top of page
Blog Post
Stay Updated on Our Blog
Join us every week as we delve into the pressing issues facing the Ethiopian healthcare system. From personal stories of resilience to in-depth analyses of medical treatments like dialysis, our blog sheds light on the challenges and triumphs within the community. Stay informed, get inspired, and learn how you can make a difference in improving healthcare access for all Ethiopians. Don’t miss out on our latest posts—your support can help transform lives!
Your support will help us continue to provide vital medical treatment to those in need. Together, we can make a meaningful difference and help build a healthier future for all.


አፍንጫዎ ሁልጊዜ ተደፍኖ ይሰማዎታል? ጉንፋን ሳይሆን የአፍንጫ እጢ ቢሆንስ?
አፍንጫዎ ለወራት ተደፍኖ ከቆየ፤ ሁልጊዜ ንፍጥ ካለዎት፤ ወይም ሽታ የመለየት አቅምዎ ቀስ በቀስ ከቀነሰ፤ ችግሩ ቀላል ጉንፋን ብቻ ላይሆን ይችላል። ናዛል ፖሊፕ (Nasal Polyp) በአፍንጫና በሳይነስ ውስጥ በሚኖር ሥር የሰደደ መቆጣት የሚፈጠር ካንሰር ያልሆነ እጢ ሲሆን፤ የመተንፈስ ችግር፣ የሽታ መቀነስ፣ የሳይነስ ኢንፌክሽን እና የእንቅልፍ መታወክን ሊያስከትል ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ስለናዛልፖሊፕ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ሕክምና እና መቼ ሐኪም ማየት እንደሚገባ በዝርዝር ቀርቧል። ለበለጠ ግንዛቤ ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
6 days ago3 min read


የመርከብ ላይ ወረርሽኝ ፡ አለምን ያሳሰበው የሃንታ ቫይረስ (Hantavirus)
በ2026 በኤም.ቪ ሆንድየስ (MV Hondius) መርከብ ላይ የተቀሰቀሰው የሃንታ ቫይረስ (Hantavirus) ወረርሽኝ ዓለምን አስግቷል። እስከ 50 በመቶ የሞት አደጋ ሊያስከትል የሚችለው የአንዴስ ቫይረስ ከኮቪድ-19 በምን ይለያል? በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የበሽታውን ምልክቶች፤ የሥርጭት መንገዶችን እና ራስዎን ከአይጥ ወለድ በሽታዎች እንዴት እንደሚከላከሉ በዝርዝር ቀርቧል።
Zebeaman Tibebu
May 103 min read


ቤተሰብዎን ከአየር ብክለት እንዴት ይጠብቃሉ?
የአየር ብክለት በኢትዮጵያ ለሞት እና ለአካል ጉዳት ሁለተኛው ዋና መንስኤ መሆኑን ያውቃሉ? ይህ ጽሁፍ በአዲስ አበባ የሚታየውን ከፍተኛ የአየር ብክለት መጠን፣ ከተሽከርካሪ ጭስ እና ከቤት ውስጥ ቃጠሎ የሚመጡ የጤና ስጋቶችን በዝርዝር ያብራራል። ጤናማ የመተንፈሻ አካል እንዲኖርዎት በቤት ውስጥ ሊወስዷቸው የሚገቡ ቀላል እርምጃዎች፣ የትራፊክ ሰዓት ጥንቃቄዎች እና በሳይንሳዊ ማስረጃ የተደገፉ የመከላከያ መንገዶችን እዚህ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Apr 244 min read


ልጅዎን ያመመው ቀላል ሕመም ነው ወይስ ሌላ?
በብዙ የኢትዮጵያ ቤቶች የሕፃናት ትኩሳትና ሳል የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን አንድ ቀላል ሕመም ወደ አደገኛ ደረጃ መሸጋገሩን እንዴት እናውቃለን? ይህ ጽሁፍ ባህላዊ እውቀትን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር በማቀናጀት ወላጆች የሕመምን መባስ እንዴት እንደሚያውቁ ይጠቁማል። የሳምባ ምችን የሚጠቁሙ አተነፋፈሶች፣ የወባ ስጋት እና የዚንክን አስፈላጊነት ጨምሮ የልጅዎን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ ወሳኝ ነጥቦችን ዝርዝር ይዞ ቀርቧል። ያንብቡት!
Zebeaman Tibebu
Apr 165 min read


“ብርድ መታኝ…” — በእርግጥ “የብርድ በሽታ” አለ?
"ብርድ መታኝ..." የሚለው አባባል በኢትዮጵያ በባህል የታወቀ የህመም ምርመራ ሆኗል። ነገር ግን በርግጥ "የብርድ በሽታ" የሚባል ነገር አለ? ይህ ጽሑፍ በባህላዊው "ብርድ" እና በሳይንሳዊው የጤና እውነት መካከል ያለውን ሚስጥራዊ ግንኙነት ይፈትሻል። በብርድ ጊዜ ለሚታዩ የበሽታ ምልክቶች መንስኤው ቅዝቃዜው ነው ወይስ ሌላ? እውነታውን አሁኑኑ ይወቁ።
Zebeaman Tibebu
Apr 83 min read


ሰዎች በድንገት ለምን ይሞታሉ?
“ትላንት እኮ ደህና ነበር...” — ይህ አረፍተ ነገር በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለሚሰማ ድንገተኛ ሞት የተለመደ ምላሽ ነው። ነገር ግን የሕክምና ሳይንስ ከዚህ ድንገተኛ ክስተት በስተጀርባ እንደ ደም ግፊት፣ ድብቅ የልብ ሕመም እና የደም መርጋት ያሉ በሽታዎችን ይጠቁማል። ይህ ጽሑፍ ለድንገተኛ ሞት ምክንያት የሚሆኑ 5 ዋና ዋና መንስኤዎችን እና በፍጹም ችላ ሊባሉ የማይገቡ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን በዝርዝር ያብራራል።
Zebeaman Tibebu
Mar 115 min read


ታዋቂዋ አርቲስት ለምን ንቅለ ተከላ አስፈለጋት?
ለመሆኑ ስመ ገናናዋ አርቲስት ሴሌና ጎሜዝ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለምን አስፈለጋት? ለአመታት ከ ስራዋ ያስተጓጎላት ከባድ በሽታ ምንድነው? ምልክቶቹስ ምንድናችው? ህክምናውስ ምን ይመስላል? ስለዚህ ሰውነት ራሱን ስለሚያጠቃበት በሽታ በጥልቀት ለመረዳት ፤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Dec 6, 20253 min read


ሰሞነኛው ጉንፋን ለምን መጣ?
ሰሞኑን በመዲናችን በአዲስ አበባ ጉንፋን እየተስፋፋ ይገኛል። ይህ ወቅታዊ ጉንፋን ባይሆንስ? ምናልባት ከባድ ቢሆንስ? ለመሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ? ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ለዚህ ሁሉ ምላሽ ይዟል። ስለዚህ ጉንፋን መስፋፋት፣ መነሻ ምክንያቶች፣ አሳሳቢ ምልክቶች፣ መከላከያ ተግባራት፣ ማድረግ ያለብዎ ድርጊቶችና መቆጠብ ስላለብዎ ነገሮች መረጃን አስደግፎ ይዘረዝራል። ሙሉ ጽሁፉን ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Oct 26, 20255 min read


ካንሰር በኢትዮጵያ ፡ ለመሆኑ ዝግጁ ነን?
ካንሰር ድሮ የሀብታም ሀገሮች ችግር ተብሎ ቢታሰብም፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ ብዙዎችን እየቀጠፈ ያለ አንገብጋቢ የጤና ችግር ነው። በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ80,000 በላይ ሰዎች ካንሰር ይታመማሉ፣ ከ50,000 በላይ ህይወታቸውን ያጣሉ። ለመሆኑ ኝ ቆም ብለው ለምን ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? እንዴትስ መከላከል እንደሚቻል ያውቃሉ? እንግዲያውስ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Oct 22, 20255 min read


አለርጂ አለብዎ? እንዴት አወቁ?
ብዙዎች አለርጂ አለብኝ ከሚለው ቃል ባሻገር ፤ ስለ አለርጂ የተሟላ ግንዛቤ የላቸውም። አለርጂን ለመከላከል ደግሞ ይህ ግንዛቤ እጅጉን አስፈላጊ ነው። አለርጂ የሰውነት መቆጣት ሲሆን ፤ በተለያዩ ቀስቃሽ አካላት ሊነሳ ይችላል። በአለም ዙሪያም ስርጭቱ እየጨመረ እየመጣ ይገኛል። ስለ አለርጂ ምንነት ፣ አይነቶች፣ ቀስቃሽ አካላት፣ ምልክቶች፣ መከላከያ መንገዶች፣ እንዲሁም ስርጭት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 28, 20255 min read


ትምባሆና የኤሌክትሪክ ሲጋራ ያላቸው የጤና እክል
ከአለም አንጻር ያነሰ ቢሆንም፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሲጋራ ያጨሳሉ። በ10 ሚሊየን የሚቆጠሩ በእጅ አዙር ያጨሳሉ፤ በየአመቱ ቢያንስ 1.3 ሚሊየን ሰዎች በእጅ አዙር በማጨሳቸው ይሞታሉ። አዲስ የመጣው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ደግሞ ይህንን ጥፋት ይጨምራል። ስለ ትምባሆና ኤሌክትሪክ ሲጋራ ጤና እክሎች፣ ስርጭት፣ ሱስ እና ህክምና መፍትሄዎች ለማወቅ ይህን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Aug 13, 20255 min read


የአስም ህመም በኢትዮጵያ
አስም በትንሹ 10 ሚሌየን ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃ ህመም ሲሆን ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግን የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነው። 80 ፐርሰንት የሚሆነው አስምን ተከትሎ የሚመጣን ሞት መከላከል ይቻላል። ሆኖም ግን አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ስለ አስም ምንነት እና ምልክቶቹ የተሟላ ግንዛቤ ስለሌለው ፤ ታማሚዎች የሚገባቸውን እንክብካቤ አያገኙም።
ስለ አስም ህመም የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 25, 20254 min read


ሶስት አመት የፈጀው አለም አቀፍ ወረርሽኝ፡🐒 የዝንጀሮ ፈንጣጣ
የዝንጀሮ ፈንጣጣ አለም አቀፍ ወረርሽኝ ከሆነ 3 አመት ተቆጠረ። ኢትዮጵያም እስከ አሁን 14 ሰው ተይዟል።
እርስዎ ግን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምን እንደሆነ እና እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ይህ ጽሁፍ ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶቹን ፣እና መከላከያ መንገዶቹ ያብራራል ያንብቡት።
Zebeaman Tibebu
Jun 18, 20253 min read


እናቶቻችን ለምንድነው በሳንባ ካንሰር እየተጠቁ ያሉት?
የሳንባ ካንስር በአለም ዙሪያ ሲጋራ ማጨስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አጭሰው የማያውቁ እናቶችን አብዝቶ ያጠቃል። የሳንባ ካንሰር የሚያጋጥምበት የእድሜ ክልልም ከሌላው አለም አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ያነሰ ነው። ለምን የሚለውን መልስ ለማወቅ ፤ በዝርዝር ይህን ጽሁፍ ያንብቡ።
Zebeaman Tibebu
Jun 10, 20254 min read


ለብርድ ህመም ፍቱን መድሐኒቱን ያውቃሉ?
የብርድ ህመም ምንድነው? ሳይንስ እንደሚለው ብርድ የሚባል በሽታ ከሌለ ለምን ቀዝቃዛ አየር ሲነካው ሰዉ ያመዋል? እውነት ሰውነቱ ውስጥ ቀዝቃዛ አየር ገብቶ ወይስ? ከብርድ ህመም ምንነት እስከ መድሐኒቱ እናነሳለን። ያንብቡ
Zebeaman Tibebu
May 13, 20253 min read


The Unusual Suspect Behind the Milk Shortage: The Story of አባሰንጋ (aba senga)/ Anthrax
Anthrax, or አባሰንጋ (Aba Senga), is more than a rural livestock disease—it’s a public health threat with real consequences for food security in Ethiopia. This article unpacks how the outbreak affects humans, how contaminated products may enter markets, why outbreaks are seasonal, and what can be done to stop its spread.
Zebeaman Tibebu
Apr 30, 20255 min read


Where Did COVID Go? Tracking a Pandemic in Disguise
COVID-19 may no longer dominate global headlines, but has it truly vanished—or merely slipped beneath our radar? This article traces the historical roots of coronaviruses, revisits past pandemics, and explores why the recent silence around COVID-19 may be misleading. As Ethiopia and the world shift focus to other health challenges, the virus continues its quiet spread. It's time to ask: how do we stay prepared for what may come next?
Zebeaman Tibebu
Apr 23, 20255 min read
bottom of page
