top of page

117 results found with an empty search

  • ትርፍ አንጀት በሽታ: ምልክቶቹ እና አደጋዎቹ

    እስቲ አስቡት ... ተራ ያሉት የሆድ ህመም በድንገት ሲያጣድፍዎ! ሲጀምር መለስተኛ የሆድ ህመም ይመስላል። ህመሙም እምብርት አከባቢ ይሰማል....በሰአታት ውስጥ ህመሙ እየጠነከረ /እየባሰ ይመጣል። ቀስፎ ይይዛል። እምብርትዎ ጋር ያለው ህመም ጋብ ሲል ፤ በቀኝ በኩል ታችኛው ሆድዎ ላይ ቀስሮ ይይዛል! ይህን ህመም ችለው ለማሳለፍ የሚሞክሩ ብዙዎች አሉ። ሆኖም ግን ድንገተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህመሞች ውስጥ አንዱ ነው። ህይወት እስከማጣት ሊያደርስ ይችላል። ይህ ተጓዥ ህመም ፤ አሁንም ችላ ካሉት ፤ ህክምና እርዳታ ካላገኙ ፤ በሰአታት ውስጥ የቀኝ የታችኛውን ሆድ ክፍል ትቶ መላ ሆድን ወጥሮ ይይዛል። ሙሉ ሆድዎ ይደድራል። ህመሙ ከባድ ስለሆነ ሆድም አያስነካም! እዚህ ጋር ሳይደርስ ህክምና ማድረግ ነበረብዎ። አሁን አደገኛ ደረጃ ደርሷል! በህይወት ለመቆየት ያለዎት ሰአታት ሊሆን ይችላል። እጅጉን አፋጣኝ የሆነ ህክምና ያስፈልግዎታል። ፈጽመው እንዳይዘናጉ! እያንዳንዷ ድቂቃ ለእርስዎ ህይወት ዋጋ አላት። አዎ! ቀላል የመሰለ የሆድ ህመም ፤ በድንገት እንዲህ የከፋ ደረጃ ያደርሳል። ይህ የትርፍ አንጀት በሽታ ነው። ብዙዎችም ህመሙን ለይተው ስለማያውቁት ይዘናጋሉ። ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ ዘፋኙዋ ኬሊ ክላርክሰንም ህመሟን ችላ ብላው ነበር። ታሪኩ እንዲህ ነው። ይህች እውቅ ዘፋኝ የአሜሪካ የዘፈን ደረጃ ሰንጠረዥን (ቢል ቦርድን) ሽልማት ፕሮግራምን እንድትመራ በ2019 ተመርጣ ነበር። ታድያ ግን መድረኩን በመራችባቸው ሶስት ሰአታት ውስጥ ከፍተኛ የሆድ ህመም ላይ ነበረች። ህመሙም ቀድም ብሎ የጀመራት ቢሆንም ፤ እምብዝም ቦታ አልሰጠቸውም ነበር። ታድያ መድረኩን በምትመራበት እለት እጅጉን ባሰባት። መደረኩን እንደምንም ብላ ጨርሳ ፤ በአፋጣኝ በሎሳንጀለስ ግዛት በሚገኘውየሴዳር ሳይናይ ሜዲካል ሴንተር ለምርመራ ሄደች። ምርምራውም ትርፍ አንጀት በማሳየቱ ፤ መድረኩን በመራች በማግስቱም ጠዋት ድንገተኛ የቀዶ ህክምና ተደረገላት። በቀጣይ ቀናትም ከበሽታዋ ልታገግም ችላለች። ቆየት ብላ በመሄዷ ግን የማገገም ጊዜዋ የተራዘመ እና እክል የሞላበት ሆኖ ነበር። ታድያ ለ መረጃ ቅርብ ይሆናሉ ብለን የምናስባቸው ታዋቂ ሰዎች እንኳን እንደዚህ ዝንጉ ከሆኑ እርስዎ ላይ ላይፈረድ ይችል ይሆን? ጉዳዩ ግን የመፍረድ አይደለም። ችላ ያሉት የሆድ ህመም ፤ ህይወትዎን ሊያስከፍል ይችላል። ተፈረድብዎ... አልተፈረደብዎ ህመሙን የሚችሉት ፤ የሚሰቃዩት እርስዎ ነዎት። ስለዚህም ዛሬውኑ ግንዛቤዎን ያስፉ። እስቲ ፤ ስለትርፍ አንጀት በጥልቀት እናንሳ። 👉ትርፍ አንጀት ምንድን ነው? ትርፍ አንጀት የትንሹ አንጀት ማብቂያ ፤ የትልቁ አንጀት መጀመሪያ ላይ ፤ እንደ ጉጠት(ወይም ጣት) አፈንግጦ የወጣ የአንጀት ክፍል ነው። ለዚህም ስሙ ትርፍ አንጀት (appendix)ይሰኛል። ይህም ክፍል ስራው ምግብ መፍጨት አይደለም። ይልቁኑ ቅርብ ላይ ያሉ የአንጀት ክፍሎችን የሚጠብቁ ፤ የበሽታ መከላከያ ስርአቶች መከማቻ ስፍራ ነው። እርሱም ብዙ የበሽታ መከላከያ ስርአት ህዋሳት በውስጡ ስላሉት ፤ በቀላሉ ይቆጣል። ቀይ ቀለም መሀከል ያለው እንደ ጅራት አፈንግጦ የወጣው ክፍል ነው ትርፍ አንጀት የሚባለው (በዚህ ምስል ላይ ተቆጥቷል) አንጀት ደግሞ በባህሪው ብዙ በሽታ አምጪ ተህዋሳትን የያዘ የሰውነት ክፍል ነው። ታድያ እነኝህ በሽታ አምጪ ተህዋሳት ወደ ትርፍ አንጀት ከደረሱ ትርፍ አንጀት ይቆጣል። አንዳንድ ጊዜ ደግም በምግብ ቁራጮች ፤ አልያም በአንጀት ተረፈ ምርቶች የትርፍ አንጀት ጫፍ ሊደፈን ይችላል። ይህን ጊዜ ትርፍ አንጀት አብዝቶ ይቆጣል። ይሄኔ ነው የትርፍ አንጀት በሽታ አለ የምንለው። 📊 ስርጭቱ ምን ይመስላል? በአለም ዙሪያ በየአመቱ ወደ 17 ሚሊየን ሰዎች በዚህ በሽታ ይጠቃሉ። ከ10 ሰዎች ውስጥ አንዱም በህይወት ዘመኑ የትርፍ አንጀት በሽታ ያጋጥመዋል ተብሎ ይገመታል። ህሉንም የእድሜ ክልል ሊያም ቢችልም ፤ ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ የሚታየው 10 እስከ 30 አመት እድሜ ያሉ ሰዎች ላይ ነው። ከሴቶችም አንጻር በወንዶች ላይም በብዛት ይስተዋላል። 😣 ችላ ሊሏቸው የማይችሏቸው የተለመዱ ምልክቶች ትርፍ አንጀት ብዙውን ጊዜ ምልክቶቹ ይህን ይመስላሉ። ✔ ሲጀምር እምብርት አከባቢ የሚሰማ መለስተኛ የሆድ ህመም ✔ ከሰአታት በኋላ ይህ የሆድ ህመም በቀኝ በኩል ወደ ታችኛው የሆድ ክፍል ያመራል። (ይህ ህመሙ መባሱን አመላካች ነው።) ✔ ከዚህ የሆድ ህመም ጋርም አብሮ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ የምግብ ፍላጎት ማጣት ትኩሳት /ብርድ ብርድ ማለት ራስ ምታት ቀኝ ታችኛው ሆድ ላይ ሲነካ ማመም ሊኖር ይችላል። ህመሙ ሲባባስም ✔ ሙሉ ሆድ ይደድራል። ✔ ሆድ የማያስነካ እጅጉን ከባድ ህመም ✔  እንዲሁም ራስ መሳት ሊኖር ይችላል። እነኝህን ምልክቶች ካዩ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ። መቼም እንዳይዘናጉ። ህይወትዎን ለማትረፍ ያለዎት ሰአታት ብቻ ሊሆን ይችላል። 🚨 አፋጣኝ ህክምና ለምን ያስፈልጋል? ትርፍ አንጀት በሽታ ቀደም ብሎ ከታከመ በቀዶ ጥገና ወይም አንዳንድ ጊዜ በአንቲባዮቲኮች ሊድን ይችላል። መዘግየት የትርፍ አንጀት መቆጣት እንዲባባስ ያደርጋል። ይህም የተቆጣ ትርፍ አንጀት ሊፈነዳ ይችላል። ሆድ ውስጥ ሲፈነዳ ፤ በሽታውን ያመጡት ባክቴሪያዎች እና የቤዝ ባህሪ ያላቸው የአንጀት ፈሳሾች ወደ ሆድ እቃ ይፈሳሉ። እነኝህም የሆድ እቃ ኢንፌክሽን ያመጣሉ። ሀሞትን ጨምሮ ሌሎች የአንጀት ኬሚካሎችም በራሳቸው የሆድ እቃ መሸፈኛን ያስቆጣሉ። በሽታው እጅጉን ይባባሳል። ባክቴሪያዎችም ከሆድም አልፈው ወደ ደም ውስጥ ይገባሉ። ይህን ጊዜ የደም ውስጥ ኢንፌክሽን ያመጣሉ። ይህም ከፍተኛ የሞት አደጋ ያለው በሽታ ነው። ታድያ ይህ ሁሉ ሳያጋጥም ፤ ቀድሞ ህክምና ቢያደርጉስ? ህይወትዎን አያድኑም? 🔬 የትርፍ አንጀት በሽታን እንዴት ማወቅ ይቻላል? ትርፍ አንጀት በሽታን ለማወቅ በይበልጥ የሚከተሉትን ምርመራዎች ያስፈልጋሉ። ✔ የዶክተር አካላዊ ምርመራ (ይህ ዋነኛውና ፤ እጅግ ጠቋሚ የሆነው ምርመራ ነው።) ✔ ኢንፌክሽን መኖሩን ለመመልከት የሙሉ ደም ምርመራም (CBC) ያስፈልጋል። ለወንዶች እነኝህ ሁለቱ ብቻ በቂ ሊሆኑ ይችላሉ። ለሴቶች እና አንዳንድ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ፤ አልትራሳውንድ ምርመራ ሊታዘዝም ይችላል። 🛠 የህክምና አማራጮቹስ ምን ይመስላሉ? የትርፍ አንጀት በሽታ የሚከተሉት የህክምና አማራጮች አሉት። 🔹 ትርፍ አንጀትን በቀዶ ህክምና ማስወገድ (Appendectomy) ይህ ተመራጩ ህክምና ነው። ይህ የተቆጣውን ትርፍ አንጀት በቀዶ ህክምና በምስሉ እንደሚታየው ቆርጦ ማውጣት ነው። ቀዶ ህክምናውም ቀላል ሲሆን ፤ ታካሚም ቢበዛ በሁለተኛ አልያም ሶስተኛ ቀን ከሆስፒታል አገግሞ ይወጣል። ይህም የቀዶ ጥገና የተለያዩ አይነቶች አሉት። 🔹 የባክቴሪያ መቃወሚያ (አንቲባዮቲክስ) እና የድጋፍ ህክምና አንዳንዴ እንደ ዶክተሩ እይታ ፤ ትርፍ አንጀት የተጠረጠሩ ታካሚዎች ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ፤ አንቲባዮቲክስ እና የድጋፍ ህክምና ሊደረግላቸው ይችላል። ይህ ግን የሚደረገው የቀዶ ጥገና በአፋጣኝ ማድረግ የሚቻልበት ሆስፒታል ውስጥ ብቻ ነው። ይህም ውሳኔ በዶክተሩ ህክምናዊ እይታ ላይ ይወሰናል። 💥 በቀዶ ጥገና ጊዜ ምን ሊያጋጥም ይችላል? የቀዶ ህክምናውን ተከትሎ የሚከተሉት ተጓዳኝ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። እነኝህ ችግሮች የማጋጠም እድላቸው እጅጉን አናሳ ነው። ታድያ ግን ዘግይተው ህክምና እርዳታ ለሚያገኙ ሰዎች ፤ የማጋጠም እድላቸው ያየለ ይሆናል። የተለመዱትም ተጓዳኝ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው። 🔹 የቀዶ ጥገና ቦታ ኢንፌክሽን (በጣም የተለመደ ነው) 🔹 የሆድ ድርቀት ወይም ሆድ ውስጥ የሚከማቹ ፈሳሾች 🔹 አንጀት መስራት ማቆም (ileus) (ይህ ጊዜያዊ ሲሆን ፤ አንጀት ወደ ቀድሞ ስራው ይመለሳል።) 🔹 አርፍደው ሄደው ከሆነ ፤ ደም ውስጥ የተሰራጨ ኢንፌክሽን (sepsis) ሊያጋጥምም ይችላል። 🧠ፈጽሞ ማድረግ የሌለብዎ ነገሮች እነኝህን ፈጽመው እንዳያደርጉ! 👉 ፈጽሞ ችላ አይበሉ። እንደ ቀላል የሆድ ህመም ጀምሮ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ፈጽሞ እንዳይዘናጉ። ከተጠራጠሩ እንኳን ፤ ሳይውሉ ሳያድሩ የሕክምና ዕርዳታ ይፈልጉ። 👉 ምልክቶቹን ካዩ የህመም ማስታገሻ ፈጽሞ እንዳይወስዱ። በሽታውን ደብቀው ህክምናን ያዘገያሉ። ለዚህም ከምርመራ በፊት ህመም ማስታገሻ መውሰድ የተከለከለ ነው። 💡 መቼም እንዳይዘናጉ! የሆድ ህመም ሁሉ ቀላል አይደለም። አንዳንዴ ህይወት ያስክፍላል! ግንዛቤው ህይወታቸውን ሊያድን ይችላልና ፤ በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች ይህንን ትምርታዊ ጽሁፍ ያጋሩ።

  • የታችኛው ጀርባ ህመም ምንድነው? ለምን ይመጣል?

    የጀርባ ህመም ሁልጊዜ በአደጋ አይጀምርም! ድንገት በአዘቦት ቀን ረዥም ሰአት ቆመው ወይም ተቀምጠው ፤ አልያም ከባድ ስራ ሲሰሩ ውለው፤ ምሽት ላይ ከድካምዎ ሊያርፉ ጋደም ሲሉ ፤ ህመሙን ያስተውሉታል። ማረፊያዎ ሰአት ላይ የታችኛው ጀርባዎ ላይ ህመም ይሰማዎታል። መጀመሪያ ላይ ችላ ይሉታል። ምንም አይደለም ብለው ይዘነጉታል። ምናልባትም ድካም ፤ አልያም እድሜ እያሉ ምክንያት ይዘረዝሩለታል። እንደእርስዎ በአለም ዙሪያ በጀርባ ህመም የሚሰቃዩ ከግማሽ ቢሊየን በላይ ሰዎች አሉ። በአለም ዙሪያ ከሚኖሩ 10 ሰዎች ውስጥ ስምንቱ በህይወት ዘመናቸው የጀርባ ህመም እንደሚያጋጥማቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። አብዛዎቹም የበሽታውን መንስኤ እንኳን በቅጡ አያውቁም። ሆኖም ግን እንደሚታሰበው የጀርባ ህመም አንድ በሽታ አይደለም። ሁልጊዜም የዲስክ መንሸራተት አይደለም። የጀርባ ህመም ምንድን ነው? የጀርባ ህመም የሚባለው የአከርካሪ አጥንት ዙሪያ የሚሰማ ህመም ነው። በብዛት ህመሙ የሚስተዋለው ሰውነትን የሚሸከመው የታችኛው ጀርባ (ወገብ )አካባቢ ነው። በዚህም ጽሁፍ የምናነሳው ስለዚህ የታችኛችው የጀርባ ህመም ነው። ይህ ክፍል ከላይ ያለውን ሰውነት ክብደት ችሎ ወደ እግር የሚያስተላልፍ ነው። ለረዥም ሰአት ሲቆሙ ፣ ሲቀመጡ ፣ አንድ አቋም ይዘው ሲቆዩ ፣ ሲታጠፉ ፣ እቃ ሲያነሱ የታችኛው ጀርባዎ አብዝቶ ይሰራል። ከእርሶ እኩል ከፍ ዝቅ ይላል። ለዚህም በእለታዊ እንቅስቃሴዎ ውስጥ ታችኛው ጀርባዎ ላይ ከባድ ጫና ሊያድርበት ይችላል። በጊዜ ውስጥም ሊጎዳ፣ ህመም ሊያመጣ ይችላል። ለዚህም የዚህኛው የጀርባ ክፍል ህመም በርክቶ ይስተዋላል። የጀርባ ህመም ምልክቱም ለየቅሉ ነው። አንዳንዶች ምቾት ማጣት ሲሰማቸው ሌሎች እንቅስቃሴ የሚገድብ ከባድ ህመም ይኖራቸዋል። ህመሙ መውጋት ፣ መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል ፣ መደንዘዝ ፣ ወደ እግር የሚሰራጭ የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል ሊሆን ይችላል። ህመሙ በአንዳንዶች ለጥቂት ቀናት ብቻ ሲቆይ ፤ ሌሎች ለአመታት ይሰቃያሉ። እንቅልፍ ያጣሉ። ስራቸውና ማህበራዊ ኑሮዋቸው ይሰናከላል። የጀርባ ህመም አንድ በሽታ አይደለም የጀርባ ህመም ፈጽሞ አንድ በሽታ አይደለም። የብዙ በሽታዎች ምልክት ነው። ሆኖም ግን ከ 10 የጀርባ ህመም ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ ምንም በሽታ አይገኝባቸውም። የሚደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎችም ጠቋሚ አይሆኑም። ይህ ማለት ግን ህመሙ ምናባዊ ነው ማለት አይደለም። የአከርካሪ አጥንት መጋጠሚያዎች፣ ጅማቶች፣ እና ዲስኮች የሚኖራቸው መስተጻምር ለውጥ ይህን ህመም ሊያመጣ ይችላል። ሆኖም ግን በላብራቶሪ አይስተዋልም። በተረፉት 10 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ላይ ይህ የሚከሰተው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው። የዲስክ መንሸራተትን ተከትሎ በሚመጣ የነርቭ መታፈን የአከርካሪ አጥንት መጥበብ (spinal stenosis) የአከርካሪ አጥንት መሳሳት (በቪታሚን ዲ ማነስ አልያም በሆርሞን ችግሮችም ሊመጣ ይችላል) የአከርካሪ አጥንት መሰበር የአከራክሪ አጥንት መጋጠሚያዎች መቆጣት (spondyloarthritis / ankylosing spondylitis) ኢንፌክሽኖች የህብለሰረሰር አልያም አከርካሪ አጥንት እጢ ወደ አከራካሪ አጥንት የተሰራጨ ካንሰር የጀርባ ህመም አጋላጭ መንስኤዎች? የጀርባ ህመም አጋላጭ በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ከእነኝህ ውስጥ ጥቂቶቹ ረዥም ሰአት መቀመጥ ፣ መቆም፣ አንድ አቁም ይዞ መቆየት ደጋግሞ መታጠፍ ፣ መነሳት በእድሜ ውስጥ የሚመጡ የአከርካሪ አጥንት ለውጦች በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ ውፍረት (ከመጠን በላይ የሰው ክብደት) ሲጋራ ማጨስ(አዎ፣ አከርካሪውንም ይነካል) ናቸው። ከዚህም ባሻገር በእርግዝና ወቅት እናቶች የሚያመጧቸው ለውጦች ጀርባ ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። የመውለጃ እድሜያቸው ያለፉ ሴቶች ደግሞ ፤ አጥንት መሳሳት ስለሚያጋጥማቸው ለጀርባ ህመም ተጋላጭነት አላቸው። ውጥረት፣ ጭንቀት እና ደካማ እንቅልፍ ደግሞ የጀርባ ህመም ን ይበልጥኑ ያባብሳሉ። ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ያደርጉታል። ምን ማድረግ ይመከራል? 👉 የጀርባ ህመም ሕክምናዎች ህመሙን በአንድ ጀምበር "አያስተካክሉም"። እጅጉን አመርቂ ውጤት የሚታየው በጊዜ ውስጥ ነው። በክትትል የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ ይችላል። ለዚህም የሚከተሉት ይመከራሉ። ይንቀሳቀሱ! መለስተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተሻለ ለውጥ ያመጣል። በተለይም ጀርባዎን እንዲያግዝ የጥንካሬ እና የማሳሳብ ስፖርቶችን ይስሩ። እንደ አስፈላጊነቱ ህመም ማስታገሻ ይውሰዱ። የአልጋ ላይ እረፍት ያድርጉ። ጀርባ ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል። ረዥም ሰአት ማረፍ ግን አይመከርም። የጀርባ ደጋፊ ማቀፊያዎችን እንደ ሀኪምዎ ምክር ያድርጉ። የጀርባ ህመምን መከላከል ይቻላል? የጀርባ ህመምን ለመከላከል የሚከተሉትን ያድርጉ። ጀርባን የሚያግዙ ጡንቻዎችን ያጠናክሩ። ትንሽ ይቀመጡ ፣ የበለጠ ይንቀሳቀሱ። ቁመናዎን ያስተካክሉ። ቀጥ ብለው ይቀመጡ። ቀጥ ብለው ይቁሙ። ክብደት ሲያነሱ ይጠንቀቁ። ጤናማ ክብደት ይኑርዎት። ማጨስን ያ ቁሙ። ጭንቀትን ይቆጣጠሩ እና በደንብ ይተኙ። መቼ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ? መለስተኛ የጀርባ ህመም በእንቅስቃሴ እና በመሠረታዊ እንክብካቤ ሊሻሻል ይችላል። ይሁን እንጂ የሚከተሉትን ካስተዋሉ ፈጽሞ ችላ እንዳይሉ። በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ። . ከ2 ሳምንት በላይ እንክብካቤ አድርገውለት ካልተሻልዎት ፤ አልያም እየባሰ ከመጣ ፤ ከጀርባ ተነስቶ ወደ አንድ ወይም ሁለቱም እግሮች ላይ የሚሰራጭ ህመም ከሆነ። በተለይ ህመሙ መደንዘዝ፣ እንደኤሌትሪክ መንዘር እንዲሁም የእግር መስነፍ ካለው፤ ለመራመድ ካስቸገርዎ። የእግሮችውን እንቅስቃሴ ለማዘዝ/ለመቆጣጠር ከከበድዎ ፤ ሽንት እና ሰገራ መቆጣጠር ካቃትዎ (ይህ አፋጣኝ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው በሽታ ምልክት ሊሆን ስለሚችል አይዘግዩ) ፤ ከህመሙ ጋር ትኩሳት፣ ላብ ማጥመቅ እንዲሁም ከፍተኛ ክብደት መቀነስ ካለ ፤ ከህመሙ በፊት አካላዊ ጉዳት ደርሶብዎ ከነበረ ፤ የሚታወቅ ህመም ካለብዎ (ለምሳሌ፡ ሳንባ ነቀርሳ፣ ኤች አይቪ የመሳሰሉት ካለብዎ)፤ የካንሰር በሽታ ካለብዎ ፤ አልያም ከነበረብዎ ፤ ስቴሮይድ ያለባቸው መድሀኒቶችን ለረዥም ጊዜ ከወሰዱ፤ ህመሙ የማያቋርጥ ከሆነ ፤ አቅራቢያዎ ወዳለ ጤና ተቋም ይሂዱ። እነኝህ ምልክቶች ካስተዋሉ ፤ ፈጽሞ ችላ አይበሉ። ከጀርባ ያለ ጠንከር ያለ በሽታ አመላካች ሊሆኑ ይችላሉና የህክምና እርዳታ ይፈልጉ። ያስተውሉ! የተለመደ ነው ብለው ችላ አይበሉ። ዶክተርዎን ያማክሩ። ዛሬውኑ ጤናዎን ይምረጡ!

  • 🦷 ጥርስ በተፈጥሮው ነጭ አይደለም!

    ጥርሶችዎ ምን ይመስላሉ? እንደ ሀጫ በረዶ የነጹ ናቸው ወይስ እንደ ጥጥ ባተሎ መለስተኛ? ወይስ ነትበዋል? በቴሌቭዝን መስታወት እንደለመድናቸው ማስታወቂያዎች ፤ ጥርስዎ ፈጽሞ ካልነጻ ፈገግታዎ ጎዶሎ ነው። እርስዎስ ምን ያስባሉ? እውነት ወይስ ሐሰት? ጥርስ በተፈጥሮው ነጭ አይደለም! ይህም የተለመደ ነው። ከህክምና አንፃር የየትኛውም ሰው ጥርስ ፈጽሞ ነጭ አይደለም ። ይህንን ለመረዳት የጥርስን አካላት ማየት ያስፈልጋል። ጥርስ በተፈጥሮው ሶስት አካላት አሉት። የጥርስ አካላት አቀማመጥ ኢናሜል(Enamel) - የጥርስ መስታወት ሲሆን፤ የጥርስ ውጫዊ ክፍል ነው። ዴንቲን(Dentin) - ይህ ከጥርስ መስታወት ስር ያለ ሲሆን በተፈጥሮ መለስተኛ ቢጫ ቀለም አለው። ፐልፕ(pulp) - ይህ የጥርስ ስጋ ሲሆን ውስጡ ደምስሮች እና ነርቮች ይገኛሉ። ይህ በደንቲን የተከለለ ሲሆን ፤ በጥርስ እምብርት ውስጥ ይገኛል። ለዚህም አይታይም። ኢናሜል በተፈጥሮው የመስታወት ባህሪ ስላለው ፤ የጥርስን የታችኛው ክፍል በከፊል ያሳየናል። ለዚህም ጥርስ ሲመለከቱ በኢናሜል አሻግረው ቢጫውን ደንቲን ነጸብራቅ ነው የሚያዩት። ➡️ ለዚህም ኢናሜል ከሳሳ ጥርስ ይበልጡኑ ቢጫ ቀለም ኖሮት ሊስተዋል ይችላል። ➡️ ኢናሜል ወፍራም ከሆነ ጥርስ ወደ ነጭ የተጠጋ ቢጫ መልክ ይኖረዋል። ለዚህ ሀጫ በረዶ የመሰለ ጥርስ ፤ ህክምናዊ እውነታ አይደለም። እንደውም ጥርሶች ነጭ ሆነው ፤ ሊቦረቦሩ ፣ ሊበሰብሱ፣ እንዲሁም በኬሚካል የተጎዱ ሊሆኑ ይችላሉ። በተቃራኒውም ጥርሶች ነጭ ሳይሆኑ ፤ ጤናማ ሊሆኑ ይችላሉ። የጥርስ ጤና የሚመዘነው ፤ በጥርስ መስታወት ጥንካሬ ፣ ጥርስ ላይ ቆሻሻ ክምችት/አንኳር ባለመኖር፣ ጥርስ መቦርቦር ባለመኖር ፣ ጥርስ በጤናማ ደረጃ ማኘክ በመቻሉ፣ ሙቀትና ቅዝቅዜን በመቻሉ፣ ድድ ጤናማ በመሆኑ፣ እንዲሁም ኢንፌክሽን ባለመኖሩ ነው። ታድያ ስለጥርስ ቀለም ምን አሳሳበን? የጥርስ ቀለም ብዙ ጊዜ ላይ የጥርስ ንጽህና አመላካች ሊሆን ይችላል። ይህ ደግም ከጥርስ መቦርቦርና ኢንፌክሽን፣ እስከ ድድ መቆጣት ድረስ ሊያስከትል ይችላል። የጥርስ ቀለም ለውጥ የምንለው ምንድነው? ጥርስ ከተፈጥሮ መልኩ በተለያዩ ምክንያቶች ሲቀየር ፤ የጥርስ ቀለም ተለወጠ እንላለን። ይህም የቀለም ለውጥ የጥርስን መስታወትን ብቻ ሲነካ እና እስከ ደንቲን ሲደርስ ልዩነት አለው። የውጭ የቀለም ለውጥ የቀለም ነጠብጣቦች የጥርስ መስታወት ላይ ሲያርፉ ይፈጠራል። በውጭ በኩል ስላለ ለማስለቀቅ ቀላል ነው። በጥርስ ብሩሽ ብቻ በቀላሉ ሊጸዳ ይችላል። ይህም በቡና ፣ በሻይ ፣ በሲጋራ፣ በምግብ ቀለሞች እንዲሁም በጥርስ ንጽህና ጉድለት ሊከሰት ይችላል። የጥርስ መስታወትን አልፎ ፤ ቀለሙ እስከ ጥርስ ውስጠኛ ክፍል ከደረሰ ግን ፤ በጥርስ ብሩሽ ማስወገድ ያዳግታል። ይህም በእድሜ በሚመጡ ለውጦች ፣ በልጅነት ዘመን ለከፍተኛ ፍሎራይድ በመጋለጥ፣ በልጅነት ዘመን በሚወሰዱ አንዳንድ መድሀኒቶች ሊከሰት ይችላል። የጥርስ ውስጣዊ ክፍል ላይ ያለ ደም መፍሰስም ይህን ሊያመጣ ይችላል። ሆኖም ግን አንዳንዶቹ ዘላቂ ናቸው። እነኝህን ቀለሞች ለማጽዳት የጤና ባለሙያ ያማክሩ። የጥርስ ቀለም ለውጥ መንስኤዎች ከዓለም ህዝብ መሀል ከ 60-75% የሚሆኑት አዋቂዎች የጥርስ ቀለማቸው ከተፈጥሮው ለውጥ እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአገራችን በኢትዮጵያም ይህ እንዲኖር ከሚያደርጉ ምክንያቶች መሀከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ቡና እና ሻይ አብዝቶ መጠጣት ቡናም ሻይም በውስጣቸው የሚያቀልሙ ኬሚካሎች (ወይም ክሮሞጅንስ / chromogens) አላቸው። በተለይም ታኒን (Tanin) የሚባለው ውህድ የጥርስ መስታወትን (enamel) መልክ ወደ ቢጫ እና ቡናማ ይለውጣል። በተለይ በኢትዮጵያ የምንጠጣው ሻይ ቅጠል ፤ በልዩ ስሙ ጥቁር ሻይ (black tea) ሲባል ፤ በውስጡ ይህን ውህድ በከፍተኛ መጠን ይዟል። ለዚህም ሻይ መጠጣት ከቡና በላይ ጥርስን አብዝቶ ያቀልማል። ከዚህም ባሻገር ሁለቱም መጠነኛ አሲዳማነት ስላላቸው ፤ የጥርስን መስታወት ያሳሳሉ። የሳሳውም የጥርስ መስታወት በቀላሉ ይቦረቦራል። ጫት መቃም አብዛኞቻችን እንደምናስተውለው ፤ ረዥም ጊዜ ጫት የሚቅሙ ሰዎች ጥርሳቸው ነትቦ ይስተዋላል። ይህም በአንድ በኩል ታኒን የሚባለው ውህድ ጫት ውስጥ በመገኝቱ እንዲሁም በጫት አሲዳማነት ይመጣል። ከዚህም ባሻገር ጫት የምራቅን መጠን ስለሚቀንስ አፍን ያደርቃል። ይህም የጥርስ ንጽህናን ያስተጓጉላል። እዚህ ላይ ጫት ጋር የሚወሰዱ ጣፋጭ መጠጦች ፣ ስኳር ፣ እንዲሁም አቾሎኒ ጥርስን ይብሱኑ ያቆሽሻሉ። እነሱን የሚመገቡት ባክቴሪያዎች ደግሞ ጥርስን ይቦረቡራሉ። ሲጋራ ማጨስ ሲጋራ በውስጡ ካሉ ኬሚካሎች መካከል ጥርስ ላይ በይበልጥ ጉዳት የሚያደርሱት ሁለት ናቸው። እነኝህም ኒኮቲን (Nicotine) እና ታር (Tar) ይሰኛሉ። ሁለቱ የጥርስን መስታወትን ያሻክራሉ። ለዚህም ሌሎች ቀለሞች ጥርስ ላይ በቀላሉ እንዲቀሩ እድል ይፈጥራል። ኒኮቲን መልክ አልባ ቢሆንም ፤ ከ አየር (ኦክስጅን) ጋር ሲገናኝ ቢጫ ይሆናል። የጥርስን መስታወት አልፎ ገብቶ ፤ የጥርስን ቀለም ወደ ቢጫ አልያም ቡናማ ቀለም ሊለውጥ ይችላል። ደም ስርንም ስለሚያጠብ ፤ የጥርስ መበስበስን ያፋጥናል። ታር በበኩሉ ከኒኮቲን በላይ የጥርስን ቀለም ይለውጣል። የጥርስ መስታወት ላይ እንደ ጥላሸት የጠቆሩ ፤ በብሩሽ ለማስለቀቅ የሚያስቸግሩ ቀለማትን ይተዋል። የጥርስ ጉዳትም እንዲፋጠን ያደርጋል። ፍሎራይድ የበዛበት የከርሰምድር ውሀ የሚጠቀሙ ማህበረሰቦች የመጠጥ ውሀ ውስጡ ያለው የፍሎራይድ መጠን ከ 1.5 ppm በላይ ከሆነ ፤ የጥርስ አመሰራረት ላይ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል። ይህም የፍሎራይድ መጠን ጥርስን የሚሰሩትን አሚዮብላስት(ameoblasts) የሚባሉትን ህዋሳት ያሰናክላል። ለዚህም ጥርስ አመሰራረቱ ይለወጣል። ይህም ጥርሳቸው መብቀል የጀመረ ፤ ከ 8 አመት በታች ያሉ ልጆችን ያጠቃል። በህጻንነታቸው ፍሎራይድ የበዛበት ውሀ ሲጠጡ ያደጉ ህጻናት ጥርሳቸው ቀለሙም ቢጫ፣ ቡናማ ወይም ጥቁር ሊመስል ይችላል። ለውጡም ቋሚ/ዘላቂ ነው። ለዚህም ቀዳሚ ምሳሌ የሚሆኑት የናዝሬት ተወላጆች ናቸው። ጣፋጭ እና የታሸጉ ምግቦችን መመገብ እነኝህ በውስጣቸው ለመፈጨት ቀላል የሆኑ ስኳሮችን ( ካርቦሃይድሬቶችን ) ይይዛሉ። አብዝተው ሲመገቧቸው ፤ ከእርሶ ባሻገር ለጥርስ ባክቴሪያዎች ምግብ ይሆናሉ። ተመግብው አቅማቸው የበረታው እነኝህ ባክቴሪያዎችም ፤ የሚያመርቱት አሲድ ጥርስን ያሳሳል። ለዚህም እነኝህ ምግቦች ጥርስን ያቆሽሻሉ ፤ መስታወቱን ያሳሳሉ ፤ ቀለሙን ይለውጣሉ። እንዲሁም ጥርስን እንዲበሰብስ አልያም እንዲቦረቦር እድል ይሰጣሉ። ጥርስን ንጽህና በአግባቡ አለመጠቀም የጥርስን ንጽህና በአግባቡ አለመጠበቅ ጉዳት አለው። ጥርስ ላይ ቆሻሻ እንዲከማች ፤ ጥርስን የሚያዳክሙ ባክቴሪያዎች እንዲበራከቱ ያደርጋል። ይህም ጥርስዎ ጥርስዎ እንዲቦረቦር እድል ይከፍታል። ታድያ ለምንድነው ጥርሳችንን እስክንታመም ፤ የጥርስ ሐኪም የማናየው? ጥርስን ወደ ተፈጥሮ ንጻቱ መመለሻ አማራጮች ጥርስ ከጤማናነት ባሻገር ፤ የውብት መገለጫ ነው። ከማንነት ጋር ቁርኝትም ስላለው ፤ ብዙዎች ጥርሳቸውን ወደ ተፈጥሮ ንጻቱ ለመለለስ ሲሞክሩ ይታያሉ። አንዳንዶች ከሰው በሰሙት ጥርሳቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ አማራጮች ሲጠቀሙ ፤ ሌሎች ደግሞ አስፈላጊውን እንክብካቤ ሲያደርጉ ይስተዋላል። ጥርስን ንጻት ለመመለስ በማህበረሰባችን ውስጥ ከሚደረጉ አማራጮች ጥቂቱን እንመልከት። 1. የጥርስ ብሩሽ እና ሳሙና ይህ የጥርስን የመስታወት ግድግዳ ማጽጃ ፤ መጥረጊያ ነው። ቆሻሻን ያስወግዳል። ነጠብጣቦችን ያጸዳል። የጥርስ ሳሙናዎች በውስጣቸው ብዙ አይነት ኬሚካል አላቸው። ከዚህም ውስጥ ፍሎራይድ የጥርስ መስታወትን ያጠናክራል። ፀረ-ባክቴሪያ ውህዶች ደግሞ ጥርስን የሚጎዱትን ባክቴሪያዎችን ያጠፋሉ። ጥናቶችም ይህን ይደግፋሉ! በቀን ሁለት ጊዜ መቦረሽ የጥርስ ቆሻሻን በእጅጉ ይቀንሳል። የጥርስ ሳሙና አዘውትሮ መጠቀም ፤ ጥርስ መስታወት ላይ ያሉ የቀለም ለውጦችን ከ15-30% ይቀንሳል። ፍሎራይድ ያለው የጥርስ ሳሙና መጠቀም ደግሞ ፤ የጥርስ መቦርቦርን እስከ 40% ይቀንሳል። ታድያ ግን ለጥርስዎ መስታወት ጤና ፤ ከጠንካራ ብሩሾች ለስላሳ ብሩሾችን እንዲመርጡ ይመከራል። የጥርስ ሳሙናዎች ዋጋቸው ተመጣጣኝ ከመሆኑም ባሻገር ፤ ለእለታዊ አጠቃቀም ምቹ ናቸው። ጥርስን የማንጻት አቅማቸው ግን የተገደበ ነው። ጥርስን የሚያነጹት ቀስ በቀስ ፤ ደጋግሞ በመጠቀም ነው። ቢሆንም ግን ጥርስ ያለበት ጉዳት እንዳይባባስ ይጠብቃሉ። ለዚህም ተመራጭ ናቸው። 2. ቤኪንግ ሶዳ (Baking Soda) ጥርስን ለማንጻት ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ፤ ይህን ውህድ ይጠቀማሉ ። ውህዱ በባህሪው ቤዝ ስለሆነ ፤ የጥርስ ባክቴሪያዎች ያመነጩትን አሲድ ይቃወማል። ጥርስንም በጊዜያዊነት ያነጻል። ችግሩ ግን ይህ ውህድ የጥርስን መስታወት ያሳሳል። ለውጡም ዘላቂ አይደለም። የጥርስን መቦርቦርንም አይቃወምም። ይልቁኑ ጥርስን ለሌላ አደጋ ተጋላጭ ያደርጋል። ለዚህም በህክምናው ፈጽሞ አይመከርም! ጥርስን መፋቅ ጥርስን በተለያዩ አይነት መፋቂያዎች መፋቅ ጠቀሜታ አለው። ጥርስ ላይ የሚከማች ቆሻሻን ወዲያውኑ ለማስወገድ ይጠቅማል። ጥርስም አዲስ ቀለም እንዳያመጣ ይከላከላል። ሆኖም ግን ጥርስ ላይ የሰነበቱ ቀለሞች ለማጥፋት ያዳግተዋል። ለዚህም ለወየበ ጥርስ መፍትሔ አይሆንም። አንዳንዶች ጥርስን ለማንጻት አብዝተው አልያም በኃይል ሲፍቁ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይመከርም። ለጥርስ ጉዳት አለው። አብዝተው ሲፍቁ የጥርስ መስታወት ሊበሳሳ ይችላል። መስታወቱን ከሳሳ ጥርስ ከመንጻት ይልቅ ፤ ከስር ያለውን የደንቲን ቢጫ ቀለም ይይዛል። በጤና ባለሙያ የሚደረግ የጥርስ ማጽዳት ይህ ጥርስ ላይ የተከማቹ ቆሻሻዎችን ፣ አንኳሮችን (calculus) ያስወግዳል። ለመልቀቅ የሚያስቸግሩ የጥርስ ቀለሞችንም ያጸዳል። እንዲሁም የጥርስ መስታወትን አንጸባራቂነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ያደርጋል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ፤ በዚህ መንገድ እስከ 90% የሚሆነውን የጥርስን ንጻት ወደነበረበት መመለስ ይቻላል። በጣም ውጤታማ ሲሆን ፤ የድድንም ጤና ያሻሽላል። ይህም ብዙዎች የማይመርጡት ከሒሳብ አንጻር ነው። ጥርስን በኬሚካል የማጽዳት ህክምና ይህ የጥርስን መስታወት ዘልቆ የሚገባ የኬሚካል እጥበት ነው። ለእጥበት ፐርኦክሳይድ የሚባል ውህድ ይጠቀማል። ጥርስን እጅጉን ሊያነጻ ፤ ሀጫ በረዶ ሊያስመስል ይችላል። በዚህ ህክምና የሚያገኙት የንጻት መጠን ፤ በጥርሶችዎ ላይ በተከማቸው ቆሻሻ መጠንና በጥርስዎ መስታወት ውፍረት ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ህክምና እጅጉን አመርቂ ውጤት ቢያሳይም ፤ ጥርስን ለቀናት ቁጡ (ሙቀትና ቅዝቃዜ የማይችል) ሊያደርግ ይችላል። ድድንም ሊያስቆጣ ይችላል። የባለሙያም ክትትል ያስፈልገዋል። አማራጮችዎ እንዲህ ቢሆኑይመረጣል! ለመከላከልና የጥርስዎን ጤና ለመጠበቅ ፤ በጥርስ ሳሙና በቀን ሁለቴ መቦረሽ ይመረጣል። መለስተኛ ነጠብጣቦች ለማስለቀቅ ፤ በባለሙያ ጥርስን ማጽዳት ይሻላል። የማይለቁ ጥልቅ ነጠብጣቦች ካሉ ፤ ጥርስን በባለሙያ በኬሚካል እጥበት ማጽዳት ይችላሉ።

  • Sick Like the West, Live Like Ethiopia: The Grim Reality

    Over millennia, the name Ethiopia  has been associated with pride, humility, and a people full of life. Ancient writers did not speak of Ethiopia with pity, but with reverence. Homer, in The Iliad  and The Odyssey , famously described Ethiopians as : “the blameless Ethiopians, dwelling apart, the farthest of men, where the gods themselves go to feast.” This was not charity. It was recognition. Behind kings, kingdoms, and civilizations, our story followed a familiar human arc — dignity, struggle, resilience. Except for the past century. Modernity Arrived! But Not on Our Terms The last hundred years brought astonishing change. Medicine entered Ethiopian reality. Hospitals rose. Antibiotics, vaccines, surgery, diagnostics — all arrived. Along with them came the perks of modernization . But also its shadows. A few decades ago, the word Ethiopia  became shorthand for poverty, hunger, and starvation in the global imagination. One photograph — powerful, real, but incomplete — froze our identity in time. Since then, Ethiopia has repeatedly been ranked among the poorest nations, often “winning” if the race is from last to first. As of early 2025 , according to global estimates, 10 million people needed food assistance. This figure carries deeper weight, where over 36% of children under five are stunted. The Federal Ministry of Health of Ethiopia and stakeholders have been fighting this uphill battle to reverse malnutrition in the country. This is not merely a nutrition issue. It is a lifelong health sentence! And yet — the truth is more complex. Yes, challenges are real. But triumphs are real, too. We Live in Ethiopia! Not the West Economically, we live Ethiopian lives. Based on 2024–2025 World Bank and IMF data, Ethiopia's average daily income is roughly $2.70 to $3.10 per person . This is just on the poverty line. Yet, paradoxically, the national currency still allows day-to-day survival. People manage. Daily living continues. The market reality is shaped by persistent inflation. Food prices rise steadily, sometimes quietly, sometimes all at once. According to World Bank estimates, overall inflation stood at around 21% in 2024 . National figures tell a slightly calmer—but still troubling—story, with the Ethiopian Statistical Bulletin reporting food inflation at 10.6% in 2026. On paper, these are numbers. Every household decision, however, is shaped by this constraint — what to buy, what to delay, what to go without. As an agricultural Society, food still finds its way to the table. Locally, it is said "የእለት እንጀራ አያሳጥንም", which translates to 'we trust, we will manage to eat.' This is not comfort. It is resilience. It is Ethiopia! The Old Enemies Never Left Communicable diseases have not been fully controlled. In just recent years, Ethiopia has faced: Marburg virus outbreak Recurrent measles resurgence Malaria hyperendemicity Rising cholera outbreaks HIV is increasing to epidemic levels in certain urban centers and the list goes on.... The old diseases never left. The new ones just arrived early. Life Ends Too Early in Ethiopia Life expectancy in Ethiopia remains around the mid-60s . It is dragged down by infections, trauma, and untreated chronic disease. Ironically age of graduation for an undergraduate degree in Ethiopia is 24 years . This means that by the time an average guy graduates from university, he has spent 40- 50 % of his life just acquiring education. When he finally begins to establish himself professionally(which mostly happens in the 30s), he only has 10 to 20 productive years of life left ahead of him. Unfortunately, a significant percentage of those who get to live longer live with disability. This is not just numbers! It is the grim reality. In the past decades, several well-known Ethiopians have died before the age of 60. Hachalu Hundessa died young at 34 . Netsanet Workineh passed away in his 40s . Eyob Mekonnen died at 37 . Tesfaye Gebreab died at 54. We can keep counting! Famous singer Tamirat Desta died at 39 years of age . Composer Elias Melka died at the age of 41. This is not a coincidence. This is the average reality. Even the former Prime Minister, His Excellency Meles Zenawi, died at 57. Some of these deaths were traumatic. Some were due to chronic illness. Some were caused by infections that should not have been deadly in the 21st century; a pattern reflective of Ethiopian reality. Of course, there are exceptions like Philanthropists Abebech Gobena and Singer Alemayehu Eshete (Ethiopian Elvis). Both died in their 80`s. Even the famous composer Emahoy Tsegué-Maryam Guèbrou died at the age of 99 in 2023. But these lives, admirable as they are, represent the exception — not the rule What is considered premature death in the rest of the world is getting regarded as timely death in Ethiopia. Even the young age of 50 is quietly treated as old age. That is not only tragic. It is devastating. Yes, there have been improvements over the past decades. Yes, life expectancy is rising. But we are still dying young. The numbers may be moving upward, but the reality on the ground tells a different story. Too many Ethiopians are still dying in their most productive years — before retirement, before stability, before watching their children grow. We Imported the Diseases: Not the Benefits Instead of acquiring the luxury  of modern life, it seems we acquired its disease pattern. This is not an exaggeration; the data shows it clearly. Cancer is rising sharply. Three years back(in 2022), Ethiopia had an estimated 80,334 new cancer cases and 54,698 cancer-related deaths . This number is expected to double in the coming decade. Hypertension and diabetes are increasing at alarming rates, especially in cities. Stroke is now a leading cause of adult disability. It is responsible for ~ 6.2% of total deaths in Ethiopia. We could continue. Ironically and tragically, we are meeting these diseases earlier in life. Cancer is no longer a diagnosis of old age. Women often arrive for care when breast and cervical cancers are already advanced, when options are fewer and outcomes harsher. Lung cancer, once associated with decades of exposure, presents at a younger age and at a later stage compared to the world . In Oncology centers across Ethiopia, it is not unusual to see waiting rooms filled with people who are too young to be there, and already too late to be saved. But the real question is: Why Us? What makes us special — in the worst way? Why did we get the worst of both worlds ? Misplaced Modernization The simple answer is nutritional Transition. Traditional societies ate organic, unprocessed foods and lived physically active lives. This was not by choice, but by necessity. Modern societies have become sedentary. Yet, they built: preventive systems, early screening, health insurance, and long-term care. We did neither fully. We became a testing ground for processed foods without nutritional literacy, sedentary lifestyles without urban planning, and Western diseases without Western safety nets. We became a wasteland of half-adapted change. The West also struggles with these diseases, but it has the health infrastructure to manage them as chronic conditions. Patients are diagnosed early, treated continuously, and survive for decades. So What Can We Do — Right Now? There is nothing abstract about this. Neither is it a policy. This is truly personal. You need to tell your family this: Check blood pressure and blood sugar regularly You might not “feel” them until it's too late. Move daily Walking is medicine. Farming is medicine. Physical labor protects the heart. Keep moving. Exercise. Respect traditional diets Our grandparents were right. Eat organically. Eat Legumes, Vegetables, and Whole grains. Treat infections seriously Don't bargain about your health. Take Vaccines when advised. Make sure to drink clean water. Hygiene saves lives. Do not normalize early death!!! Dying at 45 is not “God’s will.” It is a preventable disease. Check with your doctor regularly. Don't wait for symptoms to appear. Health facilities should not be what you visit when you get sick. Go and have a check-up. Remember : Knowledge is power. And this story is our story   We can still change its direction. We can save this Generation. Frequently Asked Questions (FAQ) – Health in Ethiopia Q1: Where can I find affordable diagnostics for common diseases in Ethiopia? Affordable diagnostic services are available in public hospitals, health centers, and government-run health institutes across the country. Some NGOs and private clinics also offer subsidized testing for conditions like diabetes, hypertension, malaria, and HIV. Some NGOs specialize in Sexual and Reproductive Services only. Q2: What are the most common health challenges faced by Ethiopians? Ethiopians face several health challenges, including: Communicable Diseases like Malaria, tuberculosis, measles, cholera, and HIV/AIDS. Non-communicable diseases like Hypertension, diabetes, stroke, and cancer. Nutrition-related issues like malnutrition and stunting among children. Traumatic Injuries like Road Traffic Accidents. Q3: Where can I find reliable information on disease prevention strategies in Ethiopia? To find the most reliable information on disease prevention in Ethiopia, use trusted sources like: Ethiopian Federal Ministry of Health (FMoH) official website . You can check its policies, guidelines, and health campaigns. The World Health Organization (WHO) Ethiopia page provides disease prevention resources and public health reports. The WHO Africa page also provides health information and news on Ethiopia. Local NGOs and communities' health programs provide educational materials and outreach activities to increase health awareness. Moreover, you can check academic literature from peer-reviewed journals. Q4: How can individuals reduce their risk of common diseases in Ethiopia? Individuals can reduce the risk of common diseases in Ethiopia by employing the following strategies: Regular health check-ups and screenings for blood pressure, blood sugar, and cancer markers. Maintaining a balanced diet rich in legumes, vegetables, and whole grains. Daily physical activity, including walking or farming. Vaccination and adherence to prescribed medications. Practicing safe hygiene and clean water consumption.

  • የደም ካንሰር ምንድን ነው?

    ፊልም ወዳጅ ከሆኑ ፤ ከእነኝህ ሁለት ተዋናዮች ውስጥ አንዱን ያውቁታል። በግራ ያለው በስፓርታከስ የሚታወቀው አንዲ ዋይትፊልድ (Andy Whitfield) ሲሆን በቀኝ በኩል ደግሞ በዴክስተር ፊልም የሚታወቀው ማይክል ሆል (Michael C. Hall) ነው። ከ ፊልም ተዋናይነታቸው ባሻገር ሁለቱንም አንድ የሚያደርጋቸው ቢኖር የደም ካንሰር ነው። ታድያ ግን የስፓርታከሱ አክተር በ 39 አመቱ ከዚህ አመት በሞት ሲለይ ፤ ማይክል ግን ከካንሰሩ አገግሞ አሁንም በህይወት አለ። ይህ የደም ካንሰርን እውነታ ያሳያል። አንዳንዶች ሲያገግሙ ሌሎች ይሞታሉ። በዚህ ጽሁፍ ስለ ደም ካንሰር እናነሳለን። ስለ ደም ካንሰር ከመወያየታችን በፊት ፤ የደም ህዋሳት ምንጭ ስለሆነው መቅኔ መረዳት ይኖርብናል። የአጥንት መቅኔዎ እጅጉን ታታሪ አካልዎ ነው። መቅኔዎ በቀን ውስጥ ወደ 500 ቢሊዮን የሚጠጉ የደም ሕዋሳትን ይሠራል። ይህም ለእርስዎ ጤናማ ህይወት እጅጉን አስፈላጊ ነው። የተመረቱት የደም ህዋሳትም በስርአት ተግባራቸውን ይፈጽማሉ። እድገታቸው፣ ስራቸው እና ሞታቸው እጅጉን ስርአት የጠበቀ ነው። መቅኔዎ አዲስ ህዋሳት የሚሠራው ፤ የሞቱ እና የደከሙ ህዋሳትን ለመተካት ነው። ከሚያስፈልገው በላይ ሆነ በታች ህዋሳትን አያመርትም። ታድያ ይህ ሚዛን ሲዛባ ፤ የደም ህዋሳትዎ መጠን ይቃወሳል። አለልክ መመረት ይጀምራሉ ፤ ይህን ጊዜ የደም ካንሰር አለ ይባላል።    30 ትሪሊየን በላይ የሚገመቱ የደም ህዋሳት ውስጥ ፤ በሺ የሚቆጠሩ ካንሰር ህዋሳት ለእርሶ ምንም ለውጥ ላያመጡ ይችላሉ። ችግሩ ግን ካንሰር ሕዋሳት መራባት አያቆሙም። በሺ የነበሩት ሚሊየን ይሆናሉ ፤ ሚሊየን የነበሩት በቢሊየን ይቆጠራሉ። ከራሳቸውም አልፎ የጤነኛ ህዋሳትን ስራ ያስተጓጉላሉ። ይህን ጊዜ ምልክት ሊያዩ ይችላሉ። ምልክት ባዩ ጊዜ ከሚሊዮን እስከ ቢሊዮን የሚቆጠሩ የካንሰር ሕዋሳት ደምዎት ውስጥ እየተዘዋወሩ ሊሆን ይችላሉ። የደም ካንሰሮች በብዛት አይታዩም ፤ ሲያጋጥሙ ግን ገዳይ ናቸው። በበአለም ዙሪያ ካሉ ካንሰሮች ውስጥ የደም ካንሰሮች 6 በመቶ የሚሆነውን ይወክላሉ። በየአመቱ ወደ 1.3 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በደም ካንሰር ሲያዙ ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ይቀጥፋሉ። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ይህ ጎልቶ ይታያል። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተደረገ አንድ ጥናት ሊዩኬሚያ የሚባለው የደም ካንሰር ካለባችው አምስት ታማሚዎች ውስጥ አንዱ ብቻ (21%) የአምስት አመት እድሜ ይኖረዋል። ባደጉ አገራት ግን ከ60 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች ከአምስት አመት በላይ ይኖራሉ። ታድያ ይህ ለምን ሆነ? ይህ እውነታ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ይያዛል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ታማሚ ዘግይቶ ነው የሚታከመው። ህክምና ቦታ ሲደርሱም ፤ ባለ የጤና መሰረተ ልማት እጥረት ፤ የተሟላ የላብራቶሪ ምርመራ ሳይደረግ ይቀራል። በሽታው መኖሩ በታወቀ ጊዜ ፤ ደርጅቶ ይገኛል። ህክምናውም ሁሉም የጤና ተቋማት በቀላሉ ስለማይገኝ ፤ ብዙዎች ህክምናውን በስርአት ለመከታተል ይቸገራሉ። ኢንፌክሽን ህመሞች በተንሰራፉባት ሀገራችን ደግሞ ፤ በስርአት ህክምና አለመከታተል የከፋ ደረጃ ላይ ይጥላል። ለዚህም የደም ካንሰር ለብዙዎች ሳይታለም የተፈታ እውነታ ይሆናል። ለምንስ ዘግይቶ ይታወቃል? የደም ካንሰሮች ቀድመው ህመም አያስከትሉም። መጠናቸው በዝቶ የጤናማ የደም ህዋሳትን ሲያስተጓጉሉ አብዛኖቹ ምልክቶቹ ይስተዋላሉ። ምልክቶቹ ግን የተለመዱ ስለሆኑ ፤ችላ ይባላሉ። ለምሳሌ፡ ድካም/ምክንያት የለሽ ድካም፡ ይህ ምልክት የቀይ የደም ህዋስ ስራ መስተጓጎል ጋር ይገናኛል። ደጋግሞ በኢንፌክሽን መያዝ ፡ ይህ የነጭ የደም ህዋስ ስራ ከመስተጓጎል ጋር የተያያዘ ነው። በቀላሉ መበለዝ እና መድማት ፡ ይህ ምልክት ከፕሌትሌት ስራ መስተጋጎል ይመጣል። ትኩሳት፡ ይህ ሰውነት የካንሰር ህዋሳትን ለማስወገድ በሚያደርገው ጥረት እንዲሁም በኢንፌክሽኖች ሊመጣ ይችላል። ክብደት መቀነስ ፡ ይህም የምግብ ፍላጎት ከመቀነስ ጋር ሊያያዝ ይችላል። እርስዎ ለመሆኑ እነኝህን ምልክቶች አይተው ካንሰር ብለው ያስባሉን? አዎ! የብዙዎችም እውነታ እንደ እርስዎ ነው። የድካማቸው ምንጭ እረፍት ማጣት፣ እድሜ ፣ ወይም ደም ማነስ ብለው ይዘናጋሉ። ትኩሳት ሲሰማቸውና ኢንፌክሽን ደጋግሞ ሲይዛቸው አንቲባዮቲክስ ደጋግመው ይወስዳሉ። ከኋላ ስለሚኖር በሽታ ፈጽሞ አይጠረጥሩም። ደግሞስ ኢንፌክሽን በሽታዎች በበዙባት ኢትዮጵያ ባይጠረጠር አይደንቅም። ኢንፌክሽን ህመሞች በበዙባት ኢትዮጵያ እነኝህ ምልክቶች አያሳስቡም። በሽታ ተችሎ እንዲታለፍ በሚያበረታታ ማህበረሰብ ውስጥ ችላ ተብለው ይታለፋሉ። ለዚህም ምልክቶቹን መቋቋም ያቃታቸው ጊዜ ጤና ተቋም ይሄዳሉ። ያን ጊዜ ዘግይተዋል። ለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ የደም ካንሰሮች ዋነኛ ገዳይ በሽታዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። አ.ኤ.አ 2019 ዓም የተደረገ ጥናት ይህን ይደግፋል። ሊዩኬሚያ የሚባለው የደም ካንሰር በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም አራት ገዳይ ካንሰሮች ውስጥ ተጠቅሷል። በምንስ ይመጣል? ለደም ካንሰር አጋላጭ የሚባሉ መንስኤዎች መሀከል ዋነኛ የሚባሉት፡ የቤተሰብ ታሪክ ፡ በቤተሰብ የደም ካንሰር ታማሚ ካለ የደም ካንሰር የማጋጠም እድሉ ከፍተኛ ነው። በጊዜ ውስጥ የሚመጡ የዘረመል ለውጦች፡ እነኝህ የዘረመል ለውጦች ህዋሳት ወደ ካንሰር እንዲለወጡ ያደርጋሉ። ለዚህም እድሜ በገፋ ቁጥር እነኝህ ካንሰሮች የማጋጠም እድል እየጨመረ ይመጣል። ለጨረር መጋለጥ፡ ደጋግሞ መጋለጥ ተጋላጭነትን ይጨምራል። ለኬሚካሎች መጋለጥ። ቤንዜን ለ ሊዩኬሚያ እንደሚያጋልጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እንዲሁም አንዳንድ ኬሚካሎች መቅኔ ላይ ባላቸው መርዛማነት እነኝህን ካንሰሮች ሊያመጡ ይችላሉ። ቫይረሶች ፡ አንዳንድ ቫይረሶችም እነኝህን ካንሰሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ። የበሽታ መከላከያ ስርአት ችግር፡ በተፈጥሮ ሆነ በመድሐኒት የሚመጥ የበሽታ መከላከያ ስርአት መዛባት እነኝህ ካንሰሮችን ሊያስከትል ይችላል። እናስ ምን ይሻላል? መደበኛ ምርመራ ያድርጉ! በ ሲቢሲ (CBC) መጀመር ይችላሉ። እንደ ሀኪምዎ ትዕዛዝ የ ደም ማይኮርሶፕ ምርመራ (peripheral smear) እና የ መቅኔ ናሙና ምርመራ (bone marrow examination) ሊያስፈልግ ይችላል። የደም ካንሰር አይነቶቹን ለመለየት ላቅ ያሉ ምርመራዎችም ሊታዘዝልዎትም ይችላሉ። በጊዜ ካወቁ የህክምና አማራጮች አሎት ። እንደ ካንሰር አይነቱ እና ደረጃው : ኬሞቴራፒ (Chemotherapy)፣ ታርጌትድ ቴራፒ (Targeted Therapy) እንዲሁም ኢምዩኖ ቴራፒ (Immunotherapy) ሊታዘዝ ይችላል። እንደ ካንሰር አይነቱ ለአንዳንድ ታካሚዎች የመቅኔ ንቅለ ተከላ ሊደረግ ይችላል። እነኝህ ታካሚዎች ከበሽታው ፈጽሞ ሊያገግሙ ይችላሉ። ይህ ሁሉ የህክምና አማራጭ ውጤታማ የሚሆነው፤ ቀድመው ህክምና ከጀመሩ ነው። ለዚህም ድካም ነው ብለው ፈጽሞ ችላ አይበሉ። መዘግየትዎ ዋጋ ያስከፍላል!

  • ተዋርደን ይሆን!? ታዋቂው ዩቲዩበር በኢትዮጵያ ያጋጠመው ህመም ምንድን ነው?

    ጉብኝቱ ለረዥም ጊዜ ተጠብቋል። ሆኖም አመጣጡ ግን ድንገተኛ ነበር! በዩቱዩብ ብእር ስሙ አይ ሾው ስፒድ በመባል የሚታወቀው አሜሪካዊው ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር ከ 3 ቀን በፊት ኢትዮጵያን ጎብኘቷል። ይህ ዩቲዩበር በዩቲዩብ ቀጥታ በሚያደርጋቸው መስተጋብሮች በአለም ዙሪያ የተወደደ ነው። ለዚህም የተለያዩ ሽልማቶች ያገኘ ሲሆን በፈረንጆቹ 2025 ራሱ እጅጉን ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ተብሎ በ ሮሊንግ ስቶንስ ተሸልሟል። ይህም የሱን ጉብኝት ለየት ያደርገዋል። ጉብኝቱ ቀጥታ ስለሆነ ፤ ብቻውን ሳይሆን በአለም ዙሪያ ያሉ ተከታዮቹም አብረውት ይጎበኛሉ። የኢትዮጵያውን "I rl stream in Ethiopia" በወቅቱ ወደ 9 ሚሊየን ሰዎች በኢንተርኔት ተከታትለውታል። ጉብኝቱ በቀጥታ ለተላለፈበት 4 ሰአት ከ 52 ደቂቃ የአለም አይኖች ኢትዮጵያ ላይ አተኩረው ነበር። ለብዙዎቹም አስደማሚ እሱም እጅጉን የወደደው ጉብኝት ነበር። ጉድ እና ጅራት ከበስተኋላ ነው እንዲሉ... ጥሬ ስጋ ከበላ ጮማ ከቆረጠ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦቹን ካጣጣመ በኋላ፤ ድንገት ሆዱን ታመመ። ሽንትቤትም ቆይቶ ሲወጣ ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች በስፋት ተጋርተዋል። አይሾው ስፒድ ጥሬ ስጋ ሲበላ ይህ አሳፋሪ ጉዳይ ይሆን? ስለ ኢትዮጵያ አለም ያለውን ምስልስ አጠልሽቶ ይሆን? ካስተዋሉ ይህ የዚህ ዩቲዩበር ችግር ብቻ አይደለም። ጥቂት የማይባሉ ጎብኚዎችን ያጋጥማል። ይህ የህክምና ክስተት በየአመቱ በአፍሪካ፣ በእስያ እና በላቲን አሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎብኝዎችን ይጎዳል። ለምን? ይህን ለመረዳት ማስተዋል ያለብዎት ነጥቦች እነሆ፡  1️⃣ ተቅማጥ በሽታ አይደለም ፤ ምልክት ነው። በህክምና ተቅማጥ ራሱን እንደቻለ በሽታ አይታዩም። አንጀት ጋር ቁርኝት ያላቸው በሽታዎች የሚያሳዩት ምልክት ነው። በሽታ መኖሩን የሚናገር መልእክት ነው። በህክምናው ቀጠን ያለ አልያም ውሀ የሆነ ሰገራ ፤ ከተለመደው በላይ አልያም በ 24 ሰአት ውስጥ ለ 3 ጊዜ ካጋጠመ ፤ ተቅማጥ ይባላል። ይህም አንጀት እንግዳ ለሆነበት ፣ ለሚጎዳው እንዲሁም ከአቅሙ በላይ ለሆነበት ነገር ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ያሳያል። የተጓዦች አንጀት ደግሞ ፣ ለሚጎበኙት አገር ባይተዋር ነው። 2️⃣ አንጀት ትውስታ አለው - እና ተጓዦች ይህ አይኖራቸውም። በኢትዮጵያ ስንኖር የምንለምደው አየሩን ብቻ አይደለም። በሀገራችን ተስፋፍተው የሚገኙ በሽታ አምጪ ተህዋሳት ጋር ሰውነታችን ተላምዷል። የምንጠጣው ውሀ የምንመገብው ምግብ ውስጥ ሊገኙ የሚችሉ ረቂቅ ተሕዋስያን ለአንጀታችን እንግዳ አይደሉም። እነሱን ከዚህ በፊት የሚያውቃቸው የበሽታ መከላከያ ስርዓታችንም አፋጣኝ እና በቂ ምላሽ ስለሚሰጥ ፤ በለመድናቸው ተሕዋሳት እምብዛም አንታመምም። ጎብኚዎች ግን ይህ ትውስታ የላቸውም። ለዚህም ተመሳሳይ ምግብ ተመግበው ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ብዙውን ጊዜ ምንም ምልክት አይታይባቸውም። ጎብኚዎች ግን ምልክቶች ይሳያሉ። ወደ ገጠሪቷ ኢትዮጵያ ሄደው እርሶም ይህ አጋጥሞት ይሆናል። ያስተውሉ! ልዩነቱ የበሽታ መከላከያ ስርአት እንጂ ንፅህና አይደለም። 3️⃣ ዋናው ተጠርጣሪ ፡ የተጓዥ ተቅማጥ በአለም አቀፍ ዙሪያ ይህ ህመም ስያሜ አለው። የተጓዥ ተቅማጥ ተብሎ ይጠራል። ወደ ዝቅተኛ  እና መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገሮች የሚጓዙ  ከ30-70% የሚሆኑት ሰዎችን ያጠቃል ። 📌 ይህም በተለያዩ በሽታ አምጪ ተህዋሳት የሚመጣ ሲሆን፤ በጣም የተለመዱት የሚከተሉት ናቸው ኢንቴሮቶክሲጅኒክ ኢ. ኮላይ  (ETEC) ካምፓሎባክተር ሺጌላ ሳልሞኔላ ከዚህም ባሻገር እንደ ኖሮ ቫይረስ ባሉ ቫይረሶች እንዲሁም እንደ ጂያርዲያ ባሉ ፓራሳይቶች ይመጣል። እነዚህ ተህዋሳትን ለመለየት ታድያ የላብራቶሪ ምርመራ ያስፈልጋል። 4️⃣ምግብ እና ውሃ ፡ የተህዋሳቱ መኖሪያ አደጋው "የኢትዮጵያ ምግብ" አይደለም ። ለ ረቂቅ ተሕዋስያን መጋለጥ ነው። ጎብኚዎች ብዙ ጊዜ እንዲጋለጡ የሚያደርጉ ምንጮች መሀከል የሚከተሉት በብዛት ይጠቀሳሉ። ያልታከመ ወይም በበቂ ያልታከመ ውሃ መጠጥ ላይ የሚደባለቁ የበረዶ አንኳሮች ያልበሰሉ አትክልቶች ንጽህናው ባልተጠበቀ ውሀ የታጠቡ ፍራፍሬዎች ንጽህናው በጥንቃቄ ክትትል ያልተደረገለት የጎዳና ላይ ምግቦች ብዙ ጊዜ ተጓዦች ላይ ህመሙ እንዲታይ ያደርጋሉ። ከዚህም ባሻገር በስርአት ባልታከመ ውሃ ጥርስን መቦረሽ   እንኳን  ይህንን በሽታ ሊያስከትል ይችላል። 5️⃣ምግቡ ንጹህ ሆኖ አንጀት ሊያምጽ ይችላል። ሁሉም ምግብን ተከትሎ የሚመጣ የተቅማጥ በሽታ በበሽታ አምጪ ተህዋስ አይመጣም። ባክቴሪያ፣ ቫይረስና ፓራሳይት በሌለበት ሁኔታ ራሱ ተቅማጥ ሊያጋጥም ይችላል። አንጀት ላለመደው የምግብ አይነት ሲጋለጥ ተቅማጥ ሊያጋጥም ይችላል። በተለይም እንደ እንጀራ ያሉ ፈርመንትድ ሆነው የሚዘጋጁ ምግቦችን ሲመገቡ ውስጣቸው ከፍተኛ-ፋይበር/አሰር ያላቸው ምግቦችን ሲመገቡ (እንጀራ ከፍተኛ ፋይበር አለው) አንጀት ያለመዳቸውን ቅመሞች ሲመገቡ ፤ ለምሳሌ ሰናፍጭ፣ አዋዜ እና የመሳሰሉትን ሲመገቡ ከፍተኛ ፕሮቲን እና ስብ/ቅባት ያላቸውን ምግቦች ሲመገቡ ተቅማጥ ሊያጋጥም ይችላል። ይህም እንደ ምግቡ አይነት በህክምናው ኦስሞቲክ አልያም ፈንክሽናል ተቅማጥ የሚባሉትን የተቅማጥ አይነቶች ያስከትላል። ይህ አደገኛ አይደለም! ቢሆንም ምልክቶቹ ግን ለጊዜው ቢሆን ያሰቃያሉ። በቀላል አማርኛ አንጀት ገና አልተላመደም። ምናልባት ጥሬ ስጋ እና የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችን አለመልመዱ ቢሆንስ? 6️⃣ ምልክቶችስ ለምን በፍጥነትና በከባድ ሁኔታ ይመጣሉ ? ይህን ለመረዳት ሂደቱን መረዳት ይኖርብናል። ለበሽታ አምጪ ተህዋሳት ሲጋለጡ ፤ በሽታ አምጪ ተህዋሳቱ የአንጀትን ሚዛን የሚያዛቡ ፤ የአንጀት ግድግዳን የሚያጠቁ መርዞች ይለቃሉ። አንጀትም ውሀ እና ማእድናት ወደ ውስጡ ይስባል/ይከታል። ከዛም ሰውነት ያጋጠመውን እንግዳ ነገር/በሽታ አምጪ ተህዋስ ጠራርጎ በፍጥነት ለማውጣት ይምክራል። ይህን ጊዜ የሚያሩሩጥ የውሀ ተቅማጥ ይጋጥማል። ሰውነት ቶሎ ማውጣት ነው የሚፈልገው። ይህ የሰውነቶት መከላከያ እንጂ የአንጀቶት ድክመት አይደለም። ታድያ ግን ያስተውሉ፡ ይህ ከዚህ በሽታ ጋር ያለ ተቅማጥ ሂደት እንጂ ለሁሉም ተቅማጥ አይሆንም እነኝህን ምልክቶች ካሰተዋሉ ታድያ ፤ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ። 🚨ደም ከቀላቀለ 🚨 ትኩሳት ካለው 🚨ሰውነትዎ ውሀ ካነሰው (ምልክቶቹ የከንፈር እና ቆዳ መድረቅ ከጀመረ፣ ድካም፣ ራስምታት ያካትታሉ) 🚨 አብሮት ደጋግሞ የሚመጣ ትውከት ካለ። 🚨 ምልክቶቹ ከ 2 ቀናት በላይ ከቆዩ 🚨 ራስ መሳት ካለ ይህን ጊዜ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ። 7️⃣ ተዋርደን ይሆን? ይህ የትም ሀገር ሊያጋጥም የሚችል የህክምና ክስተት ነው። በሚኖርበት አገረ አሜሪካ እራሱ ከዚህ በፊት ያልተመገበውን ምግብ አይነት ተመግቦ ቢሆን ይህ ያጋጥመው ነበር። በራሱም አንደበት እንዲህ ሲል ተሰምቷል። "ወንድም! (ወደ ኢትዮጵያው አይሾው ስፒድ እየተመለከተ) ጥሬ ስጋ ስበላ አንጎሌ እስኪወጣ ሽንት ቤት እንደሚያስቀምጠኝ መናገር ነበረብህ። ለወደፊቱ ንገረኝ" አይ ሾው ስፒድ ስለ ሆድ ህመሙ ሲናገር የትኛው ነው የሚለውን ለመለየት የላብራቶሪ ምርመራ ቢያስፈልግም ፤ በሱ ሁኔታ ለአንጀቱ እንግዳ ከሆነ ጥሬ ስጋ እና ጥሬ ስጋ ለመብላት የምንጠቀማቸው ቅመሞች (ሰናፍጭ፣ አዋዜ፣ ወ.ዘ.ተ..) ጋር ተያያዥነት ያለው ይመስላል። ይህ በማንኛውም አገር ፤ በማንኛውም ቦታ ፣ ማንንም ሰው ሊያጋጥም የሚችል ክስተት ነው።

  • ንቅሳትና ጤና፡ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ምርጫ

    በአለማችን በእግርኳስ ብቃታቸው ከሚሞገሱ ተጨዋቾች መካከል ክሪስቲያኖር ሮናልዶ በቅድሚያ ይጠቀሳል። ስቴዲየም በደጋፊዎች ሲያጓራ ፤ ክርስቲያኖ ኳስ ላይ የሚያሳየውን ተአምራዊ ጥበብ ተከታትለናል። በዚህም ችሎታው አምስት ጊዜ ባላንዶር ያሸነፈ ፤ እውን ምርጥ ተጫዋች ነው። እንደን ንስር አይን ካሜራም እሱ ላይ ተተክሎ ፤ እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ፤ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ያለውን መስተጋብር ፤ ኳስን ከመረብ ጋር የማገናኘት ተአምራዊ ብቃቱን አሳይቶናል። አድንቀናል! ተደምመናል! ከ አስር አመታት በላይ በቴሌቭዥናችን መስታወት በጨዋታዎቹ እና በሚሰራቸው ማስታወቂያዎች ጥሩ ተክለቁመናው አለም አድንቆለታል። ታድያ ግን ላስተዋለ ከብዙ ቡድን አጋሮቹ ለየት የሚያደርገው አንድ ጉዳይ አለ። ሰውነቱ ላይ ምንም ንቅሳት የለም። ንቅሳት የውበት ማድመቂያ የማንነት መግለጫ በሚደረግበት ዘመን ፤ ብዙ ታዋቂ ሰዎች ተነቅሰዋል። ከመነቀስም ባሻገር ንቅሳታቸውን ለአለም አሳይተዋል። አድናቆትም ተችረዋል። ታድያ ለምን አልተነቀሰም? ንቅሳት ጠልቶ ይሆን? ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። ምክንያታዊ ውሳኔ ነው። ከፋሽንና መገለጫነት የተሻገረ ፤ የሌሎችን ጤና ያማከለ ውሳኔ። እንዴት!? ማለት ጥሩ... በምግባሩ መልካምነት እና ታታሪነቱ የሚታወቀው ይህ ኳስ ተጫዋች ፤ ለጋሽ ነው። በመደበኛ ሁኔታ ደም ይለግሳል ። የቡድን አጋሩ ካሮሎስ ማርቲኒ ልጅ ከታመመ በኋላም ደግሞ የአጥንት መቅኔ መለገስ ጀምሯል ። ደም ከመለገስ ባሻገሩም ሌሎች የሱን አርአያነት እንዲከተሉ ይገፋፋል። ሌሎችም እንዲለግሱም እንደ ቢ ዘ ዋን (Be the 1) አይነት የደም ልገሳ እንቅስቃሴዎችን አካሂዷል። ይህም ንቅሳት ከመነቀስ እንዲቆጠብ ካደረጉት ምክንያቶቹ መካከል አንዱ እንደሆነ ጠቁሟል። ለእርሱ ንቅሳት ከጌጥነት ይልቅ ፤ በጎ አድራጎቱን የሚያሰናክል ድርጊት ነው። ለመሆኑ ግን የተነቀሰ መለገስ አይችልምን? አዎም! አይም! ይህን ለመረዳት በዝርዝር እናውራ። እንደ አለም ጤና ድርጅት መመሪያ ከሆነ አንድ ደም ለጋሽ ቢያንስ ቢያንስ ከተነቀሰ ለ 6 ወራት ደም ከመለገስ እንዲቆጠብ ይመክራል ። የደም ልገሳ መመሪያቸውን ሙሉ በሙሉ በዚህ ላይ የመሰረቱ ሀገራትም በበኩላቸው ይህንን ተግባራዊ ያደርጋሉ። በአንዳንድ የተሻለ ክትትል ባላቸው ሀገራት ይህ የጊዜ ገደብ ከ3 እስከ አራት ወር ሊወርድ ይችላል ። ይህ የሚሆነው ግን ንቅሳቱ ትክክለኛ ፈቃድ ባለውና ጤናማነቱ በተረጋገጠ የንቅሳት ስፍራ ሲከናወን ነው። የንቅሳት ባለሙያውም ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚውል የንቅሳት መርፌ እና ቀለም መጠቀም ይኖርበታል። የደም ተላላፊ በሽታዎች በተንሰራፉባቸው ሀገራት ደግሞ ይህ የጊዜ ገደብ ወደ አንድ አመት ከፍ ሊል ይችላል። 📌 የጊዜ ገደቡ ለምን አስፈለገ? ንቅሳት በሚሰራበት ጊዜ ፤ የንቅሳቱ መርፌ ቆዳን በስቶ ፤ የንቅሳቱን ቀለም ከቆዳ ስር ያስቀምጣል። የዚህን ጊዜ ከደም ጋር ንክኪ ይኖረዋል። ታድያ ከእርሶ በፊት የተነቀሰው ሰው በደም የሚተላለፍ ኢንፌክሽን ካለበት ተጋላጭነት ይኖርዎታል። በዚህም የተነሳ እንደ ሔፕታይተስ ቢ እና ሲ አይነት የጉበት ቫይረሶች እንዲሁም ለኤች አይቪ (አልፎ አልፎ የሚያጋጥም) ይጋለጣሉ። ችግሩ ታድያ... እነኝህ ቫይረሶች ደም ውስጥ ገብተው እስኪንሰራፉ ጊዜ ይፈጃሉ። የተነቀሰው ሰው ደም ውስጥ ቫይረሶቹ ቢኖሩም ፤ መጠናቸው አነስተኛ በመሆኑ ፤ ሙሉ ኢንፌክሽን እስኪያመጡ በላብራቶሪ ምርመራ አይገኙም። ይህን ጊዜ ቢመረመሩ የላብራቶሪ ምርመራዎ በስህተት ጤነኛ እንደሆኑ ይጠቁማል። ደም ለግሰውም ከሆነ የለገሱት ደምም ሆነ አካል ከኢንፌክሽን የጸዳ ሆኖ ይታያል። ለዚህም እርግጠኛ ለመሆን የተሰጠውን የጊዜ ገደብ መቆየት መልካም ነው። ኢንፌክሽኑ ከለጋሽ ወደ ተቀባይ እንዳይተላለፍ ይህ የጊዜ ገደብ አስፈላጊ ነው። ታድያ ደም አዘውትሮ የሚለግስ ግለሰብ ፤ ይህንን ማወቅ እና ማክበር ይኖርበታል። ክርስቲያኖም ለወራት እንኳን ደሞ መለገስን ላለማቆም ሲል አለመነቀስን መረጠ። እስከአሁን ያወራነው ስለ ተቀባዩ ጤና ነው። አንድ ጥያቄ እንጠይቅ። የለጋሹ ጤናስ ? ለማስተላለፍ ለጋሹ መያዝ አለበት እኮ። በተለይም ክህሎታቸው በጤና ሁኔታቸው ላይ ለሚመሰረት አትሌቶች ፤ ይህን ተጋላጭነት መቀነሱ ይመከራል። 📌ይህን ያውቃሉ? ንቅሳት ዘላቂ የሚሆነው ሰውነትዎ ቀለሙን ስለተቀበለው ሳይሆን ማስወገድ ስለሚሳነው ነው። እስቲ በጥልቀት እናንሳ.... የንቅሳት ቀለም እጣፈንታ ምንድንነው? የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳይቱ ከሆነ ፤ የንቅሳት ቀለም ጠብታዎች በንቅሳቱ አከባቢ ብቻ አይቆዩም። እርቀው ይጓዛሉ። አንዳንድ ጥናቶች የንቅሳት ቀለም ጠብታዎች(ቅንጣቶች) ከንቅሳት ስፍራ አልፈው ንፍፊት ውስጥ እንደተገኙ ይጠቁማሉ። ይህም በተለይ ጥቁር ካርበን (carbon black) ያላቸው ቀለሞች ላይ ተስተውሏል። ' ታድያ ህክምናዊ አንድምታው ምንድነው? ንፍፊት የሰውነት መከላከያ ስርአት ማሰማሪያ ካምፕ እንደመሆኑ ፤ እነኝህ ቀለማት የሰውነት መቆጣት ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ። የበሽታ የመከላከያ ስርአታችን ለረዥም ጊዜ ተቆጥቶ እንዲቆይ ሊያደርጉ እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ። ታድያ ግን ሰውነት ቢቆጣም ፤ የሚስተዋል አካላዊ ምልክት ላይኖር ይችላል። የንቅሳት ቀለም ያጠቆራቸው ንፍፊቶች በናሙና ምርመራ ጊዜ ግራ ያጋባሉ። ከስር ያለ በሽታን ይከልላሉ። የሌለ በሽታም መስለው ምርመራን ሊያሳስቱ ይችላሉ። ንቅሳት ቆዳን በማቅለሙ ደግሞ ፤ የቆዳ በሽታዎችን በቀለሙ ይደብቃል። የቆዳ ምርመራዎችን አስቸጋሪ ያደርጋል። ይብሱኑ የቆዳ ካንሰር ቅድሚያ እንዳይታወቅ ሊሸሽግ ይችላል። ለዚህም ንቅሳት ቦታ ላይ የሚነሱ የቆዳ ካንሰሮች አርፍደው ሊገኙ ይችላሉ። 📌 ያስተውሉ ንቅሳት ካንሰርን ያስከትላል ማለት አይደለም። ነገርግን ካንሰር በቅድሚያ እንዳይያዝ ሊያሰናክል ይችላል። ይህም በህይወት እና ሞት መሀክል ለውጥ ያመጣል። ይህ መላምት አይደለም። በጥናት የተረጋገጠ ሳይንሳዊ እውነታ ነው! የንቅሳት ቀለሞች ባህሪስ ምን ይመስላል? ዘመናዊ የንቅሳት ቀለሞች የሚከተሉት ይኖሯቸዋል። ጥቁር ካርበን አዞ የሚባሉ ውህዶች እንደ ኒኬል፣ ክሮሚየምና ኮባልት አይነት ብረት አስተኔ ላይ የተመሰረቱ የጨው ውህዶች ይኖሯቸዋል። እነኝህ ውህዶች ለጸሀይ አልትራቫዮሌት ብርሃን ወይም ሌዘር ሲጋለጡ ይፈርሳሉ። ባህሪያቸውን ይለውጣሉ። ሲፈርሱ አንዳንዶቹ መርዛማ ሲሆኑ ሌሎች ለካንሰር አጋላጭ ወደሆኑ ውህዶች (carcinogenic amines) ይቀየራሉ። ከእነኝህም መሀል አለርጂ የማምጣት ባህሪ ያላቸው በመኖራቸው ፤ ከአመታት በኋላ አለርጂ ሊመጣ ይችላል። ለዚህም ነው የቆዳ ሀኪሞች ንቅሳት ጉዳይ ላይ ጠንቃቃ ሲሆኑ የሚታዩት። ከንቅሳት ለማገገም ቆዳ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብታል? ለአይን እይታ ቆዳ በ2-3 ሳምንታት ውስጥ የጠገነ ይመስላል። ሆኖም ከደረሰበት ጉዳት ሙሉ በሙሉ ለማገገም ረጅም ጊዜ ይወስድበታል። የቆዳ መቆጣቱ እስኪለዝብ እስከ 2 ወር (6-8 ሳምንት) ሊፈጅ ይችላል። ከወራት በኋላ እራሱ ንቅሳት ስፍራ ላይ የበሽታ መከላከያ ህዋሳት ዘብ ቆመው ሊስተዋሉ ይችላሉ። የተቆጣ የንቅሳት አከባቢ ማገገሙ እንዳለ ሆኖ ሲነቀሱ... ቆዶ ጥቃት ደርሶበታል። ሰውነትዎ ለኢንፌክሽን ተጋልጧል። ጠባሳ የማጋጠም እድሉም ከፍ ያለ ነው። ይህ ራሱን የቻለ አደጋ አለው። ዶክተሮች ለምን አለመነቀስን ይመክራሉ? የቱ ይሻላል መከላከል አልያም ማስታመም ከመከላከያ አንጻር ስናየው - ባለመነቀስዎ ፤ ንቅሳትን ተከትለው የሚመጡ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ሊያስወግዱ ይችላሉ። ከውበት ባሻገር ፤ በህክምናው ንቅሳት የተረጋገጠ ጥቅም የለውም። ያሉት አደጋዎች ትንሽ ቢመስሉም ፤ ተደማምረው ብዙ እክል ሊያመጡ ይችላሉ። ከዚህም ባሻገር ዘላቂ ናቸው። ንቅሳት ተከትሎ የመጣ ጠባሳ ለዚህም ነው የስፖርት ሐኪሞች ፣ ደም ልገሳ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች እና የቆዳ ስፔሻሉስቶችን አለመነቀስን የሚመክሩት። በተለይም ለኢንፌክሽን ተጋላጭነት ሊኖራቸው የማይገባ ግለሰቦች ላይ (ዝርዝሩ በቴሌግራም ገጻችን ላይ አለ) መነቀስ አይመከርም። ታሪካዊ ዳራው ንቅሳት ለዘመናት የቆየ ነው። በየባህሉ የተለያየ ትርጓሜ እና ምክንያት አለው። የጥንት ግብፃውያን ንቅሳትን ለአምልኮ ሥርዓት ይጠቀሙ ነበር። በሌሎች አፍሪካ አገራትም ንቅሳት ማንነትን፣ ጎሳን፣ እምነትን ይገልጽ ነበር። በጥንታዊ ኢትዮጵያም የታየው ተመሳሳይ ነበር። ታድያ አሁን ዘመናዊ መሣሪያዎች የምንጠቀም ቢሆንም ፤ እነኝህ መሣሪያዎች የንቅሳትን ህክምናዊ ምህዳር አልለወጡትም። ኤች አይቪ ኤድስ ተመልሶ እየተስፋፋባት ባለባት አዲስ አበባ ፤ የጉበት ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባት ኢትዮጵያ ፤ መነቀስ ምን አይነት ዳፋ ይዞ ሊመጣ ይችል ይሆን? ምላሹ የእርስዎ ነው! 🧠 ታድያ የሮናልዶ ውሳኔ ሲተነተን ይህን ይመስላል። ንቅሳትን ማስወገድ ከኢንፌክሽን ተጋላጭነቱን ይቀንሳል። የደም ልገሳው እንዳይቋረጥ ያደርጋል። የሰውነት በሽታ መከላከል አላስፈላጊ መቆጣት እንዳይኖረው ያደርጋል። በቆዳ ምርመራዎች ላይ መሰናክል እንዳይጋጥም ያደርጋል። አላስፈላጊ የሰውነት ጉዳትን ይቀንሳል። ለዚህም ይህ ውሳኔው በዘመናዊ ሳይንስ የተደገፈ ነው።

  • ሔፓታይተስ ሲ የጉበት ቫይረስ

    የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚገልጸው በአለማችን ወደ 58 ሚሊዮን ሰዎች ሥር ከሰደደ ሄፓታይተስ ሲ ጋር ይኖራሉ። ወደ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች  በየዓመቱ በቫይረሱ ይያዛሉ። 290,000 ሰዎች በየአመቱ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ምክንያት ይሞታሉ። ከ 10 አመት በፊት የነበረ የሄፓታይተስ ሲ ስርጭት። ኢትዮጵያ መካከለኛ ስርጭት ካላቸው ሀገራት መሆኗን ያስተውሉ! ጥናታዊ ጽሁፉን እዚህ ያገኙታል። ይህ ቫይረስ በሰውነትዎ ለዓመታት ወይም ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊከርም ይችላል። በዝምታ ቀስ በቀስ ጉበትን እያጠቃ ይመሽጋል። የጉበት ጉዳት እስኪስተዋል ድረስ ምልክት አይኖረውም። ሞትም ሲያጋጥም በቀጥታ ከቫይረሱ ይልቅ፤ በሚያደርሰው ጉዳት የተነሳ ነው። አሁን ህክምና በደረሰበት አቅም ከዚህ ቫይረስ ታክሞ መዳን የሚቻል ቢሆንም ፤ አሁንም ቫይረሱ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል። በኢትዮጵያም ሔፓታይተስ ሲ መዳን እየቻለ ፣ በዝምታ ብዙዎችን የከፋ ደረጃ ያደርሳል። ለመሆኑ ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ምንድን ነው? ሄፓታይተስ ሲ ጉብትን በይበልጥ የሚያጠቃ ፤ በደም ንክኪ የሚተላለፍ ቫይረስ ነው። በህክምናው ፍላቪቫይሪዴ የሚባለው የቫይረስ ቤተሰብ አባል የሆነ አር ኤን ኤ ቫይረስ ነው። ቫይረሱ ጉበትን በይበልጥ ያጥቃ እንጂ ፤ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ላይ ተጽእኖ አለው። ቫይረሱ አንዴ ከያዘ በኋላ ሰውነት ውስጥ ተደብቆ ፤ በቋሚነት ሰውነትን የማጥቃት ዝንባሌ አለው። ይህም በህክምናው ስር የመስደድ ባህሪ (chronic) በመባል ይታወቃል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፤ በቫይረሱ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ከ70% በላይ የሚሆኑት ሥር በሰደደ የሔፓታይተስ ኢንፌክሽን ይያዛሉ። ቫይረሱም ካልታከመ በስተቀር በሰውነት ውስጥ ይቆያል። ለዚህ ኢንፌክሽን አጋላጭ ምንድን ነው? ሄፓታይተስ ሲ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በትንፋሽ (በሳል)፣ እንዲሁም በአካል ንክኪ አይተለላፍም። በሻይረሱ ለተጠቃ ሰው ደም ጋር በሚኖር ንክኪ ብቻ ይተላለፋል። ለዚህም ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ ደህንነቱ ያባልተጠበቀ መርፌ በመወጋት / መርፌዎችን እንደገና መጠቀም እንደ እንጥል መቁረጥ ጉሮሮ መቧጠጥ ያሉ ባህላዊ የህክምና አማራጮች በደም ስር የሚወሰድ አደንዛዥ እጽ በመጠቀም የጤና ባለሙያዎች ስራ ላይ በሚያጋጥማቸው ድንገተኛ በመርፌ መወጋት በበሽታው ከተጠቃ ሰው ጋር በሚኖር ወሲባዊ ግንኙነት እንዲሁም አንዳንዴ በእርግዝና ወራት በቫይረሱ አንድ እናት ከተያዘች ፣ ቫይረሱ ወደ ጽንስ ሊተላለፍ ይችላል። ሄፓታይተስ ሲ በኢትዮጵያስ? በኢትዮጵያ በቫይረሱ ዙሪያ ላይ የተደረጉ ጥናቶች የቫይረሱ ስርጭት ከ 1 እስከ 3 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል ይገምታሉ። በቅርብ የወጡ ጥናቶች መጠኑ ከዚህም ሊቀንስ እንደሚችል ቢያመላክቱም ፤ ስርጭቱም እንደ ክልሉ እና አከባቢው የተለያየ ነው። ከምእራቡ አንጻር በኢትዮጵያ በደም ስር የሚወሰድ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ እምብዛም የለም። አብዛኛውን ጊዜ ንጽህናችው ባልተጠበቁ የባህላዊ ህክምናዎች፣ በህክምና ስፍራ በሚያጋጥም ተጋላጭነት እንዲሁም በግብረ ስጋ ግንኙነት በብዛት ይተላለፋል። ይህ እንደዚህ እንዳለ ብዙ የሄፐታይተስ ሲ ታማሚዎች ዘግይተው ህክምና ስፍራ ይመጣሉ። ጤና ተቋም በመጡ ጊዜ ቫይረሱ ጉበት ላይ ቋሚ ጉዳት አድርሶ ይገኛል። የቫይረሱን ስርጭት ለመቃወም የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ስትራተጂ ነድፎ እየሰራ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር የደም ልገሳ ፕሮግራሞች ደም ውስጥ ቫይረሱ መኖሩን ይመረምራሉ። ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራም እየሰራ ይገኛል። ሆኖም ግን ቫይረሱ በመደበኛ ሁኔታ እየተመረመረ አየደለም። የፀረ-ቫይረስ መድሀኒቱ ተደራሽነት ውስን ነው። የጸረ ቫይረስ መድሀኒቱም ሲገኝ ሂሳቡ ብዙዎችን ይፈትናል። የህመም ምልክቶቹ ቫይረሱ ጸጥተኛ ነው። ብዙ ጊዜ ጉዳት እስኪያደርስ ድረስ ምልክት አያሳይም። ምልክት ካሳየ ይህንይመስላል። ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲይዝ ፡ ፈጽሞ ምልክት ላይሳይ ይችላል። አልያም መለስተኛ ድካም ፣ አነስተኛ ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። አንዳንዶች ላይ ቆዳ እና አይን ቢጫ ሊሆኑ ይችላሉ። ቫይረሱ ስር ከሰደደ ቫይረስ ስር ሲሰድ፣ ታካሚዎች ምንም ላያስተውሉ ይችላሉ። አልያም ለዓመታት መለስተኛ ድካም ሊሰማቸው ይችላል። ቫይረሱ ግን ከጀርባ ጉበት ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ ይቆያል። ይህንንም ተከትሎ ጉብት ቋሚ ጉዳት ይደርስበታል። ከመቁሰል አልፎ ጉበት ጠባሳ ይኖረዋል። ጉበት እንደደረሰበት ጉዳት የተለያዩ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ። እነኝህም ምልክቶች በቫይረሱ የተነሳ የሚመጡ አይደሉም። ከጉበት ባሻገርስ? ሔፓታይተስ ሲ ቫይረስ ቆዳ ላይ የሚያመጣቸው ለውጦች። ጥናታዊ ጽሁፉን እዚህ ያገኙታል። ከጉበት ባሻገር ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ይጠቃሉ። የሚከተሉትን ሊጎዳ ይችላል- የበሽታ መከላከያ ስርዓት ን ያሰናክላል ኩላሊት ያስቆጣል (membranoproliferative glomerulonephritis) ቆዳንም ሲያጠቃ ቆዳ ላይ ጥቋቁር ምልክቶችን ያሳያል ( lichen planus, vasculitis) የሆርሞን ስርአትንም አዛብቶ ለ ስኳር ህመም ሊያጋልጥ ይችላል ( insulin resistance, type 2 diabetes ) ደም ላይ የፕሌትሌት መጠን ሊመነምን ይችላል። ባይታከሙስ ምን ይፈጠር ይሆን? ህክምና ከሌለ ሥር የሰደደ ሄፓታይተስ ሲ ወደሚከተሉት ሊያመራ ይችላል- 1️⃣ የጉበት መቁሰል /መከርቸች (Fibrosis) 2️⃣ የጉበት ጠባሳ (cirrhosis) 3️⃣  የጉበት ደም ስሮች ላይ የሚታይ ደ ም ግፊት (Portal hypertension) 4️⃣ የጉሮሮ ደም መፍሰስ (Variceal Bleeding) 5️⃣የሆድ መወጠር ወይም መነፋት (Ascites) 6️⃣ የጉበት ካንሰር ህክምና ቢደረግም ፤ አንዴ የጉብት ጠባሳ ካጋጠመ የጉበት ካንሰር የማጋጠም እድል እጅጉን ከፍተኛ ነው። ለዚህም ቀድሞ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። 📌 ሄፓታይተስ ሲ ሙሉ በሙሉ ሊድን ከሚችሉ በጣም ጥቂት ሥር የሰደደ የቫይረስ ኢንፌክሽኖች አንዱ ነው። ታሪኩ የሚቀየረው እዚህ ላይ ነው። በአሁኑ ወቅት ያሉ የቫይረሱ መቃወሚያ ፀረ ቫይረሶች (DAA) በአፍ በሚዋጥ መልክ የሚሰጡ ሲሆን ፤ ከ ሁለት እስከ ሶስት ወር መድሀኒቶቹን መውሰድ ያስፈልጋል። እነኝህ መድሀኒቶች በአግባቡ ከተወሰዱ ከቫይረሱ ፈጽሞ ይፈውሳሉ። ምን መደረግ አለበት? የ ጉበት ቫይረስ አለብዎ ? እንዴት አወቁ? ዛሬውኑ ይመርመሩ። በተለይ የህክምና መርፌ ከወጋዎት ጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ከሆነ ያልታወቀ የጉበት በሽታ ካለብዎ ከደም ጋር የተያያዘ/አካል መቆረጥ/መቅደድ ያለበት ባህላዊ ህክምና ካደረጉ በፍጥነት ይመርመሩ። ስር ሳይሰድ ፤ ቋሚ ጉዳት ሳያደርስ ቫይረሱን ይያዙት። ዛሬውኑ ተግባራዊ ለውጥ ያምጡ! ዛሬ ይመርመሩ! እርስዎንም ቤተሰብዎንም ይጠብቁ!

  • The Three Ghosts of New Year’s Day

    New Year’s is supposed to be a promise. A promise of a new beginning. A promise to make tomorrow better than yesterday. A promise whispered at midnight in Most cities around the world. Yet every year, there is a similar story. As fireworks crack the sky, emergency rooms across the world brace themselves. It is not just the celebrations that pose risks. New Year’s Eve and New Year’s Day are among the most dangerous hours of the year: medically, statistically, and tragically. Don't think of this as an opinion. Behind the celebrations, three “ghosts” sneak quietly in the darkness, leaving lasting harm and taking lives. They haunt only those who let their guard down. This is what decades of public health data, trauma registries, and emergency medicine textbooks reveal. Ghost 1: Road Traffic Crashes If New Year’s had a signature cause of death, this would be it. According to World Health Organization (WHO) data. road traffic injuries kill1.19 million people every year worldwide. They are considered the leading cause of death among young people aged 5–29 years globally. What makes New Year’s special? During the New Year, cars, fueled by alcohol and adrenaline, turn into lethal missiles. Medical and traffic surveillance data show that alcohol-impaired driving surges during celebrations. Data indicate that about one-third of New Year's Day traffic deaths involve alcohol, higher than any other day of the year. It is known that even small amounts of alcohol slow reaction times. It blurs vision and cloud judgement. Combine this with fatigue, night driving, and speeding, will give recipee for disaster. These road traffic accidents not only claim many lives but also result in major disabilities. In Emergency Rooms, doctors are busy treating severe head injuries, chest trauma, and abdominal trauma. In the worst cases, deaths occur before arrival This is a tragedy! What actually saves lives ✔ Zero drinking and driving. There is no “just one drink.” ✔ Designated drivers planned before the celebration ✔ Using taxis, rideshares, or staying overnight Ghost 2: Firework Injury Fireworks are a mesmerizing display before our eyes. They sparkle. They shine. They promise joy. They are sensations of the New Year`s celebration. They look harmless But in the hospital emergency rooms, they cause nightmares. Peer-reviewed Journals indicate that: Firework injuries peak within hours after midnight. Mostly the hands, eyes, face, and head are frequently injured areas. Most fireworks injuries require surgical treatment. Unfortunately, many victims are young adults and children. Firework injury severity is worsened by Alcohol. Deaths are less common than road crashes. Yet, when fireworks kill, they do so brutally! The long-term cost A single firework injury can result in: Permanent vision loss Finger or hand amputation Facial disfigurement Lifelong disability What do you need to do? ✔ Leave fireworks to professionals ✔ Never handle fireworks while drinking ✔ Keep children at a safe distance ✔ Avoid illegal or homemade fireworks entirely Ghost 3: Fires and Indoor Disasters Imagine a New Year`s Eve party..... The music is loud. Laughter fills the room. Champagne glasses clink. The night is alive… This is the perfect atmosphere! However, it is only a single spark away from catastrophe. New Year’s parties often share the same ingredients. They are mostly indoors with walls that trap heat and smoke. The parties are at night in a low-visibility setting, that slow reaction time. Mostly, the spaces are crowded with extra guests. Do you see the picture? This seemingly innocent combination is inherently dangerous. What are the hidden dangers: In these parties, strings of twinkling lights and overloaded electrical outlets can ignite within seconds. Candles and open flames are not placed at a safe distance. They can be found dancing too close to decorations. In the heat of the celebrations, people cook while intoxicated, when attention slips, and accidents happen And Accidents do happen! Data indicate that holiday fire tragedies rarely claim lives through flames alone . Most deaths come from smoke inhalation and panic-induced stampedes . These claims victims before flames even reach them. However, with a few simple precautions, it can be a night to remember 💡 How to keep the night alive—safely: ✔ Ensure exits are clear and limit the crowd ✔ Keep fire extinguishers handy and accessible ✔ Avoid open flames in crowded indoor spaces So this new year, you need to change your behavior. It will change outcomes. Remember It`s your choice ! Not luck. Not destiny. Not prayer alone. Simple choices determine who sees the next sunrise. Happy New Year 2026 from all of us at the Tegbar Organization! May this be the year we save more lives, make stronger choices, and create brighter tomorrows together. ✨

  • ከውፍረት ባሻገር ፡ ልብ ላይ ያለ ጫና

    በሚሊየኖች የሚሆኑ ሰዎች በአለም ዙሪያ የውፍረት ችግር አለባቸው። በፈረንጆች 2022 ይህ ቁጥር ወደ 900 ሚሊየን ይጠጋ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ውፍረት ደግሞ በበኩሉ ልብ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከባድ በመሆኑ ፤ ከእነኝህ መሀከል አብዛኞቹ በአመታት ውስጥ የልብ በሽተኞች ይሆናሉ። በልብ በሽታ ምክንያት ከሚሞቱ አስር ሰዎች መሀከል አንዱ ከውፍረት ጋር በተያያዘ ምክንያት እንደሚያርፍ ከ አመት በፊት የወጣ መረጃ ይጠቁማል። በግምትም በየአመቱ 1.9 ሚሊየን የሚሞሉ ሰዎች ከውፍረት ጋር በተያይዘ ልብ ህመም ይሞታሉ። ይህ ችላ ሊባል የማይችል እውነታ ነው! ጠላት ከሩቅ አይመጣም አይደል እንደሚባለው.... አብሮት ያለ ሰውነትዎ ውስጥ የተደበቀ ፤ ውፍረት እና ተያይዞት ያለ የስብ ችግር ፤ በአመታት ውስጥ ልብ በሽታ ሊያስከትል ይችላል። ይህ ቫይረስ ወይም መርዝ አይደለም። ግዙፍነት/ ግርማ ብለው የሚኮሩበት ፤ እንደሰውነትዎ የሚያስቡት ውፍረት ነው ጠላትዎ! 📊 ውፍረት ምንድንነው? በህክምና ክብደትን በተለያዩ ክፍሎች መመደብ የምንችልበት መስፈርት ሲኖር ፤ ከዚህ ውስጥ በዋነኝነት ጥቅም ላይ የሚውለው ቢኤም አይ (BMI) ይባላል። በዚህ መስፈርት መሰረትም ክብደት እንደሚከተሉት መክፈል ይቻላል። መደበኛ/ጤናማ ክብደት የሚባለው 18.5-24.9 ያለው ነው። ይህ ጤናማ ደረጃ ተብሎ ይታሰባል። ከመጠን በላይ ክብደት የሚባለው 25-29.9 ያለው ነው። ይህም ተያያዥ የጤና ችግሮች አሉት። ከመጠን በላይ ውፍረት የሚባለው ከ 30 በላይ ሲሆን ፤ ይህም ለልብ ፣ ስኳር ፣ ደም ግፊት እና የተለያዩ በሽታዎች ዋነኛ መንስኤ ነው። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለልብ በሽታ አንደኛ አጋላጭ ነው።  መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ቢኤምአያቸው ከ 30 የበለጡ ግለሰቦች ለ ልብ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው በ 2.4 እጥፍ የጨመረ ነው። ቢኤም አያቸው ከ 25 እስከ 29.9 የሆኑ ሰዎች እራሱ የልብ በሽታ የማጋጠም እድላቸው ከጤነኛ ሰው በ 61 % ይጨምራል። ይህ ቀላል አይደለም! ለልብ አደጋ ለመጋለጥ የግድ ከመጠን በላይ ውፍረት መሆን አያስፈልግም። ቢኤም አይዎ ከመደበኛ ከፍ እስካለ ድረስ የመጋለጥ እድልዎ የጨመረ ነው። 🔍 ይህ በሽታ ነው ! ከመጠን በላይ መወፈር በህክምናው እንደበሽታ ነው የሚታሰበው። በልብ መዋቅር እና ኡደት ላይም ጎጂ ለውጦችን ያመጣል። ቢኤም አይዎት ከመደበኛ መጠኑ በአንድ ሲጨምር የልብ ድካም አደጋን  በወንዶች ላይ በ 5% እናም በሴቶች ላይ ደግሞ በ 7% ይጨምራል። ሰውነትዎ ውፍረት እስካለው ድረስ ታታሪ ልብዎ መቼም ቢሆን ጤና አይደለችም። ሁልጊዜ ለአደጋ እንደተጋለጠች ነው። ታድያ በአመታት ውስጥ አንድ ቀን እጅ መስጠቷ አይቀርም። ትደክማለች ወይም የልብ ጥቃት ያጋጥማታል። ያን ጊዜ ግን አርፍደዋል። 📌አሳሳቢው ውፍረት፡ ቦርጭ ቦርጭ የምቾት መስሎ ሊታይ ይችላል። ሆኖም ግን የሰውነት አካላት ጋር የተደበቀ የስብ ክምችት እጅ አዙር አመላካች ነው። በድራፍት ጠጪዎች ላይ በብዛት ስለሚታይ የድራፍት ቦርጭ (beer belly) ይባላል። ውፍረት የሌለባቸው ቀጭን ሰዎች ላይ እንዲሁም ጥሩ ቁመና ያላቸው ሰዎች ላይም ይታያል። አንዳንዶች እንደውም ቢኤም አይ መስፈርታቸው ጤነኛ ሆኖ ቦርጭ ይኖራቸዋል። ቦርጭ እስካለ ድረስ ልብዎ መቼም ሰላም አትሆንም። በሆድ አካባቢ ውፍረት መኖር (ቦርጭ) የልብ ህመም ተጋላጭነትዎን ከግማሽ በላይ ይጨምራል። ቢኤም አያቸው ጤነኛ ሆኖ እንኳን ቦርጭ ያለባቸው ሰዎች እንኳን የልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው እስከ 33 ፐርሰንት የጨመረ ነው። ቦርጭ በጠፋ ቁጥር አካላት ውስጥ የተደበቀው ስብ እንዴት እንደሚጠፋ ይመልከቱ። ያስተውሉ ይህ የመልክ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ጥያቄው የልብ ጤና ነው። ልብዎት ሁሌም አደጋ ላይ ናት! 🔥 ውፍረት ብቻውን አይመጣም። ውፍረት ብቻውን አይመጣም። ጭፍሮች አሉት። ጀሌዎቹን አስከትሎ ነው የሚመጣው።ሰውነት ላይ በሚያደርሰው ጥቃት ብዙ በሽታዎችን ያመጣል። እነኝህም በሽታዎች በበኩላቸው ልብን ይበልጥ ያዳክማሉ። ከመጠን በላይ መወፈር  የደም ግፊትን ይጨምራል። ውፍረት በኩላሊት፣ በነርቭ ፣ በደምስሮችና በልብ ላይ በሚያደርሰው ጫና ፤ በአመታት ውስጥ ደም ግፊት እንዲከሰት ያደርጋል። ደም ግፊት በአለም ዙሪያ ለ ልብ ድካም እና ለስትሮክ ዋነኛ መንስኤ ሆኖ ይጠቀሳል። ከመጠን በላይ ክብደት ሰውነታችን ከስኳር ጋር ግንኙነት ላለው ለ ኢንሱሊን ሆርሞን ምላሽ እንዳይሰጥ ያደርጋል። ይህም በአመታት ውስጥ የስኳር በሽታን ያስከትላል። የስኳር በሽታም በበኩሉ የልብ ድካም እና የልብ ጥቃት በማምጣት የታወቀ ነው። ቢኤም አይዎ ከ 25 (ከመደበኛ) ከበለጠ የስኳር ተጋላጭነትዎ በ 5 እጥፍ የጨመረ ነው። ከ 30 ከበለጠ ደግሞ ተጋላጭነትዎ እስከ 28 እጥፍ ሊጨምር ይችላል። 📍 የደም ውስጥ ስብ ችግርና ውፍረት ሲወፍሩ ቆዳዎ ስር እና አካላቶችዎ አጠገብ ሰውነትዎ ትርፍ ስብን ያከማቻል። ከዚህም አልፎ አንዳንዴ ደም ስር ግድግዳ ላይም ስብን ማስቀመጥ ይጀምራል። የተትረፈረፈው ስብም ወደ ደም እየገባ የደም ውስጥ ስብ መጠን ይጨምራል። ሚዛን ያቃውሳል። ይህም እላይ ለጠቀስናቸው ለሁሉም በሽታዎች መንስኤ ይሆናል። አካላትን ያጠቃል። ደም ስር ያደድራል። ልብን ኩላሊትን ይጎዳል። ይህ የተዛባ የስብ ክምችት በህክምናው ዲስሊፒደሚያ (dyslipidemia)ይባላል። ስለ ደም ስብ ክምችት ለመረዳት ፤ ደም ውስጥ ስላሉ የስብ አይነቶች ማንሳቱ መልካም ነው። ባብዛኛው ማህበረሰብ ስለ ኮሌስትሮል በነሲብ ቢይቅም፤ የደም ውስጥ ስብ ኮሌስትሮል ብቻ አይደለም። በዋነኝነት አራት አይነት ስቦች አሉ። የእነኝህን ስብ አይነቶች ፤ ጤናማ መጠናቸው እና ልብ አደጋ የሚያስከትሉበት ከፍተኛ መጠን እነሆ ፡ የስብ አይነት ጤናማ መጠን የልብ አደጋ የሚጨምረበት መጠን ጠቅላላ ኮሌስትሮል <200 mg / dL ≥240 mg / dL - ከፍተኛ አደጋ LDL ("መጥፎ") ኮሌስትሮል <100 mg / dL ≥160 mg / dL - ከፍተኛ አደጋ HDL ("ጥሩ") ኮሌስትሮል ≥50 mg/dL (ሴቶች) / ≥40 mg/dL (ወንዶች) ከእነዚህ ያነሰ - ከፍተኛ አደጋ ትራይግላይሴራይድ <150 mg / dL ≥200 mg/dL የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል ያስተውሉ ከመጠን ባለፈ ውፍረት ጊዜ ይህ ሚዛን ይቃወሳል። የልብ ህመም ተጋላጭነትን በእጅጉ ይጨምራል። ቀጭን መሆንስ ከዚህ አደጋ ነጻ ያወጣል? "ቀጭን ነኝ! ስለዚህ ልቤ ጤናማ ነው። "የሚለውን አስተሳሰብ ማሰወገድ አለብን። ለእይታ ቀጨን መምሰል ነጻ አያወጣም። ለምን? ለእይታ ቀጭን ቢመስሉም በሰወነትዎ ውስጥ በተለይ አካላትዎ ስር የስብ ክምችት ሊኖር ይችላል። የደም ውስጥ ስብ መዛባት ሊኖርብዎት ይችላል። በተለይ ደግሞ ቦርጭ ካለብዎ! አዎ ! ጤናማ ክብደትን መጠበቅ ጠቃሚ ነው። ነገር ግን  ከጤናማ የደም ቅባት መጠን ጋር ካልተጣመረ በስተቀር ፍጹም የልብ ጤናን አያረጋግጥም። 🍔 አመጋገቤ ምን ይምሰል ?  የሚበሉት ነገርን ማስተካከል እጅጉን ጠቃሚ ነው። የደም ውስጥ ቅባት መጠንን ይቀንሳል። የልብ በሽታ አደጋን ይቀንሳል። 🔹 በፍራፍሬ፣  በአትክልት፣ በጥራጥሬ የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትረው ይመገቡ። 🔹 ጤናማ ስብ ይመገቡ። አለልክ የተጠበሱ ምግቦችን ፣ ጮማንና ቅቤን ይቀንሱ። በእነርሱ ፋንታ የእጽዋት ዘይቶችን ይመገቡ። አሳም የጤናም ስብ ምንጭ ስለሆነ ፤ አሳም መመገብ ይቻላሉ። 🥗 ኮሌስትሮሌን ለመቀነስ ምን ልመገብ? የደም ውስጥ ስብ መጠንን ለማሻሻል የሚከተሉትን እንዲመገቡ ይመክራል። ✔ አጃ እና አዝእርት- የሚሟሟ አሰር (ፋይበር) ስላላቸው መጥፎ ኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ያግዛሉ። ✔   ጥራጥሬዎች (ባቄላ ፣ ምስር)  - በፋይበርና በእፅዋት ፕሮቲን የበለጸጉ ስለሆኑ የመጥፎ ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳሉ። ✔ የቅባት እህሎች  - እንደለውዝ ያሉ የእጽዋት ቅባት ምንጮች ጤናማ ናቸው። የደም ውስጥ ስብ መጠንን ያሻሽላሉ። ✔   ዓሳ (ሳልሞን ፣ ሰርዲን)  - የባህር ምግቦች በኦሚጋ 3 ዘይቶች የበለጸጉ ስለሆኑ ፤ ትራይግላይሰራይድ በመባል የሚታወቀውን የስብ አይነት ይቀንሳሉ። ✔   ቅጠላ ቅጠሎች እና ፍራፍሬዎች  - አንቲኦክሲደንትስ እና አሰር (ፋይበር) ስላላቸው ፤ የደም ውስጥ ቅባት መጠንን ያሻሽላሉ። ለዚህም እነዚህን ምግቦች ሲመገቡ የደምዎ ውስጥ ስብ መጠን ይሻሻላል። 🍟 ማስወገድ ያለብዎ ምንድነው? ❌ ቅቤና ጮማ ይቀንሱ። ❌ የታሸጉ ምግቦች አያዘውትሩ። ውስጣቸው ትራንስ ፋቲ አሲድ(TFA) ያላቸው ዘይቶች አይጠቀሙ ። ❌ ብስኩቶች እና ጣፋጮች አያዘውትሩ። እነዚህ መጥፎ ኮሌስትሮልን አብዝተው ጥሩ ኮሌስትሮልን ይቀንሳሉ። በደም ስሮች ውስጥም ስብ እንዲከማች እድል ይፈጥራሉ። እዚህ አመጋገብ ላይ ክብደት ቢቀንሱስ ? ይህ እጅግ መልካም ነው! የደም ውስጥ ስብ ክምችትዎ ይሻሻላል። ጤናማ ይሆናል። የልብ ህመም ተጋላጭነትዎ ይቀንሳል። የቀነሱት ክብደት መጠነኛ ቢሆን እንኳን እንዳይዘናጉ። እንዳይሳነፉ ! ክብደትን በትንሹ መቀነስ እንኳን አመርቂ የሆነ ለውጥ ያመጣል። ውጤታማነቱ ከመድሀኒት ሊበልጥ እንደሚችል የሚጠቁሙ ጥናቶች አሉ። ለውጥ የሚመጣው ቀስ በቀስ ነው። ይበርቱ! አመጋገብዎን ያሻሽሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ። ልብዎ አምዎት ሳይመጡ ፤ ዛሬውኑ እርምጃ ይውሰዱ! መደበኛ ምርመራ ያድርጉ። ለልብዎ ጤና ፈጽሞ ችላ እንዳይሉ!

  • የልብ ድካም በሽታ፡ ለምን? እንዴት?

    ከመወለዳችን በፊት በእናታችን ማህጸን ውስጥ ስራ የሚጀምረው ታታሪው ልብ ፤ እስከ መጨረሻ ደቂቃችን ድረስ ይተጋል። ሆኖም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ሆስፒታሎች ተኝተው ከሚታከሙ አስር ታካሚዎች አንዱ የልብ ችግር እንዳለበት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም ውስጥ የልብ ድክመት ከፍተኛውን ይወስዳል። ለመሆኑ የልብ ድካም ምንድን ነው? መረረኝ ሰለቸኝ የማይለው ታታሪ ልብ እንዴትስ ደከመ? እዚህ ጋር የልብ ድካም የሚለውን ቃል ቀድመን መለየት ይኖርብናል። በተለምዶ ሁለት የልብ በሽታዎች የልብ ድካም ተብለው ይጠራሉ። አንደኛ፡ ልብ አቅም ሲያጣ እና የተለምዶ ስራውን መስራት ሲያቅተው ልብ ደከመ እንላለን። ይህ በህክምናው ኸርት ፌለር (Heart Failure) ይባላል። ሁለተኛ፡ የልብ መጋቢ ደም ስር ሲደፈን ፤ እርሱን የተመረኮዘው የልብ ጡንቻ ይሞታል/ ይታፈናል/ይራባል። ይህ ደግሞ በህክምና ማዮካርዲያል ኢንፍራክሽን (myocardial infraction) ይባላል። ይህን ብዙ ጊዜ ፊልሞች ላይ ያሉ ገጸ ባህሪያት ልባቸውን ይዘው ሲወድቁ የምናየው ህመም ነው። ይህ በተለምዶ ልብ ድካም ይባል እንጂ ስያሜው በሽታውን በትክክል አይገልጽም። ይልቁኑ የልብ ጥቃት (Heart attack) አቻ የሚለው ትርጓሜ ይሻላል። በዚህ ጽሁፍ የምናወራው ስለመጀመሪያው ነው።       የልብ ድካምን እንደ አንድ በሽታ አያስቡት። የልብ ድካም የብዙ የልብ በሽታዎች መጨረሻ መዳረሻ ነው። ያልታከሙ አልያም በህክምና ቁጥጥር ስር ያልዋሉ ብዙ በሽታዎች የልብ ድካም ያመጣሉ። ልብ "ሲደክም" ማለት ምን ማለት ነው? በሕክምና አነጋገር የልብ ድካም የሚከሰተው ልብ የሰውነትን  ፍላጎት ለማሟላት በቂ ደም መርጨት/ መግፋት ሲሳነው ነው። አልያም ይህንን ለማድረግ ልብ ከፍተኛ ጉልበት የሚያወጣ / ግፊት የሚያሳድር ከሆነ ልብ ደክሟል ይባላል። ይህንን ለመረዳት አንድ የጉልበት ሰራተኛን በምናብዎ ይሳሉ። ይህ የጉልበት ሰራተኛ ቀኑን ሙሉ ሳያሰልስ በቀላሉ ሲሸከም ውሏል። ወደ ኋላ ግን ሲደክም ፤ ተመሳሳይ ስራ ለመስራት በጣም ኃይል ማውጣት ፤ ወይም የሚሸከመውን ክብደት መቀነስ ይጀምራል። ልብም ላይ እንዲሁ... ታድያ ልብ ሲደክም የወትሮ ስራውን መስራት ይሳነዋል። ይህን ስራውን መስራት በመሳኑ ፤ በተለያዩ አካላት ላይ ምልክቶቹ ይስተዋላሉ። ሳንባ ውሀ ይይዛል። ለዚህም ትንፋሽ ማጠር ሊታይ ይችላል። ወደ ሰውነት በቂ ደም እየተዳረስ ስላልሆነ ፤ በትንሽ እንቅስቃሴ ቶል ድካም ይኖራል። ጉበትም ይቆጣል/ ያብጣል። እግሮች እንዲሁም ሆድ እብጠት ሊኖራቸው ይችላል። ከዚህም ባሻገር የምግብ ፍላጎት ሊቀንስ ፤ የደረት ህመም ሊሰማ፣ የልብ አመታት ሊለወጥ፣ ወ.ዘ.ተ... ይችላል። ከባድ ድንገተኛ ጥቃት ካልደረሰበት በቀር ፤ ታታሪው ልብ እስኪደክም አመታት ይፈጅበታል። ልብዎ ግን እጅ በቶሎ አይሰጥም ። ጉድለቱን ለማስተካከል ፤ በቂ ደም ለሰውነት ለማድረስ ይታገላል። ለዚህም እንዲረዳው የልብ ጡንቻውን ያወፍራል፣ ግድግዳዎቹን ያሰፋል፣ በፍጥነት መስራት ይጀምራል። ታድያ ግን ይህም አይበቃም። እነኝህ ማካካሻ እርምጃዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የልብ ስራን ቢያሻሽሉም ፤ በጊዜ ሂደት ውስጥ ልብን በይበልጥ ይጎዳሉ። ስራውን ያስተጓጉላሉ። ለዚህም ልብ ይበልጡኑ ይዳከማል። ልብ ሰውነትን ለማዳን በሚያደርገው ትግል ውስጥ ፤ ራሱን ቀስ በቀስ ያጠፋል። ለምን የልብ ድካም ያጋጥማል? የልብ ድካም በሽታ በተለያዩ ምክንያቶች የሚመጣ ቢሆንም ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛ ምክንያት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። 1. ከፍተኛ የደም ግፊት ይህ እጅጉን የተለመደና በጣም ችላ የሚባል የልብ ድካም ምክንያት ነው። ከአምስት ጎልማሳ መሀል አንዱ የደም ግፊት ህመም አለበት በሚባልባት ኢትዮጵያም አሳሳቢ ነው። ብዙዎቹም 'ጤነኛ ነኝ 'ብሎ በማመን ቁጥጥር ስር ያልዋለ የደም ግፊት በሽታ  ይዘው ይኖራሉ። የደም ግፊት ቁጥጥር ላይ ሳይውል ከፍ ብሎ ከቆየ ፤ ልብ ላይ ጫና ያሳድራል። ልብ መደበኛ ስራውን ለመስራት ፤ ይህንን የደም ግፊት ተቃርኖ መግፋት አለበት። ይህም የልብን ጡንቻ ያወፍራል። አንድ ስፖርተኛ ጂም ገብቶ ክብደት አንስቶ እንደሚገዝፈው ፤የልብ ጡንቻዎች ከፍተኛ ግፊት እየተቃወሙ ስለሚሰሩ ይገዝፋሉ፤ ይደነድናሉ። ይህም ልብ የሚሸከመውን ደም መጠን ይቀንሳል። ስራውን ያስተጓጉላል። ለአመታት ልብዎት በጸጥታ ታግሎ ፤ በመጨረሻ እጅ ይሰጣል። ይዳከማል። ይህን ጊዜ ምልክቱን ያያሉ። ነገር ግን ልብ ቀድሞውኑ ጉዳት ደርሶበታል።   2. የሩማቲክ የልብ ሕመም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የልብ ድካም ምክንያቶች ውስጥ ይህ ከፍተኛ ቦታው ይወስዳል።  በሽታው በህክምና ስሙ የሪዩማቲክ የልብ ህመም ይባላል። ስለዚህ በሽታ በጥልቅ ለማወቅ ፤ ከዚህ በፈት የጻፍነውን ጽሁፍ ያንብቡ። ይህ ህመም የሚጀምረው ፤ በልጅነት ጊዜ ባልታከመ የጉሮሮ ኢንፌክሽን ነው። ኢንፌክሽኑ ቢጠፋም የበሽታ መከላከያ ስርአታችን የልብ ቧንቧን ያጠቃል። ይህም ቧንቧዎቹንም ያጠባል። የእነኝህ ቧንቧዎች በስርአት አለመስራት ፤ ልብ ላይ ስራን ይጨምራል። ልብም ስራው እንዳይስተጓጎል ፤ ጉልበት አሳድሮ በይበልጥ ይሰራል።  ታድያ ለአመታት ሲተጋ የነበረው ልብም መዛል ይጀምራል። ይዳከማል። ብዙ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመምተኞችን የሚያጋጥመው አሳዛኝ እውነታም ይሄ ነው። በሚዋጥ ባክቴሪያ መቃወሚያ (antibiotics) መከላከል ግን ይቻል ነበር። በይበልጥ ለማወቅ ይህንን ትምህርታዊ ጽሁፍ ያንብቡ። ከኦክስጅን ማነስ ጋር የተያያዙ የልብ በሽታዎች ልብ ጡንቻ ነው። ልክ እንደ ሁሉም ጡንቻዎች  ኦክስጅን  እና ምግብ ያስፈልገዋል። ይህ ደግሞ በልብ መጋቢ ደም ስሮች በኩል ይደርሳል። ታድያ የእነኝህ ደም ስሮች መቋረጥ/ መጥበብ ለልብ ጡንቻዎች የሚደርሰውን የደም አቅርቦት ይቀንሳል። ልብም በቂ ኦክስጅን ስለማይደርሰው ይታፈናል። ለዚህም የልብ ጡንቻ መታፈን የሚያመጡ በሽታዎች (Ischemic Heart Disease)ይባላሉ። በኦክስጅን እጥረት የተነሳ የልብ ጡንቻዎች ስራቸውን በአግባቡ መስራት ይሳናቸዋል። ይሞታሉ። ይህም የልብ ስራን ይበልጥ ያስተጓጉላል። የተቀረው የልብ ክፍልም በተጎዱ ጡንቻዎች ፋንታ ለመስራት ስለሚሞክር ፤ ጫናው ይበዛበታል። ይህም ልብን ያዳክማል።  ይህ በሽታ  በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ይገኛል። ለመስፋፋቱ ባለፉት አመታት ያሳየናቸው የአኗኗር ለውጦች እንደመንስኤነት ይጠቀሳሉ። 4. የስኳር በሽታ በብዛት እንደሚታወቀው የስኳር በሽታ ልብ ላይ ብዙ ጉዳት ያሰከትላል። ስኳር ልብን በተለያዩ መንገዶች ሊጎዳ ይችላል። ከላይ ባየነው መሰረት ፤ የልብ ደምስሮችን በማጥበብ ፤ ጡንቻዎችን ሊያስርብ ይችላል።  የደምስሮች መደደርን ሊያመጣ ስለሚችል ፤ ልብ ላይ ስራ ሊጨምርም ይችላል።  የልብን ትናንሽ የደም ስሮችንም  ያጠቃል።  ከዚህም ባሻገር የልብ ጡንቻ ላይም ተጽእኖ ያሳድራል። እነኝህም በጊዜ ሂደት ውስጥ ልብ ድካም ያመጣሉ። ለዚህ የደምዎን የስኳር መጠን ዛሬውኑ ይቆጣጠሩ።   5. ሌሎች በሽታዎች ከዚህም ባሻገር ረዥም ጊዜ የቆየ የደም ማነስ ኦክስጅን መጠንን ስለሚቀንስ ልብ ብዙ እንዲሰራ ያስገድደዋል። ይህም በጊዜ ውስጥ ልብን ሊያዳክም ይችላል። ለዚህም ደም ማነስ ነው ብለው አይዘናጉ። የሳንባ በሽታዎች ሳንባ ጋር ያለውን ግፊት ሊጭምሩ ስለሚችሉ ፤ ከሳንባ ጋር ግንኙነት ያለው የቀኝ ልብ ይዳከማል። ለረዥም ጊዜ የቆዩ ኢንፌክሽኖችም በቀጥታ ልብን በመጉዳት አልያም ልብ ላይ ስራ በመጨመር ያዳክማሉ።   የልብ ድካም ለምን አሳስቢ ሆነ? የልብ ድካም የደም ዝውውር በሽታ ብቻ አይደለም። የዕለት ተዕለት ኑሮ ተግዳሮት ነው። ታካሚዎች በተለምዶ የሚሰሯቸውን ስራዎች ለመስራት ይቸገራሉ።  ቤት ማስተካከል፣ ርቆ መራመድ ፣ መስገድና መጸለይ  እንኳን ሊሳናቸው ይቻላል። እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መድከም/ ትንፋሽ ማጠር ሊያጋጥማቸው ይችላል። እንቅስቃሴ ያለው ስራ በአግባቡ ለመስራት ስለሚቸገሩ ፤ ከስራ ቦታ ሊፈናቀሉ ይችላሉ። በሌላ ሰው ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ሆስፒታልም ደግመው ደጋግመው ይሄዳሉ። የኢትዮጵያስ እውነታ ምን ይመስላል?   በኢትዮጵያ የተደረጉ ጥናቶችም ይህንን ይደግፋሉ። የልብ ድካም በሽተኞች ብዙ ተግዳሮቶች ይገጡማቸዋል። ይህም በገጠሪቷ ኢትዮጵያ በሚኖሩ፣ በሴቶች እንዲሁም ዝቀተኛ ገቢ ባላቸው  የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ይሰተዋላል። በሽታው ለእነኝህ ማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮን ያከብድባቸዋል። ድህነትንም ያባብሳል። ድህነትም በበኩሉ ደግሞ በሽታውን ያባብሰዋል። ።  ይህ አስከፊ አዙሪት ነው!    የልብ ድካም ለምን ረፍዶ ይታወቃል? የልብ ድካም ብዙ ጊዜ አያስታውቅም። የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች በእለት ተእለት ህይወት የሚያጋጥሙንን ያስመስላሉ። ታካሚዎች "በቃ ደክሞኛል" "እያረጀሁ ነው" "ውጥረት ነው"ይላሉ።  በተለይ የህክምና ተደራሽነት ዝቀተኛ በሆነባቸው አከባቢዎች እነኝህ ምልክቶች ቦታ አይሰጣቸውም። ለዚህም በኢትዮጵያ የልብ ድካም ብዙ ጊዜ ዘግይቶ፣ ከብዶ እና ተወሳሰቦ ይደረስበታል።   ይህንን ታሪክ መለወጥ ግን ይችላሉ። ቀድመው የደም ግፊትዎን ከተቆጣጠሩ በአፋጣኝ የጉሮሮ የኢንፌክሽን ህክምና ካደረጉ የደምዎን የስኳር መጠን ከተቆጣጠሩ መደበኛ የጤና ምርመራ ካደረጉ መከላከል ይችላሉ! ፍቱኑ መድሀኒትም መከላከል ነውና ፤ ፈጽሞ አይዘናጉ። ዛሬውኑ እርምጃ ይውሰዱ።  ጤና ተኮር ትምህርታዊ መረጃዎችን በመከታተል ግንዛቤዎን ያስፉ።

  •  ጸጥተኛው መንገድ፡ ከከፍተኛ የደም ግፊት ወደ ኩላሊት ውድቀት

    ይህን ያውቃሉ? በአለም ዙሪያ ከ 5 ሰዎች ውስጥ አንዱ( 1.4 ቢሊየን ሰዎች) የደም ግፊት በሽታ አለባቸው። ደም ግፊት ካለባቸው አምስት ሰዎች ውስጥ በአማካይ አንዱ (21 %) ስር የስደደ የኩላሊት በሽታ አለበት።  ይህ ማለት በአለም ዙሪያ 294 ሚሊየን ሰዎች በደም ግፊት ምክንያት የመጣ የኩላሊት በሽታ አለባቸው። በኢትዮጵያም መረጃዎች ተመሳሳይ ስርጭት ያሳያሉ። ከ 3 አመት በፊት በተደረገ ጥናት ከ 5 ኢትዮጵያውያን ውስጥ በአማካይ አንዱ (19.6 በመቶ) የ ደም ግፊት አለበት። በኩላሊት በሽታዎች ዙሪያ ሀገር አቀፍ ጥናት ባይኖርም ፤ አንድ አምስተኛ የሚጠጉ የደም ግፊት በሽተኞች (21.7%) ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ (CKD) አለባቸው። ይህ ቀላል ቁጥር አይደለም! በኢትዮጵያ ባሉ የጤና ተቋማት ፤ ሰዎች በየጊዜው ከባድ የኩላሊት ጉዳት/በሽታ እንዳለባቸው ፤ በድንገት ይሰማሉ። ይህም ብዙዎችን ያስደነግጣል። እንዴትም ብለው ብዙዎች ይጠይቃሉ? ምላሹ ቀላል ነው።! ለዓመታት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የደም ግፊት ኩላሊትን ይጎዳል። አሳዛኙ ሁኔታ ደም ግፊትም ኩላሊት በሽታም እንዳለባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያውቁም አሉ። ለምን ካሉ ፡  የደም ግፊት ድምጽ የለውም! ምልክቶችም ላይሳይ ይችላል።  ቁጥጥር ስር ካልዋለ ልብን ይጎዳል ፤ ኩላሊትን በለሆሳስ ያጠፋል።  የተሟሉ የዲያሊሲስ ተቋማት ውስን በሆኑባት ኢትዮጵያ ደግሞ ፤ ይህ እጅጉን ሊያሳስብ ይገባል። ያሉን የዲያሊሲስ ህክምና አገልግቶቾች በከተሞች ከመገኘታቸው ባሻገር ፤ ሂሳባቸው ከፍ ያለ ነው። ይህም ረዥም ጊዜ የኩላሊት እጥበት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የህክምና ወጪ ኢኮኖሚን ያቃውሳል።   የደከመ ኩላሊትን ከማከም የኩላሊት በሽታን መከላከሉ ቀላል ነው። ቁልፉ ደግሞ የደም ግፊትን መቆጣጠር ነው። ደም ግፊት  እንዴት ኩላሊት በሽታ ያመጣል? ይህን ለመረዳት ኩላሊትዎን እንደ ማጥለያ አድርገው ይውሰዷቸው። እነኝህ ጥቃቅን ማጥለያዎች አያርፉም። ደም በየደቂቃው በውስጣቸው ያልፋል።  ቆሻሻን ፣ ትርፍ ፈሳሽን እና መርዛማ ኬሚካሎች አስወግደው ፤ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን (ፕሮቲንን ጨምሮ) ሰውነት ውስጥ ያስቀራሉ። ታድያ እነኝህ ማጥለያዎች በስርአት እንዲሰሩ የሚያርፍባቸው ግፊት ትክክለኛ መጠን መሆን አለበት። ግፊቱ ሲበዛስ? እነኝህ ማጥለያዎች ከፍ ባለ ግፊት ውስጥ በሚሰሩበት ጊዜ ይጎዳሉ። መደበኛ ማጥለያ ግፊት ብናበዛበት እንደሚቀደድ/ እንደሚበጣጠስ ሁሉ ፤ እነኝህ ማጥለያዎች ጠባሳ ያመጣሉ። ስራቸው ይስተጓጎላል። ያስቀሩት የነበረው ፕሮቲን በሽንት በኩል አምልጦ መውጣት ይጀምራል። የፕሮቲኑ አፈንግጦ መውጣት ከኩላሊት ጉዳት የመጀመሪያ ምልክቶች መሀከል ይካተታል። ኩላሊትን የሚመግቡ የደም ስሮችም ያለውን ከፍተኛ ግፊት ለመቋቋም ግድግዳቸው ይወፍራል። ይህ የደም ግፊት ለወራት ወይም ለዓመታት ከፍ ያለ ሆኖ ሲቆይ፤ የኩላሊት ስራ እየተዳከመ ይመጣል። የኩላሊት ውድቀት ይመጣል።  ሂደቱ ግን ዝግ ያለ ፤ እንዲሁም ህመም የሌለው ነው። ለዚህም ብዙ ጊዜ ሰዎች የኩላሊት በሽታቸውን የሚያውቁት ጉዳቱ ካየለ በኋላ ፤ የኩላሊት ውድቀት ሲጀምር ነው።   ይህም ያዘናጋል። ብዙዎችም ደም ግፊታቸውን ለመቆጣጠር ይሰንፋሉ። መድሀኒቶቻቸውን በስርአት አይወስዱም። በመደበኛ ሁኔታ ደም ግፊታቸውን አይከታተሉም። ይህንን ለመከላከል የደም ግፊትዎ ስንት ቢሆን ይመከራል? ይህ እንደታካሚው ስለሚለያይ ፤ ዶክተርዎን ቢያማክሩት ይመረጣል። ታካሚ እንዳለበት የደም ግፊት ደረጃ ፤ ግቡ ሊለያይ ይቻላል።   አለም አቀፍ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የደም ግፊት መጠንዎ ከ 140/90 እንዲያንስ ይመከራል። ከተቻለ ከ130/80 ቢሆን እጅጉን ተመራጭ ነው። ሆኖም ግን ዶክተርዎን ያማክሩ። የደም ግፊት ካለብዎ እነኝህን ምልክቶች ችላ አይበሉ! እላይ እንደጠቀስነው ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ቀድሞ ምልክት አያሳይም። እነኝህን ምልክቶች ግን ካዩ ፤ የኩላሊት ጉዳትን አመላካች ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ ችላ አይበሉ። የእግር(ቁርጭምጭሚት ጋር) እና አይን አከባቢ ያለ እብጠት ሽንት ላይ አረፍ መኖር (ሽንት ውስጥ ፕሮቲን መደባለቁን ያመላክታል) ምንጩ ያልታወቀ ድካም የሽንት መጠን መቀነስ የምግብ ፍላጎ መቀነስ ማቅለሽለሽና ማስታወክ ምልክቶቹን አይተው በሄዱ ጊዜ እንኳን ፤ ኩላሊት ከባድ ጉዳት አጋጥሞት ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ምልክቶቹን እንዳዩ በአፋጣኝ መሄድዎ ፤ ጉዳቱን ባለበት ለመቆጣጠር ያስችላል። ምልክቶቹን ከማወቅ በላይ ፤ መደበኛ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ ይመከራል። ይህም የኩላሊት ጉዳት ገና ሳይጀምር ለመያዝ ያስቻላል።   ለመከላከል ምን ያድርጉ? ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎ / የደም ግፊት ያለበት ሰው የሚንከባከቡ ከሆነ  የሚከተሉትን ያድርጉ። የደም ግፊትዎን በየጊዜው ይለኩ።  ምልክቶች አይጠብቁ። አቅራቢያዎ ያለ ፋርማሲ ወይም የጤና ተቋም ሄደው ይመርመሩ። ዶክተርዎ ያዘዘልዎ መድሃኒቶችን ያለማቋረጥ ይውሰዱ። መድሀኒት መዝለል ኩላሊት ላይ ጉዳት እንዲያጋጥም እድል ይከፍታል። የሚመገቡትን የጨው መጠንን ይቀንሱ።  ጨው የደም ግፊት መጨመር ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አለው።  መደበኛ አካላዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ። ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ።  መደበኛ የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ።  ኩላሊትዎ ተዳክሞ እስኪሄዱ አይጠብቁ። እንደ ደም ክሪያቲኒን እና ሽንት ምርመራ ያሉ ቀላል ምርመራዎች ራሲ ጉዳት መኖሩን ሊጠቁሙ ይችላሉ። ያስተውሉ ፡ መጠነኛ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች እንኳን የደም ግፊትን ቁጥጥርን ያሻሽላሉ። የደም ግፊት በሽተኛ መሆንዎ በራሱ ፤ የኩላሊት በሽታ የመጋጠም እድልዎን ይጨምራል። ያስተውሉ አላመምዎትም ማለት ደህና ነዎት ማለት አይደለም።  የደም ግፊትዎን ይለኩ! መድሃኒትዎን ይውሰዱ! ከማርፈድዎ በፊት ኩላሊትዎን ዛሬ ይጠብቁ!

bottom of page