top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ፡ማድረግ ያለብዎ እና የሌለብዎ
ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያ አንድ ግለሰብ ሲወድቅ ወይም በመንገድ ላይ አደጋ ሲያጋጥመው፣ ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ አያውቁም። አንዳንድ ክብሪት ለኩሶ ያስሸትታል ፤ ሌሎች ውሃ ይጠጣሉ። ግን ይህ ከመጥቀም ሊጎዳ ይችላል። ትክክለኛ መጀመሪያ እርዳታ ማወቅ ሕይወት የሚያድን ችሎታ ነው። በጥልቀት ለማረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 30, 20254 min read


🦴 ስብራት ወይስ ውልቃት?
ስብራት እና ውልቃት ተመሳሳይ ሊመስሉ ይችላሉ። ሆኖም ፈጽሞ ይለያያሉ። ህክምናቸውም እንዲሁ። ታድያ ግን ጥቂት የማይባሉ ታካሚዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ምርመራ ሳያደርጉ ፤ ውልቃት/ስብራት ነው ተብለው በወጌሻ ሲታከሙ ይቆያሉ። ታድያ ይህ ደግሞ ብዙ ዳፋ አለው። ስለ ስብራት እና ውልቃት ምንነት ፣ ምልክቶች ፣ ባህላዊ አረዳዶች፣ ህክምና እና ስርጭት በጥልቀት ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 25, 20254 min read


የሐሞት ጠጠር ምልክቶቹና ህክምናው
'ሀሞት' የሚለው ቃል አብዝተን በተለምዶ የምንጠቀመውም ሲሆን ፤ የሀሞት ጠጠር ግን ጤናን የሚያውክ በሽታ ነው። እነኝህ ከአሸዋ የሚስተካከሉ ጥቃቅን ድንጋዮች የሚያስከትሉት ህመም ፈጽሞ ቀላል አይደለም። ምግብ በተበላ ቁጥር እያገረሽ ጤና ይነሳል። ታድያ ግን ሁሉም የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ምልክት አያሳዩም። ስለ ሀሞት ጠጠር ምንነት፣ ምልክቶቹ፣ መንስኤዎቹ፣ ስርጭቱ፣ ህክምናው እና መከላከያ መንገድ ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 21, 20253 min read


ራሰ በራነት እንዴት ያጋጥማል? እንዴት እንከላከል?
ራሰ በራነት ፀጉርን ማጣት ብቻ አይደለም ። ከ ባህል ጋር ቁርኝት ያለው በራስ መተማመንን የሚፈትን ነዉ። ስለ ራሰ በራነት ምንነት ፣ ስርጭት ፣ መንስኤና መፍትሔ በጥልቀት ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Sep 15, 20255 min read


የልጅዎ ሽፍታ አሳሳቢ መሆኑን እንዴት ይወቁ?
በመጀመሪያ አመት እድሜ ከተለመዱ ህመሞች ውስጥ ሽፍታ ተጠቃሽ ነው። ብዙውን ጊዜ እነኝህ ህጻናት የሚያሳዩት ሽፍታ የሚያሳስብ ባይሆንም ፤ አንዳንዴ ግን የከባድ ጤና ችግር አመላካች ይሆናል። ወላጆች እና ሞግዚቶች ተራው እያስጨነቃቸው ፤ አሳሳቢውን ችላ እያሉ ሊታዩ ይችላል። ለዚህም መለየት አስፈላጊ ነው። ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ በመጀመሪያ አመት የሚያጋጥሙ የሽፍታ ህመሞችን እንዴት መለየት እንደሚቻል ፤ በምን እንደሚከሰቱ ፤ እንዲሁም አሳሳቢ ምልክቶችን ከነመከላከያ መንገዶች ይጠቅሳል። ያንብቡት !
Zebeaman Tibebu
Sep 2, 20254 min read


አለርጂ አለብዎ? እንዴት አወቁ?
ብዙዎች አለርጂ አለብኝ ከሚለው ቃል ባሻገር ፤ ስለ አለርጂ የተሟላ ግንዛቤ የላቸውም። አለርጂን ለመከላከል ደግሞ ይህ ግንዛቤ እጅጉን አስፈላጊ ነው። አለርጂ የሰውነት መቆጣት ሲሆን ፤ በተለያዩ ቀስቃሽ አካላት ሊነሳ ይችላል። በአለም ዙሪያም ስርጭቱ እየጨመረ እየመጣ ይገኛል። ስለ አለርጂ ምንነት ፣ አይነቶች፣ ቀስቃሽ አካላት፣ ምልክቶች፣ መከላከያ መንገዶች፣ እንዲሁም ስርጭት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 28, 20255 min read


ስለ ማይግሬን ራስምታት ማወቅ ያለብዎ
ማይግሬን ራስ ምታት ብቻ አይደለም። የ የማቅለሽለሽ/የማስታወክ፣ የእይታ መረበሽ፣ ድምጽ/ብርሀን አለመቻል የሚያስከትል ውስብስብ የነርቭ በሽታ ነው። በዓለም ዙሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ሰዎችን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ10 ጎልማሶች መካከል አንዱን እንደሚያጠቃ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህ ጽሁፍ ስለማይግሬን ምንነት፣ ስርጭት፣ ምልክቶች፣ መንስኤዎች፣ የህክምና አማራጮች እና የመከላከያ ዘዴዎች ያብራራል። ያንንቡ፤ ግንዛቤዎን ያሻሽሉ።
Zebeaman Tibebu
Aug 25, 20254 min read


🌸የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ ባይመጣስ?
መቼ ነው የወር አበባ ከመደበኛ ተለወጠ የምንለው? በአለም ዙሪያ ከ 4ት ሴቶች በትንሹ አንዷ በህይወት ዘመኗ ከመደበኛ የተለየ የወር አበባ ታያለች። የወር አበባ ለውጥ ከጀርባ ያለ በሽታን ሊሳይ ይችላል። ሆኖም ግን ብዙ ጊዘ በችልተኝነት የሚታይ ጉዳይ ነው። ታድያ ስለ ወር አበባ ምንነት ፣ መደበኛ ባህሪያት ፣ ከተለምዶ የሚያሳይቸው ለውጦች ፣ መንስኤዎቹ ፣ ምፍትሒዎቹ ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ።
Zebeaman Tibebu
Aug 21, 20253 min read


ብጉር እና መከላከያ መንገዶቹ
ብጉር በዓለም ዙሪያ ከ200 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የሚያጠቃ በሽታ ነው። በኢትዮጵያም ከተለመዱ የቆዳ ችግሮች መሀል ይጠቀሳል። ጉዳቱም ከ ቆዳ ችግር አልፎ፣ የራስ መተማመንን ሸርሽሮ፣ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ተጽእኖ አድርጎ፣ የስነልቦና እክል ያመጣል። ስለ ብጉር መንስዔዎች፣ ህክምናዎች፣ መከላከያ መንገዶች ፣ በቤትዎ ማድረግ ስለሚችሏቸው አማራጮች ለማወቅ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ። ግንዛቤዎን ያሻሽሉ።
Zebeaman Tibebu
Aug 17, 20254 min read


ትምባሆና የኤሌክትሪክ ሲጋራ ያላቸው የጤና እክል
ከአለም አንጻር ያነሰ ቢሆንም፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሲጋራ ያጨሳሉ። በ10 ሚሊየን የሚቆጠሩ በእጅ አዙር ያጨሳሉ፤ በየአመቱ ቢያንስ 1.3 ሚሊየን ሰዎች በእጅ አዙር በማጨሳቸው ይሞታሉ። አዲስ የመጣው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ደግሞ ይህንን ጥፋት ይጨምራል። ስለ ትምባሆና ኤሌክትሪክ ሲጋራ ጤና እክሎች፣ ስርጭት፣ ሱስ እና ህክምና መፍትሄዎች ለማወቅ ይህን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 13, 20255 min read


የስኳር በሽታ አስከፊ ዳፋ የሆነው ዲኬኤ
ክትትል ያልተደረገለት ስኳርን ተከትሎ የሚመጣ ሆድ ህመም ለህይወት አስጊ ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ? ይህ ህመም ዲያቤቲክ ኬቶ አሲዶሲስ ይባላል። ከሆድ ህመም ባሻገር ፤ ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት፣ ውህ አብዝቶ መጠጣት እንዲሁም ማቅለሽለሽ ምልክቶቹ ሊሆኑ ይችላሉ። በሰለጠኑ ሀገራት እምብዛም ቢሆንም ፤ በኢትዮጵያ ይህ ህመም እስከ 46 ፐርሰንት እንደሚያጋጥም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስለዚህ ህመም ፣ ምልክቶቹ ፣ መንስኤዎቹ እና መከላከያ መንገዶቹ በይበልጥ ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 10, 20254 min read


When Work Becomes Illness
What if the ache in your back, the breath you struggle to catch, or the fatigue you can’t explain is just your job?
In Ethiopia, thousands silently suffer from work-related illnesses caused by toxic exposure, poor ergonomics, and unsafe conditions. From factory floors to hospital wards, workers face preventable health risks every day—without protection, diagnosis, or justice.
This article exposes the hidden crisis of occupational health in Ethiopia, backed by data, personal
Zebeaman Tibebu
Aug 6, 20255 min read


🎀 የጡት ካንሰር ምን? በምን? እንዴት? 🎀
የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ ሴቶችን ከሚያጠቁ ካንሰሮች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። የኢትዮጵያ ሴቶችም ከሌላው አለም ቀድመው በጡት ካንሰር እየታመሙ ፤ አርፍደው እየታከሙ ፤ በቶሎ እየሞቱ ይገኛሉ። ይህም በዋነኝነት ከግንዛቤ እጥረት ጋር ይገናኛል። ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ሰለ ጡት ካንሰ ምንነት ፣ አይነቶች፣ መንስኤዎች ፣ ምልክቶች ፣ መከላከያ መንገዶችና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ያብራራል። የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Aug 3, 20254 min read


❗ሾተላይ
ሾተላይ በባል እና ሚስት ደም አለመጣጣም ላይ ተመስርቶ በእርግዝና ወቅት፤ ጽንስን የሚያጠፋ ነው። ሾተላይ መከላከያ መድሐኒት ቢኖረውም ፤ በግንዛቤ ጉድለት የተነሳ፤ አሁንም እናቶች እየተጠቁ ይገኛሉ። ስለ ሾተላይ በሽታ የተሟላ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 31, 20253 min read


የማጅራት ገትር ህመም ምልክቶች እና መከላከያዎቹ
ማጅራት ገትር ህመም ሁሉንም የእድሜ ክልል የሚያጠቃ ቢሆንም በይበልጥ በህጻናተ እና በአዛውንት ዘንድ ይታያል። ኢትዮጵያም የዚህ ህመም ወረርሽኝ ደጋግሞ ስለሚያጠቃት ፤ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ ስንሰለት ሀገሮች መሀል ትገኛለች። ከዚህ ህመም እራስዎን ቤተሰብዎንም ለመጠበቅ ፣ ምልክቶቹን እና መከላከያ መንገዶቹን ማወቅ ይኖርብዎታል። የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 27, 20254 min read


🔥 When the Body Rebels?
Autoimmune diseases—where the immune system attacks the body—are rising in Ethiopia, causing chronic symptoms often missed or misdiagnosed. Conditions like lupus, rheumatoid arthritis, and type 1 diabetes affect many, but lack of awareness and testing delay diagnosis. Improving education and access to care is urgent to save lives. Read More
Zebeaman Tibebu
Jul 25, 20253 min read


ከልጣጩ እስከ ፍሬው የሕክምና ጥቅም ያለው ፓፓያ
ፓፓያ ሁሉ ነገሩ የጤና ጠቀሜታ ያለው ፍራፍሬ ነው። ለዚህም በባህላዊ ህክምና ለሆድ መፈጨት ችግር እንዲሁም ለተለያዩ ህመሞች ለዘመናት ጥቅም ላይ ውሏል። ሳይንሳዊ ጥናቶችም ይህንን እያረጋገጡ ይገኛሉ። ስለ ፓፓያ ጤና ጠቀሜታ ሳይንስ ምን ይላል? እንዴትስ አድርገው ቢጠቀሙት ይመረጣል? በዝርዝር ለማወቅ ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 21, 20253 min read


🌞 የቫይታሚን ዲ እጥረት 13 ወር ፀሀይ ባላት አገር
በምድር ወገብ እየኖርን ፤ ቀጥታ የፀህይ ጨረር እያገኘን እራሱ በኢትዮጵያ ውስጥ የቫይታሚን ዲ እጥረት መጠን ከፍተኛ ነው። ይህም ደግሞ ከገጠር በከተማ ይብሳል። ይህ የአባይን ልጅ... የሆነ ታሪክ የኢትዮጵያ እውነታ ከሆነ ሰነባብቷል። ስለ ቫያታሚን ዲ እጥረት ፣ ምልክቶቹ ፣መከላከያዎቹ እና ነባራዊ ሁኔታ በይበልጥ ለመረዳት ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 16, 20253 min read


የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና መዘዙ
ባብዛኞቻችን ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሰምተናል። ከተለመዱ የባክቴሪያ ህመሞች መሀል ይጠቀሳል። መከላከል የሚቻል ህመም ሆኖ ሳለ በአለም ዙሪያ በየአመቱ 300 ሺ ሰው ያህል በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተነሳ ይሞታል። ስለ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ ስለ ምልክቶቹ ፣ መከላከያ መንገዶቹ እና ተያያዥ መዘዞቹ ለማወቅ ይህን ትምሀርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jul 13, 20253 min read


ከእድሜ ጋር የሚያያዘው የአጥንት መሳሳት ህመም
ወድቆ አለመነሳትን ስለሚያመጣው ፤ ቀላሉን እንቅስቃሴ ወደ አጥንት ስብራት ስለሚለውጠው ፤ አጥንት መሳሳት ምን ያህል ያውቃሉ? በአለም ዙሪያ ከ 50 አመት በላይ ከሆናቸው ሶስት ሴቶች መሀከል አንዷ በዚህ በሽታ የተነሳ የአጥንት ስብራት ያጋጥማታል። በእውነተኛ ታሪክ አዋዝቶ ፤ ስለ አጥንት መሳሳት ፣ መንስኤዎቹ፣ መከላከያ መንገዶቹ እና በኢትዮጵያ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ያነሳልና ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ። ግንዛቤዎን ያስፉ።
Zebeaman Tibebu
Jul 10, 20255 min read
bottom of page

