top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


ስለ ነስር ማወቅ ያለብን እውነታዎች፦ መንስኤው፣ ስህተቶች እና ህይወት አድን እርምጃዎች
ድንገት አንድ ሰው ከአፍንጫው ደም ቢፈስ ምን ያደርጋሉ? "ጭንቅላትህን ወደ ኋላ አዘንብል!" የሚለው የለመድነው ምክር ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የነስር እውነተኛ መንስኤዎችን፣ ማንም ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ 3 ሳይንሳዊ የመጀመሪያ እርዳታዎችን እና ወደ ሕክምና መቼ መሄድ እንዳለብዎ በዝርዝር ይማራሉ።
Zebeaman Tibebu
7 hours ago4 min read


🫁 ትንፋሽ ማጠር ሁሉ የሳንባ ችግር ነው?
ትንፋሽ ሲያጥርዎት ወዲያውኑ ሳንባዎን ይጠረጥራሉ? እውነቱ ግን ትንፋሽ ማጠር ሁልጊዜ የሳንባ ችግር አይደለም። ከልብ፣ ከደም፣ ከጭንቀት እና ከሌሎች ሁኔታዎችም ሊመጣ ይችላል። ስለ ትንፋሽ ማጠር የተሟላ ግንዛቤ ይኑርዎ! ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 294 min read


በቀን ስንት ስኳርና ጨው መመገብ አለብን?
በምግባችን ውስጥ ትክክለኛውና ጤናማው የስኳር እና የጨው መጠን ስንት ነው? “እኔማ በሻይ ላይ ስኳር አልጨምርም” ማለት ብቻውን በቂ ዋስትና አይሆንም። እንደ በርበሬ እና ሽሮ ያሉ ባህላዊ ምግቦች ውስጥ አስቀድሞ የሚጨመረውን ስውር ጨው ከግምት በማስገባት፤ በቀን ልንመገበው የሚገባንን ትክክለኛ መጠን ምን ያህል ነው። ለተሻለ ግንዛቤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 14 min read


ስለ ጭንቅላት ዕጢ ማወቅ ያለብዎ!
የአንጎል ዕጢ (Brain Tumor) ምንድን ነው? ምልክቶቹስ እንዴት ይታወቃሉ? ብዙዎች “ካንሰር አይደለም” ማለት “ምንም አደጋ የለውም” የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ይህ ጽሑፍ አዲስ የራስ ምታት፣ የእይታ መለወጥና መንቀጥቀጥን ጨምሮ 8 ዋና ዋና የአንጎል ዕጢ ምልክቶችን ያብራራል። በተጨማሪም በሽታው በደም ምርመራ የማይታወቅበትን ምክንያት፣ የ-MRI እና የባዮፕሲ ጥቅምን እንዲሁም ያሉ የሕክምና አማራጮችን ይዘረዝራል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 284 min read


ጉንፋን ብለው አትዘናጉ! ሳንባ ምች ቢሆንስ?
የሳንባ ምች (Pneumonia) እንደ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ሊጀምር ይችላል። ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ወደ ሳንባ ሲደርስ ሳል፣ ትኩሳት፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል። በኢትዮጵያም የሳንባ ምች ብዙዎችን ለሞት የዳረገ በሽታ ነው። ሳንባ ምች እንዴት እንደሚይዝ፣ ከተለመደ ጉንፋን እንዴት ሊለይ እንደሚችል፣ እራስዎን እንዴት መከላከልና ምልክቶቹ ሲጀምሩ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 184 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


ኮሌስትሮል፦ ወዳጅ ወይስ ጠላት? መንስኤዎቹ፣ ምልክቶቹ፣ እና መፍትሔው
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ለዓመታት ሊቆይ ይችላል። ራስዎን ጤነኛ እየተሰማዎትም ቢሆን ኮሌስትሮልዎ ከፍ ሊል ይችላል። ምልክቶችን ከመጠበቅ ይልቅ ምርመራ ማድረግ ለምን አስፈላጊ ነው? ይህንን እና ስለኮሌስትሮል የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 105 min read


ውሻ ነክሶዎታል? ማወቅ ያለብዎት እውነታዎች!
የውሻ ንክሻን በፍጹም "ቀላል ቁስል" ብለው አይለፉ! የሬቢስ (Rabies) ቫይረስ ምልክት ከመታየቱ በፊት ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ ግን ለሞት ይዳርጋል። ከንክሻ በኋላ ባሉ የመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች መወሰድ ስላለባቸው ወሳኝ እርምጃዎች እና ህይወትን የሚያድኑ የህክምና መንገዶችን ይወቁ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Aug 35 min read


የዝሆኔ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይከሰታል? መከላከያ መንገዶቹስ
የዝሆኔ በሽታ (Elephantiasis) በአብዛኛው አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ብዙዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። በሀገራችንም ይህ በሽታ ከትንኝ ንክሻ እና ቀይ አፈር ላይ በባዶ እግር ከመሄድ ጋር ይያዛል። የበሽታውን ምልክቶች፣ የሕክምና አማራጮች እና ራስን የመከላከያ መንገዶችን ይወቁ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 65 min read


ቲማቲም አሜባን ይቀሰቅስ ይሆን? ስለ አሜባ በሽታ እና መከላከያ መንገዶች ይወቁ!
“ቲማቲም አትብላ!"" ሰላጣ ከበላህ አሜባህ ይነሳል።” ይህን ምክር ያልሰማ ኢትዮጵያዊ የለም። ነገር ግን አሜባ ለዓመታት ተኝቶ ኖሮ፤ ቲማቲም ስለበላን ብቻ በድንገት ሊነቃ ይችላልን? ይህንን አስተሳሰብ በሳይንሳዊ ማስረጃ የሚሞግተውን፣ ስለ አሜባ ጥልቅ ግንዛቤ የሚሰጠውን፣ ምልክቶቹንና፣ ትክክለኛውን የአሜባ ሕክምና የሚያሳየውን አዲሱን ጽሑፋችንን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 305 min read


የቢጫ ወባ ክትባት፡ ሳልከተብ ካርዱ ቢኖረኝስ?
በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ዓለም አቀፍ ተጓዦች ትክክለኛውን የየሎ ፌቨር (የቢጫ ወባ) ክትባት ሳይወጉ፤ የሀሰት ቢጫ ካርድ ብቻ በመግዛት ሕይወታቸውን ለከፍተኛ አደጋ ያጋልጣሉ። ይህ ጽሑፍ የቫይረሱን አስከፊ የጤና ስጋቶች፤ የክትባቱን የዕድሜ ልክ ጥቅሞች፤ ከጉዞዎ ምን ያህል ቀናት በፊት መከተብ እንዳለብዎ፤ የጎንዮሽ ጉዳቱን እና የሚመከረውን ውሳኔ አጠናቅሮ ይዟል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jun 185 min read


ዝምተኛው የቆሽት ካንሰር
🚨 የዓይን ቢጫ መሆን፣ ያለ ምክንያት ክብደት መቀነስ፣ የጀርባ ሕመም እና የምግብ ፍላጎት መጥፋት አስተውለዋል? እነዚህ አንዳንድ ጊዜ የቆሽት ካንሰር የመጀመሪያ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ቆሽት ካንሰር “ዝምተኛ ካንሰር” ተብሎ የሚጠራው ለረጅም ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ሊያድግ ስለሚችል ነው። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ። 👇
Zebeaman Tibebu
Jun 115 min read


መጸዳጃ ቤት ውስጥ ማማጥ በጤናችን ላይ የሚያስከትለው ከባድ መዘዝ
ብዙዎቻችን ሽንት ቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓት የመቀመጥ እና የማማጥ ልማድ አለን። ነገር ግን ይህ ቀላል የሚመስል ልማድ ለኪንታሮት፣ ለራስ መሳት፣ ለዓይን ጉዳት ወይም ለድንገተኛ የልብ አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል ያውቃሉ? ማማጥ በሰውነታችን ላይ የሚያመጣውን ድብቅ የሕክምና አደጋ እና ችግሩን የምናስወግድባቸውን 7 ተግባራዊ መንገዶች ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 46 min read


በኢቦላ የሚጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር ወደ 1000 እየተጠጋ ይገኛል።
የኮቪድ-19 እና የኤምፖክስ ወረርሽኞችን ተከትሎ፣ አሁን ደግሞ በኮንጎ እና በኡጋንዳ የተቀሰቀሰው ብርቅዬው የቦንዲቡግዮ ኢቦላ ዝርያ ዓለምን እያሰጋ ይገኛል። ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች በተጠረጠሩበት እና የተለየ ክትባት በሌለው በዚህ ወረርሽኝ ዙሪያ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ልናውቃቸው የሚገቡ ሳይንሳዊ እውነታዎችን፣ ምልክቶችን እና ዓለም አቀፍ የመከላከያ ስትራቴጂዎችን በዝርዝር የሚያቀርብ ማራኪ የሕክምና ጽሁፍ ።
Zebeaman Tibebu
May 284 min read


ዳማከሴ ወይስ ጤና አዳም ፡ የቱ ይሻላል?
በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዳማከሴ እና ጤና አዳም እጅጉን ጥቅም ላይ የሚውሉ የቤት ውስጥ መድሀኒቶች ናቸው። ነገር ግን አንዱ ለመተንፈሻ አካላት፣ ሌላኛው ደግሞ ለምግብ መፈጨት ልዩ 'ባለሙያ' መሆናቸውን ያውቁ ኖሯል? ይህ ጽሑፍ የጥንቱን የኢትዮጵያ የዕፅዋት ጥበብ ከዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ ጋር በማጣመር የሁለቱን እፅዋት ድብቅ ኃይል፣ ጥቅምና አስፈላጊ ጥንቃቄዎች በዝርዝር ያብራራል። 'ተፈጥሯዊ' መሆኑ ብቻውን 'ደህንነቱ የተጠበቀ' እንደማያደርገው ተገንዝበው፤ እነዚህን ውድ እፅዋት እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚችሉ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
May 135 min read


የመርከብ ላይ ወረርሽኝ ፡ አለምን ያሳሰበው የሃንታ ቫይረስ (Hantavirus)
በ2026 በኤም.ቪ ሆንድየስ (MV Hondius) መርከብ ላይ የተቀሰቀሰው የሃንታ ቫይረስ (Hantavirus) ወረርሽኝ ዓለምን አስግቷል። እስከ 50 በመቶ የሞት አደጋ ሊያስከትል የሚችለው የአንዴስ ቫይረስ ከኮቪድ-19 በምን ይለያል? በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የበሽታውን ምልክቶች፤ የሥርጭት መንገዶችን እና ራስዎን ከአይጥ ወለድ በሽታዎች እንዴት እንደሚከላከሉ በዝርዝር ቀርቧል።
Zebeaman Tibebu
May 103 min read


ስለ ሪህ ማወቅ ያለብዎ
ሪህ በአንድ ወቅት "የነገስታት በሽታ" ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የጤና ፈተና ሆኗል። በድንገት ከሚከሰተው የ"እኩለ ሌሊት ጥቃት" ጀምሮ የዘመናዊ አመጋገብ እስከሚያመጣው ተጽዕኖ ድረስ፤ ይህ የሜታቦሊዝም ችግር እንዴት እንደሚከሰት እና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል በዚህ ጽሁፍ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
May 35 min read


ቤተሰብዎን ከአየር ብክለት እንዴት ይጠብቃሉ?
የአየር ብክለት በኢትዮጵያ ለሞት እና ለአካል ጉዳት ሁለተኛው ዋና መንስኤ መሆኑን ያውቃሉ? ይህ ጽሁፍ በአዲስ አበባ የሚታየውን ከፍተኛ የአየር ብክለት መጠን፣ ከተሽከርካሪ ጭስ እና ከቤት ውስጥ ቃጠሎ የሚመጡ የጤና ስጋቶችን በዝርዝር ያብራራል። ጤናማ የመተንፈሻ አካል እንዲኖርዎት በቤት ውስጥ ሊወስዷቸው የሚገቡ ቀላል እርምጃዎች፣ የትራፊክ ሰዓት ጥንቃቄዎች እና በሳይንሳዊ ማስረጃ የተደገፉ የመከላከያ መንገዶችን እዚህ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 244 min read


ጋንግሪን፦ ምልክቶች፣ መንስኤዎች እና መከላከያ መንገዶች
ጋንግሪን ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በዝምታ ነው። መጀመሪያ የጣት መጥቆር፣ ቀጥሎም የማይድን ቁስል ፤ ከዚያም የሕዋሳት መሞት። ይህ ከጊዜ ጋር የሚደረግ የህልውና ትግል ነው። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የጋንግሪን አይነቶችን፣ አደገኛ ምልክቶች እናነሳለን። በኢትዮጵያ ውስጥ ጋንግሪንን ተከትሎ አብዛኛው ጊዜ ለምን አካል እንደሚቆረጥ እንመረምራለን። እውቀት ከመቆረጥ ያድናል፤ ህይወትን ይታደጋል። ዝርዝሩን ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 55 min read


ሰው ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ አለብዎት?
አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? ይህ የሰውን ሕይወት ለማዳን የሚረዱ ሳይንሳዊ እርምጃዎችን፣ የደረት መጫን (CPR) እርዳታዎችን እና እንደ ሚሪንዳ ማጠጣት ወይም ክብሪት ማሽተት ያሉ ባህላዊ ልምዶችን በዝርዝር ያብራራል። በመጀመሪያዎቹ አራት ወርቃማ ደቂቃዎች ውስጥ የአእምሮ ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ ወሳኝ ጥቆማዎችን ይሰጣል። የሚጥል በሽታ (Seizure) ሲያጋጥም የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ያስረዳል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Mar 44 min read
bottom of page
