top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


ጉንፋን ብለው አትዘናጉ! ሳንባ ምች ቢሆንስ?
የሳንባ ምች (Pneumonia) እንደ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ሊጀምር ይችላል። ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ወደ ሳንባ ሲደርስ ሳል፣ ትኩሳት፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል። በኢትዮጵያም የሳንባ ምች ብዙዎችን ለሞት የዳረገ በሽታ ነው። ሳንባ ምች እንዴት እንደሚይዝ፣ ከተለመደ ጉንፋን እንዴት ሊለይ እንደሚችል፣ እራስዎን እንዴት መከላከልና ምልክቶቹ ሲጀምሩ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 184 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


“ይሰማኛል! ግን ቃላቱ አይለዩልኝም?” — በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ የመስማት ችግር ምልክቶች
ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት የሚከሰት ወይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ ብቻ የሚገደብ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። የመስማት ችሎታ ማጣት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው ቀስ በቀስ ነው። በዚህ ጠቃሚ የጤና መመሪያ ውስጥ፣ “ድምፅ እየሰሙ ቃላትን ለመለየት መቸገርን” ጨምሮ በፍጹም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የቀደሙ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን፣ ዋና ዋና መንስኤዎቻቸውን እና የሕክምና መፍትሔዎችን በዝርዝር እንመረምራለን።
Zebeaman Tibebu
Aug 57 min read


"ማንኮራፋት" የሰላማዊ እንቅልፍ መግለጫ ወይስ የጤና ጠንቅ?
"ማንኮራፋት የጥሩ እንቅልፍ ምልክት ነው" የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ህይወትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥለው ይጠንቀቁ! በምሽት የሚሰማው ይህ ድምፅ የልብ፣ የጭንቅላት ደም መፍሰስ (ስትሮክ) እና ከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤ የሆነው የ«ስሊፕ አፕኒያ» (Sleep Apnea) ስውር ምልክት ሊሆን ስለሚችልበት አስገራሚ እውነታ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 303 min read


አፍንጫዎ ሁልጊዜ ተደፍኖ ይሰማዎታል? ጉንፋን ሳይሆን የአፍንጫ እጢ ቢሆንስ?
አፍንጫዎ ለወራት ተደፍኖ ከቆየ፤ ሁልጊዜ ንፍጥ ካለዎት፤ ወይም ሽታ የመለየት አቅምዎ ቀስ በቀስ ከቀነሰ፤ ችግሩ ቀላል ጉንፋን ብቻ ላይሆን ይችላል። ናዛል ፖሊፕ (Nasal Polyp) በአፍንጫና በሳይነስ ውስጥ በሚኖር ሥር የሰደደ መቆጣት የሚፈጠር ካንሰር ያልሆነ እጢ ሲሆን፤ የመተንፈስ ችግር፣ የሽታ መቀነስ፣ የሳይነስ ኢንፌክሽን እና የእንቅልፍ መታወክን ሊያስከትል ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ስለናዛልፖሊፕ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ሕክምና እና መቼ ሐኪም ማየት እንደሚገባ በዝርዝር ቀርቧል። ለበለጠ ግንዛቤ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Jul 273 min read


በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ የጉበት ቫይረሶች
ሄፓታይተስ ኤ እና ኢ በበዛት በሕጻንነት ዘመን የሚታዩ፤ ጉበትን የሚያጠቁ ቫይረሶች ናቸው። እነኝህ ቫይረሶች በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ የጉበት ሥራን በፍጥነት በማሰናከል እስከ 25% የሞት አደጋ ያስከትላሉ። የበሽታውን ምልክቶቹ፣ መከላከያ መንገዶች፣ ምርመራዎች ፣ ህክምናውን እና መከላከያ መንገዶቹን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 225 min read


የትራኮማ የዓይን በሽታ በኢትዮጵያ:- መንስኤዎች፣ ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች
በኢትዮጵያ ከ61 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ይህ ጽሑፍ በቀላሉ መከላከል እየተቻለ ብርሃንን በዝምታ ስለሚሰርቀው የትራኮማ የዓይን በሽታ መንስኤዎች፣ ደረጃዎች እና ፍቱን ስለሆነው የዓለም ጤና ድርጅት የ"ሴፍ" (SAFE) መከላከያ ስልት ዝርዝር መረጃዎችን በሚስብ መልክ ያቀርባል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Jul 194 min read


የመመረዝ አደጋ በኢትዮጵያ፦ የሚያጋጥሙ መርዞች እና መፍትሔዎቻቸው
በኢትዮጵያ በብዛት የሚከሰቱ ድንገተኛ የመመረዝ አደጋዎችን፣ መንስኤዎቻቸውን እና ሕይወት አድን የሆኑ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ መንገዶችን ይረዱ። ሰከንዶች በሚወስኑበት በዚህ የሕክምና ቀውስ ውስጥ ምን ማድረግ እና ምን ማስወገድ እንዳለብዎት ይወቁ። እራስዎን ያዘጋጁ።
Zebeaman Tibebu
Jul 96 min read


ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን? ከማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ጀርባ ያለው እውነት
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ‘አዛውንት የሚመስል ህጻን በጥቁር ጺም ተወለደ’ የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ታይተዋል። የህክምና ሳይንስ ግን ‘ህጻን በእርግጥም አዛውንት መስሎ ሊወለድ ይችላልን?’ ለሚለው ጥያቄ ከምናስበው በላይ አስደናቂ ምላሽ አለው። ከእድሜያቸው በላይ ያረጁ የሚመስሉ ህጻናትን ገጽታ የሚፈጥሩ ብርቅዬ የጤና እክሎች ምንድን ናቸው? ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 33 min read


ህመም ያለመሰማት በሽታ (CIP)፡ ፀጋ ወይስ ርግማን
ህመም አለመሰማት ልዩ ስጦታ ወይስ አሰቃቂ የህክምና ቅዠት? ተፈጥሯዊ የህመም ስሜት እጦት (CIP) የተባለውን እጅግ አልፎ አልፎ የሚታይ ከዘረመል ጋር ተይያዝነት ያለውን በሽታ እናነሳለን። ለምን ህመም ለሰው ልጅ ህልውና ወሳኝ የጥበቃ ዘዴ እንደሆነ በዚህ አስገራሚ የህክምና ጽሑፍ ውስጥ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
May 244 min read


የማሕበራዊ ሚዲያ አብዝቶ መጠቀም ጭንቅላት ላይ ያለው ተጽእኖ
ስልክዎን አብርተው ማለቂያ የሌለውን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ወደ ታች እየሳቡ ለሰዓታት መጥፋት የዕለት ተዕለት ልማድዎ ሆኗል? ይህ ዝም ብሎ የተፈጠረ ስንፍና ሳይሆን፣ የዲጂታል ዓለም አእምሯችንን አወቃቀርና የዶፓሚን (Dopamine) ሆርሞን ፍሰትን እንዴት እንደቀየረው የሚያሳይ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። ይህ ጽሑፍ ማህበራዊ ሚዲያ በትኩረት፣ በእንቅልፍ እና በስነ-ልቦናችን ላይ የሚያመጣውን ጫና (በተለይም በወጣቶች ላይ) በክሊኒካዊ መረጃዎች አስደግፎ ያብራራል። አእምሯችን ላይ የሚከሰተውን የኒውሮ ፕላስቲሲቲ (Neuroplasticity) ለውጥ እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል እና የስልክ አጠቃቀማችንን ሚዛናዊ ለማድረግ የሚረዱ ቀላል የሕክምና ሳይንስ መፍትሔዎችን ዝርዝር ይዟል። ሙሉውን አንብበው የአእምሮዎን ጤና እና ትኩረት ይመልሱ!
Zebeaman Tibebu
May 184 min read


ልጅዎን ያመመው ቀላል ሕመም ነው ወይስ ሌላ?
በብዙ የኢትዮጵያ ቤቶች የሕፃናት ትኩሳትና ሳል የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን አንድ ቀላል ሕመም ወደ አደገኛ ደረጃ መሸጋገሩን እንዴት እናውቃለን? ይህ ጽሁፍ ባህላዊ እውቀትን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር በማቀናጀት ወላጆች የሕመምን መባስ እንዴት እንደሚያውቁ ይጠቁማል። የሳምባ ምችን የሚጠቁሙ አተነፋፈሶች፣ የወባ ስጋት እና የዚንክን አስፈላጊነት ጨምሮ የልጅዎን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ ወሳኝ ነጥቦችን ዝርዝር ይዞ ቀርቧል። ያንብቡት!
Zebeaman Tibebu
Apr 165 min read


ለልጅ ስልክ መስጠት ኦቲዝም ያመጣ ይሆን?
የልጅዎ የንግግር መዘግየት ወይም የአይን ለአይን ግንኙነት መቀነስ ከስልክ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ይሆን? በአዲስ አበባ ቤቶች ውስጥ እየተለመደ የመጣው የ'ዲጂታል ኦቲዝም' ስጋት እና በመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት ውስጥ የሰው ልጅ ግንኙነት ያለው ወሳኝ ሚና ምን እንደሆነ ይረዱ። ቴክኖሎጂን ከልጅዎ እድገት ጋር እንዴት ማመጣጠን እንደሚችሉ የሚረዱ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Mar 304 min read
bottom of page
