሽ ማጠር የተሟላ ግንዛቤ ይኑርዎ! ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 294 min read


MRI ወይስ CT Scan? የትኛው የተሻለ ነው?
CT ወይስ MRI? የቱ ነው የሚሻል? ብዙዎች MRI ከCT “የላቀ” ምርመራ እንደሆነ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ CT ፈጣን ስለሆነ ይመርጡታል። እውነታው ግን ...... የሁለቱን ሳይንሳዊ ልዩነት፣ የትኛው መሣሪያ ለየትኛው በሽታ ቀዳሚ ምርጫ እንደሆነ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
Sep 94 min read


ሥራዬን እወደዋለሁ ግን መሄድ ሰልችቶኛል፦ ሥራ እና የአእምሮ ጤና
“ሥራዬን እወደዋለሁ… ግን ከእንግዲህ መሄድ አልፈልግም።” ይህ የሰነፍ ሰዎች ሰበብ ሳይሆን፣ በሀገራችን በብዙ የሥራ ዘርፎች ውስጥ በየቀኑ የሚሰማ የጤና እክል ምልክት ነው። በዚህ የሕክምና ጽሑፍ ውስጥ በሥራ ላይ ጭንቀት፣ በሥራ መቃጠል (Burnout) እና በድብርት (Depression) መካከል ያሉትን ወሳኝ ልዩነቶች፣ የዓለምና የሀገራችንን ተጨባጭ ቁጥሮች፣ እንዲሁም መፍትሔዎቹን እንፈትሻለን። ያንብቡ። አእምሮዎን መጠበቅ ሥራዎን መጥላት ሳይሆን ራስዎን መታደግ ነው።
Zebeaman Tibebu
Sep 45 min read


በቀን ስንት ስኳርና ጨው መመገብ አለብን?
በምግባችን ውስጥ ትክክለኛውና ጤናማው የስኳር እና የጨው መጠን ስንት ነው? “እኔማ በሻይ ላይ ስኳር አልጨምርም” ማለት ብቻውን በቂ ዋስትና አይሆንም። እንደ በርበሬ እና ሽሮ ያሉ ባህላዊ ምግቦች ውስጥ አስቀድሞ የሚጨመረውን ስውር ጨው ከግምት በማስገባት፤ በቀን ልንመገበው የሚገባንን ትክክለኛ መጠን ምን ያህል ነው። ለተሻለ ግንዛቤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 14 min read


የጾም ሳይንሳዊ ሚስጥር፡ ሳይንስ ዛሬ የደረሰበት የጤና መፍትሔ
አብዛኞቻችን ጾምን እንጾማለን። አባቶቻችን ከዘመናት በፊት በመንፈሳዊ ጥበብ የኖሩትን ይህንን የጾም በረከት፣ ዛሬ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎ በሳይንስ ተደግፎ መጥቷል። ይህ ዘመናዊ አጿጿም ("Intermittent Fasting") ምንድነው? ለጤናችንስ ያለውን እውነተኛ ፋይዳ ምን ይመስላል?
Zebeaman Tibebu
Aug 255 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


“ይሰማኛል! ግን ቃላቱ አይለዩልኝም?” — በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ የመስማት ችግር ምልክቶች
ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት የሚከሰት ወይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ ብቻ የሚገደብ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። የመስማት ችሎታ ማጣት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው ቀስ በቀስ ነው። በዚህ ጠቃሚ የጤና መመሪያ ውስጥ፣ “ድምፅ እየሰሙ ቃላትን ለመለየት መቸገርን” ጨምሮ በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የቀደሙ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን፣ ዋና ዋና መንስኤዎቻቸውን እና የሕክምና መፍትሔዎችን በዝርዝር እንመረምራለን።
Zebeaman Tibebu
Aug 57 min read


ውሻ ነክሶዎታል? ማወቅ ያለብዎት እውነታዎች!
የውሻ ንክሻን በፍጹም "ቀላል ቁስል" ብለው አይለፉ! የሬቢስ (Rabies) ቫይረስ ምልክት ከመታየቱ በፊት ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ ግን ለሞት ይዳርጋል። ከንክሻ በኋላ ባሉ የመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች መወሰድ ስላለባቸው ወሳኝ እርምጃዎች እና ህይወትን የሚያድኑ የህክምና መንገዶችን ይወቁ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 35 min read


"ማንኮራፋት" የሰላማዊ እንቅልፍ መግለጫ ወይስ የጤና ጠንቅ?
"ማንኮራፋት የጥሩ እንቅልፍ ምልክት ነው" የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ህይወትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥለው ይጠንቀቁ! በምሽት የሚሰማው ይህ ድምፅ የልብ፣ የጭንቅላት ደም መፍሰስ (ስትሮክ) እና ከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤ የሆነው የ«ስሊፕ አፕኒያ» (Sleep Apnea) ስውር ምልክት ሊሆን ስለሚችልበት አስገራሚ እውነታ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 303 min read


በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ የጉበት ቫይረሶች
ሄፓታይተስ ኤ እና ኢ በበዛት በሕጻንነት ዘመን የሚታዩ፤ ጉበትን የሚያጠቁ ቫይረሶች ናቸው። እነኝህ ቫይረሶች በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ የጉበት ሥራን በፍጥነት በማሰናከል እስከ 25% የሞት አደጋ ያስከትላሉ። የበሽታውን ምልክቶቹ፣ መከላከያ መንገዶች፣ ምርመራዎች ፣ ህክምናውን እና መከላከያ መንገዶቹን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 225 min read


የትራኮማ የዓይን በሽታ በኢትዮጵያ:- መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች
በኢትዮጵያ ከ61 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ይህ ጽሑፍ በቀላሉ መከላከል እየተቻለ ብርሃንን በዝምታ ስለሚሰርቀው የትራኮማ የዓይን በሽታ መንስኤዎች፣ ደረጃዎች እና ፍቱን ስለሆነው የዓለም ጤና ድርጅት የ"ሴፍ" (SAFE) መከላከያ ስልት ዝርዝር መረጃዎችን በሚስብ መልክ ያቀርባል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Jul 194 min read
bottom of page
