top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


🫁 ትንፋሽ ማጠር ሁሉ የሳንባ ችግር ነው?
ትንፋሽ ሲያጥርዎት ወዲያውኑ ሳንባዎን ይጠረጥራሉ? እውነቱ ግን ትንፋሽ ማጠር ሁልጊዜ የሳንባ ችግር አይደለም። ከልብ፣ ከደም፣ ከጭንቀት እና ከሌሎች ሁኔታዎችም ሊመጣ ይችላል። ስለ ትንፋሽ ማጠር የተሟላ ግንዛቤ ይኑርዎ! ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 294 min read


መንጋጋ መቆለፍ ብቻ አይደለም! ስለ ቴታነስ ማወቅ ያለብዎት እውነታ
አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክቶችን እና ሕይወት አድን የመከላከያ መንገዶችን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Aug 134 min read


አፍንጫዎ ሁልጊዜ ተደፍኖ ይሰማዎታል? ጉንፋን ሳይሆን የአፍንጫ እጢ ቢሆንስ?
አፍንጫዎ ለወራት ተደፍኖ ከቆየ፤ ሁልጊዜ ንፍጥ ካለዎት፤ ወይም ሽታ የመለየት አቅምዎ ቀስ በቀስ ከቀነሰ፤ ችግሩ ቀላል ጉንፋን ብቻ ላይሆን ይችላል። ናዛል ፖሊፕ (Nasal Polyp) በአፍንጫና በሳይነስ ውስጥ በሚኖር ሥር የሰደደ መቆጣት የሚፈጠር ካንሰር ያልሆነ እጢ ሲሆን፤ የመተንፈስ ችግር፣ የሽታ መቀነስ፣ የሳይነስ ኢንፌክሽን እና የእንቅልፍ መታወክን ሊያስከትል ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ስለናዛልፖሊፕ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ሕክምና እና መቼ ሐኪም ማየት እንደሚገባ በዝርዝር ቀርቧል። ለበለጠ ግንዛቤ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Jul 273 min read


የመመረዝ አደጋ በኢትዮጵያ፦ የሚያጋጥሙ መርዞች እና መፍትሔዎቻቸው
በኢትዮጵያ በብዛት የሚከሰቱ ድንገተኛ የመመረዝ አደጋዎችን፣ መንስኤዎቻቸውን እና ሕይወት አድን የሆኑ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ መንገዶችን ይረዱ። ሰከንዶች በሚወስኑበት በዚህ የሕክምና ቀውስ ውስጥ ምን ማድረግ እና ምን ማስወገድ እንዳለብዎት ይወቁ። እራስዎን ያዘጋጁ።
Zebeaman Tibebu
Jul 96 min read


የዝሆኔ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይከሰታል? መከላከያ መንገዶቹስ
የዝሆኔ በሽታ (Elephantiasis) በአብዛኛው አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ብዙዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። በሀገራችንም ይህ በሽታ ከትንኝ ንክሻ እና ቀይ አፈር ላይ በባዶ እግር ከመሄድ ጋር ይያዛል። የበሽታውን ምልክቶች፣ የሕክምና አማራጮች እና ራስን የመከላከያ መንገዶችን ይወቁ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ። ይህን ጽሁፍ ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jul 65 min read


የፌስቱላ ስውር ስቃይ እና ተስፋው
የወሊድ ፊስቱላ የአካል ስቃይ ብቻ ሳይሆን የእናቶችን ክብርና ማኅበራዊ ሕይወት የሚያናጋ የዝምታ ሸክም ነው።በሽታው በተራዘመ ምጥ፣ በሕፃናት ጋብቻ እና በአገልግሎት እጦት የሚከሰት ከባድ የእናቶች ጤና ችግር ነው። ይህ ጽሑፍ የበሽታውን ምንነት፣ መንስኤዎቹን፣ ምልክቶቹን፣ የሚያስከትላቸውን ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የመከላከልና የሕክምና አማራጮችን በቀላሉ ያብራራል። ያንብቡ!
Zebeaman Tibebu
Jun 154 min read


ዝምተኛው የቆሽት ካንሰር
🚨 የዓይን ቢጫ መሆን፣ ያለ ምክንያት ክብደት መቀነስ፣ የጀርባ ሕመም እና የምግብ ፍላጎት መጥፋት አስተውለዋል? እነዚህ አንዳንድ ጊዜ የቆሽት ካንሰር የመጀመሪያ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ቆሽት ካንሰር “ዝምተኛ ካንሰር” ተብሎ የሚጠራው ለረጅም ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ሊያድግ ስለሚችል ነው። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ። 👇
Zebeaman Tibebu
Jun 115 min read


ስለ እምብርት ኸርኒያ ማወቅ ያለብዎ?
እምብርትዎ አካባቢ ድንገተኛ እብጠት አስተውለዋል? ወይስ በሕፃን ልጅዎ ላይ አይተውት ተጨንቀዋል? ይህ እብጠት በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው "የእምብርት ኸርኒያ (Umbilical Hernia)" ምልክት ሊሆን ይችላል። ችግሩ በሕፃናትና በአዋቂዎች ላይ ለምን ይከሰታል? መቼስ ነው አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው? ስለ ምልክቶቹ፣ መንስኤዎቹ እና መፍትሔዎቹ ከዚህ ጽሑፍ ዝርዝር ግንዛቤ ያግኙ።
Zebeaman Tibebu
Jun 84 min read


ህመም ያለመሰማት በሽታ (CIP)፡ ፀጋ ወይስ ርግማን
ህመም አለመሰማት ልዩ ስጦታ ወይስ አሰቃቂ የህክምና ቅዠት? ተፈጥሯዊ የህመም ስሜት እጦት (CIP) የተባለውን እጅግ አልፎ አልፎ የሚታይ ከዘረመል ጋር ተይያዝነት ያለውን በሽታ እናነሳለን። ለምን ህመም ለሰው ልጅ ህልውና ወሳኝ የጥበቃ ዘዴ እንደሆነ በዚህ አስገራሚ የህክምና ጽሑፍ ውስጥ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
May 244 min read


ዳማከሴ ወይስ ጤና አዳም ፡ የቱ ይሻላል?
በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዳማከሴ እና ጤና አዳም እጅጉን ጥቅም ላይ የሚውሉ የቤት ውስጥ መድሀኒቶች ናቸው። ነገር ግን አንዱ ለመተንፈሻ አካላት፣ ሌላኛው ደግሞ ለምግብ መፈጨት ልዩ 'ባለሙያ' መሆናቸውን ያውቁ ኖሯል? ይህ ጽሑፍ የጥንቱን የኢትዮጵያ የዕፅዋት ጥበብ ከዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ ጋር በማጣመር የሁለቱን እፅዋት ድብቅ ኃይል፣ ጥቅምና አስፈላጊ ጥንቃቄዎች በዝርዝር ያብራራል። 'ተፈጥሯዊ' መሆኑ ብቻውን 'ደህንነቱ የተጠበቀ' እንደማያደርገው ተገንዝበው፤ እነዚህን ውድ እፅዋት እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚችሉ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
May 135 min read


ስለ ሪህ ማወቅ ያለብዎ
ሪህ በአንድ ወቅት "የነገስታት በሽታ" ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የጤና ፈተና ሆኗል። በድንገት ከሚከሰተው የ"እኩለ ሌሊት ጥቃት" ጀምሮ የዘመናዊ አመጋገብ እስከሚያመጣው ተጽዕኖ ድረስ፤ ይህ የሜታቦሊዝም ችግር እንዴት እንደሚከሰት እና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል በዚህ ጽሁፍ ይረዱ።
Zebeaman Tibebu
May 35 min read


ሙዚቃ እና ጤና
ሙዚቃ ዝም ብሎ መዝናኛ ነው ወይስ ባዮሎጂያዊ ፍላጎት? ከልብ ትርታ መረጋጋት ጀምሮ አእምሮን እስከ ማደስ ድረስ ፤ ሙዚቃ እንዴት እንደ ተፈጥሯዊ የህመም ማስታገሻና የበሽታ መከላከል አቅም ማጠናከሪያ እንደሚያገለግል ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ይወቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 205 min read


ከባድ የወር አበባ ህመም ባይሆንስ?
በኢትዮጵያ ከባድ የወር አበባ ህመም ብዙውን ጊዜ እንደ ተፈጥሯዊ ሂደት ተቆጥሮ ችላ ይባላል። ነገር ግን ይህ ህመም 'ኢንዶሜትሪዮሲስ' የተባለና በመውለጃ ዕድሜ ላይ የሚገኙ 10% ሴቶችን የሚያጠቃ የጤና እክል ሊሆን ይችላል። በባህላዊ ጫና እና በግንዛቤ እጥረት ምክንያት የብዙዎችን ጤና እና የመውለድ ዕድል እየቀማ የሚገኘውን የዚህን ህመም ሳይንሳዊ መንስኤዎችና አስፈላጊ ምርመራዎች እና ህክምና ይውቁ። ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Mar 85 min read


ሰው ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ አለብዎት?
አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቆ ሲያገኙ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? ይህ የሰውን ሕይወት ለማዳን የሚረዱ ሳይንሳዊ እርምጃዎችን፣ የደረት መጫን (CPR) እርዳታዎችን እና እንደ ሚሪንዳ ማጠጣት ወይም ክብሪት ማሽተት ያሉ ባህላዊ ልምዶችን በዝርዝር ያብራራል። በመጀመሪያዎቹ አራት ወርቃማ ደቂቃዎች ውስጥ የአእምሮ ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ ወሳኝ ጥቆማዎችን ይሰጣል። የሚጥል በሽታ (Seizure) ሲያጋጥም የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ያስረዳል። ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Mar 44 min read


🔥ስለ ጨጓራ ቁስለት ማወቅ ያለብዎ ነገሮች?
በኢትዮጵያ ብዙዎች "ጋስትራይተስ ነው" ብለው ችላ የሚሉት የላይኛው ሆድ ማቃጠል፣ ለካ ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥል የውስጥ ቁስል ሊሆን ይችላል። የጨጓራ እና የትንሹ አንጀት ቁስል ልዩነታቸው ምንድን ነው? የትኛው ነው ምግብ ሲበሉ የሚሻለው? ስለ ጨጉራ ቁስለት አደገኛ ውስብስብ ችግሮች እና ሳይንሳዊ የፈውስ መንገዶች ዝርዝር ለመረዳት ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Mar 13 min read


ዳማከሴ እውነት ያድናል? ሳይንስ ምን ይላል?
ዳማከሴ (Ocimum lamiifolium) በኢትዮጵያ ለዘመናት በባህላዊ ህክምና ያገለገለ ተክል ነው። ነገር ግን ሳይንስ ምን ይላል? ይህ ጽሁፍ በዳማከሴ ውስጥ ያሉ ፋይቶኬሚካሎች፣ የሙቀት መቀነሻ አቅሙ፣ የስኳር ቁጥጥር ባህሪው እና የፀረ-ባክቴሪያ ተፅእኖውን በጥናቶች መሰረት ያቀርባል። ግንዛቤዎን ለማስፋት ያንብቡት
Zebeaman Tibebu
Feb 164 min read


የታችኛው ጀርባ ህመም ምንድነው? ለምን ይመጣል?
የጀርባ ህመም ሁልጊዜ በአደጋ አይጀምርም።
ከረዥም ሰአት መቀመጥ፣ መቆም ወይም ከባድ ስራ በኋላ በዝምታ ሊጀምር ይችላል። ሆኖም ብዙ ጊዜ ችላ ይባላል። ስለ ታችኛው የጀርባ ህመም በጥልቅ ይወቁ! ምልክቶቹን ፣ መንስኤዎቹን፣ ህክምናዎቹና መከላከያዎቹን ይለዩ። ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Feb 83 min read


የህመም ማስታገሻ እና የኩላሊት ጠንቁ
ብዙ ሰዎች ህመም ሲሰማቸው አይቡፕሮፌን ወይም ዳይክሎፌናክ ይወስዳሉ። እነዚህ መድሀኒቶች በፈጣን እፎይታ ቢሰጡም ፣ ዘርፈ ብዙ ተጓዳኝ ጉዳት አላቸው። ኩላሊት ድክመትም ሊያመጡ ይችላሉ። እንዴት? ለምን? ማንስ ተጋላጭ ነው? ምንስ ያድርጉ የሚለውን ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Dec 11, 20253 min read
bottom of page
