top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


🌞 የቫይታሚን ዲ እጥረት 13 ወር ፀሀይ ባላት አገር
በምድር ወገብ እየኖርን ፤ ቀጥታ የፀህይ ጨረር እያገኘን እራሱ በኢትዮጵያ ውስጥ የቫይታሚን ዲ እጥረት መጠን ከፍተኛ ነው። ይህም ደግሞ ከገጠር በከተማ ይብሳል። ይህ የአባይን ልጅ... የሆነ ታሪክ የኢትዮጵያ እውነታ ከሆነ ሰነባብቷል። ስለ ቫያታሚን ዲ እጥረት ፣ ምልክቶቹ ፣መከላከያዎቹ እና ነባራዊ ሁኔታ በይበልጥ ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 16, 20253 min read


የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና መዘዙ
ባብዛኞቻችን ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሰምተናል። ከተለመዱ የባክቴሪያ ህመሞች መሀል ይጠቀሳል። መከላከል የሚቻል ህመም ሆኖ ሳለ በአለም ዙሪያ በየአመቱ 300 ሺ ሰው ያህል በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተነሳ ይሞታል። ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ ስለ ምልክቶቹ ፣ መከላከያ መንገዶቹ እና ተያያዥ መዘዞቹ ለማወቅ ይህን ትምሀርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 13, 20253 min read


ከእድሜ ጋር የሚያያዘው የአጥንት መሳሳት ህመም
ወድቆ አለመነሳትን ስለሚያመጣው ፤ ቀላሉን እንቅስቃሴ ወደ አጥንት ስብራት ስለሚለውጠው ፤ አጥንት መሳሳት ምን ያህል ያውቃሉ? በአለም ዙሪያ ከ 50 አመት በላይ ከሆናቸው ሶስት ሴቶች መሀከል አንዷ በዚህ በሽታ የተነሳ የአጥንት ስብራት ያጋጥማታል። በእውነተኛ ታሪክ አዋዝቶ ፤ ስለ አጥንት መሳሳት ፣ መንስኤዎቹ፣ መከላከያ መንገዶቹ እና በኢትዮጵያ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ያነሳልና ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ። ግንዛቤዎን ያስፉ።
Zebeaman Tibebu
Jul 10, 20255 min read


የምሽት አይነስውርነት እና ቪታሚን ኤ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማሻሻል ብዙ ጥረቶች እያደረገች ቢሆንም ፤ የቪታሚን ኤ እጥረት አሁንም ተንሰራፍቶ ይገኛል። የምሽት አይነስውርነትም እንዲሁ። ስለ ቪታሚን ኤ እና ስለ ምሽት አይነስወርነትም በይበልጥ ለመረዳት ፤ መንስኤዎቹን፣ መከላከያ መንገዶቹን እና ነባራዊ ሁኔታውን በጥልቀት ለማወቅ ፤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 8, 20254 min read


🩸 የደም አይነት እና አመጋገብ፡ ሳይንስ ወይስ ተረት ?
የደም አይነትዎ ምንድን ነው? ከአበላልዎ ጋር ይያዛልን? ምን ይመስልዎታል?
መቼም እስከዛሬ ስለደም አይነትና ስለ አመጋገብ ቁርኝት ሰምተዋል። ይህ ሀሳብ በፈረንጆቹ በ90ዎቹ ነው የጀመረው። ታድያ ሳይንስ ስለዚህ ምን ይላል?
በዝርዝር ለማወቅ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 4, 20255 min read


ትኩስ ምግብ በመብላት ስለሚመጣው ካንሰር ያውቃሉ?
ትኩስ ምግብ አዘውትሮ መመገብ በገዳይነታቸው ከሚጠቀሱ ካንሰሮች መሀከል አንዱ ለሆነው ለጉሮሮ ካንሰር ያጋልጣል። በአመጋገብ ባህላችን ደግሞ ለዚህ ያጋልጠናል። ትኩስ ነገርና የጉሮሮ ካንሰር ያላቸውን ቁርኝት ለማወቅ፤ ምልክቶቹን ለመለየት ፤ መከላከያ መንገዶቹን ለመገንዘብ ይህን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 29, 20253 min read


የአስም ህመም በኢትዮጵያ
አስም በትንሹ 10 ሚሌየን ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃ ህመም ሲሆን ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግን የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነው። 80 ፐርሰንት የሚሆነው አስምን ተከትሎ የሚመጣን ሞት መከላከል ይቻላል። ሆኖም ግን አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ስለ አስም ምንነት እና ምልክቶቹ የተሟላ ግንዛቤ ስለሌለው ፤ ታማሚዎች የሚገባቸውን እንክብካቤ አያገኙም።
ስለ አስም ህመም የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 25, 20254 min read


🌿ጤና አዳም ጀርባ ያለው ሳይንስ
ስለ ጤና አዳም ምን ያህል ያውቃሉ? ስሙ እንደሚናገረው በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ፤ ዘመናዊ ህክምና ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። ከጤና አዳም ጀርባ ስላለው ሳይንሳዊ እውነታ ለመረዳት ፤ ይህን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 22, 20254 min read


ሶስት አመት የፈጀው አለም አቀፍ ወረርሽኝ፡🐒 የዝንጀሮ ፈንጣጣ
የዝንጀሮ ፈንጣጣ አለም አቀፍ ወረርሽኝ ከሆነ 3 አመት ተቆጠረ። ኢትዮጵያም እስከ አሁን 14 ሰው ተይዟል።
እርስዎ ግን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምን እንደሆነ እና እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ይህ ጽሁፍ ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶቹን ፣እና መከላከያ መንገዶቹ ያብራራል ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Jun 18, 20253 min read


ትኩረት የሚነፍገው አቅለብላቢው የአእምሮ ህመም (ADHD)
ህጻናትን ሰነፍ ፤ አዋቂዎችን ውጤታማ እንዳይሆኑ ስለሚያደርገው ህመም ያውቃሉ? ይህ ህመም ትኩረት ይነፍጋል ፣ አደብ ያሳጣል። ተማሪዎች ትምህርት እንዲያቋርጡ ፣ ሰነፍ እንዲባሉ ያደርጋል። ስለህመሙ በይበልጥ ለመረዳት ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 15, 20254 min read


እናቶቻችን ለምንድነው በሳንባ ካንሰር እየተጠቁ ያሉት?
የሳንባ ካንስር በአለም ዙሪያ ሲጋራ ማጨስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አጭሰው የማያውቁ እናቶችን አብዝቶ ያጠቃል። የሳንባ ካንሰር የሚያጋጥምበት የእድሜ ክልልም ከሌላው አለም አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ያነሰ ነው። ለምን የሚለውን መልስ ለማወቅ ፤ በዝርዝር ይህን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 10, 20254 min read


አደገኛው የጉበት ቫይረስ ፡ ሔፓታይተስ ቢ
ሄፓታይተስ ቢ በኢትዮጵያ ውስጥ የጉበት ህመም መንስኤዎች ውስጥ ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በሽታውን መከላከል ቢቻልም እስከ 10 ሚሌየን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። ስለዚህ ጉብት ቫይረስ መተላለፊያ ና መከላከያ መንገዶች ያንብቡ። የሚወዷቸውን ከቫይረሱ እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
Jun 2, 20253 min read


የኩላሊት ጠጠር መንስኤዎች እና መከላከያ መንገዶች
የኩላሊት ጠጠር አመጋገቦትን በማስተካከል ሊያሻሽሉት የሚችሉት ህመም ሆኖ ሳለ ብዙ ኢትዮጵያውያን በኩላሊት ጠጠር ህመም ይሰቃያሉ። ህመሙ እንዴት እንደሚመጣ እና እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ለማወቅ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
May 29, 20253 min read


🌿 ሺ ህመም የሚፈራው ቅጠል - ሽፈራው
ሽፈራው በአያቶቻችን ጥበብ ላይ የተመሠረተ ፤ በዘመናዊ ሳይንስ የተረጋገጠ ፤ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተአምረኛ ቅጠል ነው። ስለዚህ ቅጠል ዘመናዊ ህክምና የደረሰበትን የጤና ጠቀሜታ ዘርዝረው ለመረዳት ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
May 25, 20252 min read


የተስፈኛ እናት ፍርሀት ፡ የኦቲዝም ጉዞ በኢትዮጵያ
ባለፉት አመታት ብዙ ለውጥ ቢታይም ፤ የኦቲዝም ህመም አሁንም በኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ አለው። የሚያስፈልገውን እገዛ ማግኘትም አታካች ነው። ለዚህም ቤተሰቦች ብዙ ውጣ ውረድ ያሳልፋሉ። የዚህ ጽሁፍ ባለታሪክ እናትም እውነታ ይሄ ነው። ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
May 19, 20255 min read


ለብርድ ህመም ፍቱን መድሐኒቱን ያውቃሉ?
የብርድ ህመም ምንድነው? ሳይንስ እንደሚለው ብርድ የሚባል በሽታ ከሌለ ለምን ቀዝቃዛ አየር ሲነካው ሰዉ ያመዋል? እውነት ሰውነቱ ውስጥ ቀዝቃዛ አየር ገብቶ ወይስ? ከብርድ ህመም ምንነት እስከ መድሐኒቱ እናነሳለን። ያንብቡ
Zebeaman Tibebu
May 13, 20253 min read


የጭንቀት ህመም ጉዳይስ?
ይህ ጽሁፍ ከዚህ በፊት ተዘጋጅቶ በነበረው ፤ የራስ ማጥፋት ጽሁፍ ላይ በተሰጡ ምላሾች ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው። በዚህ ጽሁፍ የመንፈስ ጭንቀትን ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶችን እናነሳለን። በመንፈስ ጭንቀት ነባራዊ ሁኔታ እና መፍትሔዎቹ ዙሪያ በደንብ እንወያያለን። በመንፈስ ጭንቀት ዙሪያ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሚሰጥ ነው።
Zebeaman Tibebu
May 5, 20253 min read


የስትሮክ ህመም ነባራዊ ሁኔታ
ስትሮክ በድንገት የሚደርስ ፣ ህይወትን የሚለውጥ እና እየተስፋፋ ያለ ህመም ነው። በኢትዮጵያም ቀዳሚ የሞት ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳል። በዚህ ጽሑፍ ስትሮክ ምንድነው፣ አይነቶቹ ምንድናቸው እና ትኩረት ለምን እንደሚያስፈልግ እናነሳለን።
Zebeaman Tibebu
Apr 28, 20254 min read


አካል ጉዳት እና ግንዛቤው - 2
ባልታሰበ ክስተት ወይም ባልታከመ ህመም ሁላችንም አካላዊ ጉዳት የማጋጠም እድል አለን። ካልተጠነቀቅን አካል ጉዳተኝነት የሁላችንም እጣፈንታ ነው። በታሪክ አዋዝተን ስለ አካል ጉዳተኝነት ፣ መንስኤዎቹ ፣ መከላከያ መንገዶቹ ፣ ስለነባራዊ ሁኔታው እና ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ጉዳዮች በጥልቅ እናነሳለን።
Zebeaman Tibebu
Apr 27, 20254 min read


የተረሳ ህይወት፡ የመርሳት ህመም በኢትዮጵያ
የሰው ፊት አይተው ፣ እላይ ታች ብለው፣ ገስጸውና መክረው ያሳደጉ አባቶች እና እናቶች መስዕዋት የከፈሉላቸውን ልጆቹቸውን ሲረሱ ፤ ያቀኑት ጎጆ ሲጠፋባቸው ማየት እጅግ ያሳዝናል። በዚህ ጽሁፍ ስለ ዲመንሺያ /መርሳት ህመም ምልክቶቹ፣ መከላከያዎቹ እና ኢትዮጵያ ላይ ስላለው እውነታ እንወያያለን። ስለ ህመሙ በጥልቀት ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 21, 20254 min read
bottom of page
